Telegram Web Link
#ጉባኤ_ሐዲስ_ኪዳን
(ለማስታወስ)
#ማቴ_8_ክፍል_አምስት
“በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።”
  — ማቴዎስ 8፥16-17
ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ።”
  — ማቴዎስ 8፥18
• ብዙዎች መሆናቸው ከነፍስ ኃጢአት የተነሣ ብዙዎች የአጋንንት ማደሪያ የነበሩ መሆናቸውን ያሳያል

• መላው የሰው ልጅ በእግረ አጋንንት እየተጠቀጠቀ የነበረ መሆኑን ለማመልከት
• የአጋንንትን በሰው ልጅ ላይ መሠልጠን ለማስረዳት
#መናፍስትን በቃሉ አወጣ፤ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ

• መናፍስትን በቃል ማስወጣት፡-
•  የማዘዝ ሥልጣንን የሚገልጽ ነው፤
•  በቃሉ ዓለማትን የፈጠረ መሆኑን የሚያስረዳ ነው ፤
• ምሥጢሩ፡- አካላዊ ቃል ወልድ ዲያብሎስን ድል አድርጎ እኛን ማዳኑን ያጠይቃል
• የታመሙትን መፈወስ፡- የታመሙ ማለት ስቃይ ያለባቸው ፤ ሌሊትም ቀንም በህመም ስሜት የሚሰቃዩ ማለት ነው፤ ከስቃያቸው እንዲያርፉ ከድካማቸው እንዲፈቱ ማድረጉን ያመለክታል፤
•  ምሥጢሩ ፡- ከስቃየ ሲኦል ከጻዕረ ሞት ከሙስና መቃብር ሊያድነን መምጣቱን ያስረዳል
ክፍል አምስት
• ‹‹ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ›› ማቴ 8፡18
• የከበቡት ሰዎች መልኩን ማየት የሚፈልጉ (እስመ መብዝኅተ ዓለም ዘይተልውዎ ለመድኅን ኮኑ ይፈቅዱ ይርአዩ ብርሃነ ዐቢየ ወስነ ብሩሀ ዘይወጽእ እምገጹ፤ ዮሐ.አፈ)፤ ተአምራት የሚፈልጉ ፤ ፈውስ የሚፈልጉ ናቸው
• ምሥጢሩ ፡- በትንቢት መነጽርነት የተመለከቱት ነቢያት በትንቢት በተስፋ በሱባዔ ከበቡት ማለት ነው
• አንድም አብነት የሚያደርጉት ሐዋርያት ፤ ሰማዕታት፤ ሊቃውንት መምህራን ፤ ምእመናን በአሚን/ በሃይማኖት ከበቡት ማለት ነው
መሻገር
• ጌርጌሴኖን የአጋንንት መንደር ነው፤ የመቃብር የሲኦል የገሃነም ምሳሌ ነው (28)
• ወደ ማዶ እንዲሻገሩ ማዘዙ የሰው ልጅ ከበደል በኋላ በሥጋ ወደ መቃብር ፤ በነፍስ ወደ ሲኦል ወደ ገሃነም እንዲወርድ ተፈርዶበት የነበረውን ያሳያል
• አርሱ በመርከብ ተሸግሮ ይፈውሳቸዋል፤ በሥጋ ማርያም ተገልጦ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ታሪካችንን መቀየሩን ያመለክታል ፤
• ወደ ማዶ መሻገር ማለት ነቢያት ዘመነ ክርስቶስን በሩቅ እንደተመለከቱት በእምነት እንደተሻገሩት የሚያሳይ ነው (እነርሱም በአካለ ነፍስ ሲኦል ወርደው ነበር)
• በሐዲስ ኪዳን ነፍሳት በመስቀል ትርክዛው ባሕረ እሳት እየተቀዘፈላቸው በዕለተ ዓርብ ከሲኦል ወጥተው ወደ ገነት እንደሚሻገሩ የሚያሳይ ነው (ማዕዶት የሚባለው ይህ ነው፤ ከጌርጌሶኖን )
• ሐዋርያት ፤ ሰማዕታት፤ ሊቃውንት ፤መነኮሳት፤ መምህራን፤ ምእመናን መከራውን በጥብዐት እንዲሻገሩት የሚያሳይ ነው

....ይቀጥላል
ይቆየን!

ሁላችንን ወደ ንስሐ ሕይወት ያሻግረን🙏

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
#መስከረም_5

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም አምስት በዚች ቀን #ቅድስት_ሶፊያ_ሰማዕት ከሁለት ልጆቿ ጋር በሰማዕትነት አረፈች፣ #አቡነ_አሮን_መንክራዊ እረፍት ነው፣ #ቅዱስ_ማማስ_ሰማዕት በሰማዕትነት አረፈ፣ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ #አፄ_ልብነ_ድንግል እረፍቱ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሶፊያ_ሰማዕት

መስከረም አምስት በዚች ቀን የከበረች ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ አክሶስናና በርናባ ከሚባሉት ጋር በሰማዕትነት ሞተች ።

ዘመነ ሰማዕታት በሚል በሚታወቀው 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ብዙ ቅዱሳት እናቶቻችን ስለ ፍቅረ ክርስቶስ አንገታቸውን ሰጥተዋል:: አንዳንዶቹ ደግሞ ሕይወታቸው እጅግ የሚያምር ነበር:: ከእነዚህ ቅዱሳት እናቶቻችን አንዷ ዛሬ የምናከብራት ሐጊያ ሶፊያ ናት::

በዚህ ስም ከሚጠሩት አንዷ ስትሆን በቀደመ ሕይወቷ ክርስቶስን አታውቅም ነበር:: ጣዖትን የሚያመልኩ ወላጆቿ አሳድገው አጋቧት:: ከትዳሯም 2 ቡሩካት ሴቶች ልጆች ወልዳለች:: ስማቸውም አክሶስናና በርናባ ይባላል:: ልጆቿ ልብ እያገኙ በሔዱ ጊዜ ቅድስት ሶፍያ ስለ እውነተኛው አምላክ ትመራመር ገባች::

በወቅቱ የነበሩ ብዙ ሃይማኖቶችን መዘነች:: ከክርስትና በቀር ግን ሌሎቹ ሚዛን እንደማይመቱም አስተዋለች:: "እውነኘተኛው አምላክ ሆይ! ምራኝ እርዳኝም" ስትል ጸለየች:: መድኃኔዓለም ለጠሩት አያሳፍርምና ፈጥኖ በጐውን ጐዳና አሳያት።

ድኅነት ለልጆቿም ይሆን ዘንድ ሁለቱንም ጠርታ ስለ ክርስትና አማከረቻቸው:: ደስ ብሏቸው ተቀበሏት:: እርሷም ጊዜ ሳታጠፋ ወደ ዻዻስ ሒዳ ማሕተመ ክርስትና: ሃብተ ውልድናን ትቀበል ዘንድ ከልጆቿ ጋር ተጠመቀች:: በቅድስናና ደስ በሚያሰኝ አኗኗርም እስከ መከራ ቀን ቆየች::

የመከራ ጊዜ ሲደርስም ልጆቿን ጠርታ "ስለ ክርስቶስ ፍቅር እንሙት" አለቻቸው:: ቡሩካቱ አክሶስናና በርናባም ደስ እያላቸው "እሺ" አሏት:: ወዲያውም በመኮንኑ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ከመካድና ከስቃይ ሞት የትኛውን እንደሚመርጡ ቢጠየቁ እነርሱ መሞትን መረጡ:: ወደ እሥር ቤትም ከተቷቸው::

ቅድስት ሶፍያ 2 ልጆቿ ይጸኑላት ዘንድ አዘውትራ ገድለ ሰማዕታትን እና ክብራቸውን ትተርክላቸው ነበር:: በተለይ የታላቁዋን አንጌቤናይት (እመቤት) ሶፍያንና የ3 ልጆቿን (ዺስጢስ: አላዺስና አጋዺስ) ተጋድሎ እየነገረች ታጸናቸው ነበር።

ከእሥር በኋላ ግርፋት ታዞባቸው እናት ራቁቷን ስትገረፍ መልአክ ወርዶ ሲጋርዳት ልጆች በማየታቸው ደስ አላቸው:: ቅድስት ሐጊያ ሶፍያና 2 ልጆቿ እጅግ የበዛ ስቃይን ስለ ቀናች እምነት ተቀበሉ:: ምላስ እስከ መቆረጥም ደረሱ:: በመጨረሻ ግን በዚህች ቀን ተገድለው አክሊለ ሰማዕታትን ገንዘብ አደረጉ

የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የሁሉን ቅዱሳን ቤት ሠርቶ የእርሷን በመዘንጋቱ ለራሱ ባሰራው ቤተ መንግስት ላይ ተአምር ታይቷል። ለ3 ያህል ጊዜ ስሙን ሲያስቀርጽ መልአክ እየወረደ ይፍቀው የሶፍያንም ስም ይጽፈው ነበር።

በመጨረሻም ንጉሡ ልጁን እስከ መገበር ደርሶ ቤተ መንግስቱ የቅድስት ሶፍያና የ2 ልጆቿ ቤተ ክርስቲያን ለመሆን በቅቷል:: ምንም ለ3 ጊዜያት ያህል ሙሉ እድሳት ቢደረግለትም ዛሬ አሕዛብ የያዙትን ይህንን ቅርስ ንጉሡ የሠራው ከ1700 ዓመታት በፊት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አሮን_መንክራዊ

በዚህች ቀን አቡነ አሮን መንክራዊ ዕረፍታቸው ነው፡፡ አቡነ አሮን ወላጅ አባታቸው የላስታው ጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ናቸው፡፡ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የላስታ ነገሥታት የዘር ሐረጋቸው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡

ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ ‹‹የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት›› ወይም ‹‹የላስታ መንግሥት›› በመባል ይታወቃል፡፡ የንጉሥ ሰሎሞን ዘር የሆነው መራ ክርስቶስ 3 ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም ጠንጠውድም፣ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ናቸው፡፡ ጠንጠውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፣ ገብረ መስቀልም አቡነ አሮንን ወለደ፣ ግርማ ስዩም ይምርሐነ ክርስቶስን ወለደ፣ ዣን ስዩም ደግሞ ገብረ ማርያምንና ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ ማርያምም ነዓኲቶ ለአብን ወለደ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሕዝብንም በቅድስናና በንጽሕና አገልግለው አልፈዋል፡፡

አቡነ አሮን ግን ገና በ7 ዓመታቸው ነው ዓለምን ፍጹም ንቀው በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እጅ የመነኮሱት፡፡ በ16 ዓመታቸውም ዋልድባ ገዳም ገብተዋል፡፡ ነሐሴ 5 ቀን ገና ሲወለዱ ሙት አስነሥተዋል፡፡ በሀገራችን እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሲሰብኩ የሸዋው ንጉሥ አንኮበር ድረስ ጠርቷቸው ሲሔዱ አዋሽ ወንዝ ሞልቶባቸው አገኙት፡፡ ሲሻገሩም ዳዊታቸውን ወስደባቸው፡፡ ‹‹ልጆቼን አመነኮስክብኝ›› በሚል ሰበብ ንጉሡ 7 ዓመት በግዞት አስሮ አስቀመጣቸው፡፡ ነገር ግን ከ7 ዓመት በኋላ አቡነ አሮን ተመልሰው በአዋሽ ወንዝ ሲመጡ መልአክ መጣና ‹‹መቋሚያህን ወደ ወንዙ ላክ›› አላቸው፡፡ መቋሚያቸውንም ቢልኩ ከ7 ዓመት በፊት ወደ ወንዙ ገብቶባቸው የነበረውን ዳዊታቸውን ይዘው አወጡ፡፡ ዳዊቱም በውኃው አልራሰም ነበር፣ ይልቁንም አቧራውን አራግፈው ፈጣሪያቸውን አመስግነው ዳዊታቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡ ያ ዳዊታቸው ዛሬም ድረስ በጋይንት አበርጉት ቅዱስ ሚካኤል ይገኛል፡፡

ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ውስጥ የሚገኘው እጅግ አስደናቂ ገዳማቸው ፍልፍል ዋሻ ሲሆን ጣራው ክፍት ነው፣ ክፍት በሆነው ጣራ በኩል ፀሐይ ሲገጣ ስለሚያቃጥል ጥላ ይይዛሉ ነገር ግን የጻድቁ ግዝት ስላለበት ዝናብ ወደ መቅደሱ ፈጽሞ አይገባም፡፡ እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ አቡነ አሮን በዋድላ ሜዳ አልፈው ሲሄዱ አንችም ሜዳ ላይ እንደ ኢያሱ ፀሐይን በቃላቸው ገዝተው አቁመዋታል፡፡

ከታች ጋይንት ተነሥተው መንገድ ሲሄዱ በሰንበት ቀን በሬ ጠምዶ ሲያርስ የነበረን ገበሬ ‹‹ለምን በሰንበት ታርሳለህ?›› ቢሉት ‹‹ምቀኛ መነኩሴ›› ብሎ በጅራፉ ቢገርፋቸው በሬዎቹ ግን ፈጽሞ አልንቀሳቀስ ብለው ቆመዋል፡፡ በዚህ የተናደደው ገበሬም አቡነ አሮንን መሬት ላይ ጥሎ ገረፋቸው፡፡ እሳቸውም ተነሥተው ሲሄዱ ዛፎች ተነቅለው እየተከተሏቸው፣ ቃልም አውጥተው በሰው አንደበት አመስግነዋቸዋል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ማማስ_በሰማዕት

በዚህችም ቀን ቅዱስ ማማስ በሰማዕትነት ሞተ የአባቱ ስም ቴዎዶስዮስ የእናቱም ያኖች ናቸው። በንጉሥ ዑልያኖስ ዘመንም ስለ ሃይማኖታቸው ይዘው አሠሩአቸው በእሥር ቤትም ሳሉ አረፉ።

አንዲት ክርስቲያናዊት ሴት መጥታ ይህን ሕፃን ወስዳ እንደ ልጅዋ አድርጋ አሳደገችው። ስሙንም ማማስ ብላ ሰየመችው ትርጓሜውም። የሙት ልጅ ማለት ነው አባትና እናት የለውምና።
@petroswepawulos
@petroswepawulos
@petroswepawulos
የመስከረም ፭ #ግጻዌ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ዘነግህ ምስባክ

‹‹ቡዙኀ ገብርከ እግዚኦ አምላኪየ መንክረከ። ወአልቦ ዘይመስሎ ለሕሊናከ። አይዳዕኩ ወነገርኩ ወበዝኀ እምኊልቊ።››

‹‹አቤቱ አምላኬ፥ ያደረግኸው ተአምራት ብዙ ነው፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ።››
🌻📖 መዝሙር ፴፱፥፭

የዕለቱ ምንባባት

🌻📖 ዮሐንስ ፩ ፥ ፲፭ - ፳፭
፲፭ ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፦ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።
፲፮ እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤
፲፯ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።
፲፰ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
፲፱ አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
፳ መሰከረም አልካደምም፤ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ።
፳፩ እንኪያስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም አለ። ነቢዩ ነህን? አይደለሁም ብሎ መለሰ።
፳፪ እንኪያስ፦ ማን ነህ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት።
፳፫ እርሱም፦ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ፦ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ።
፳፬-፳፭ የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩና፦ እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ፥ ስለ ምን ታጠምቃለህ? ብለው ጠየቁት።

🌻📖 ፩ኛ ጢሞቴዎስ ፭ ፥ ፩ - ፯
፩-፪ ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፥ እርሱን ግን እንደ አባት፥ ጎበዞችን እንደ ወንድሞች፥ የሸመገሉትን ሴቶች እንደ እናቶች፥ ቆነጃጅቱን እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና ለምናቸው።
፫ በእውነት ባልቴቶች የሆኑትን ባልቴቶች አክብር።
፬ ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ፥ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና።
፭ ብቻዋንም ኖራ በእውነት ባልቴት የምትሆን በእግዚአብሔር ተስፋ ታደርጋለች፥ ሌትና ቀንም በልመና በጸሎትም ጸንታ ትኖራለች፤
፮ ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት።
፯ ያለ ነቀፋ እንዲሆኑ ይህን ደግሞ እዘዝ።

🌻📖 ፩ኛ ጴጥሮስ ፫ ፥ ፭ - ፲
፭ እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፤
፮ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።
፯ እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።
፰ በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፥ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፥ እንደ ወንድሞች ተዋደዱ፥ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ፤
፱ ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።
፲ ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤

🌻📖 ሐዋርያት ፲፮ ፥ ፰ - ፲፮
፰ በሚስያም አጠገብ አልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።
፱ ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው፦ ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር።
፲ ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፥ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና።
፲፩ ከጢሮአዳም ተነሥተን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ በነገውም ወደ ናጱሌ በመርከብ ሄድን፤
፲፪ ከዚያም ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ እርስዋም የመቄዶንያ ከተማ ሆና የወረዳ ዋና ከተማና ቅኝ አገር ናት፤ በዚህችም ከተማ አንዳንድ ቀን እንቀመጥ ነበር።
፲፫ በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን።
፲፬ ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።
፲፭ እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።
፲፮ ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።
@petroswepawulos
@petroswepawulos
@petroswepawulos
ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት።››

‹‹የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።››
🌻📖 መዝሙር ፵፬፡፱


✝️የዕለቱ ወንጌል

🌻📖 ማቴዎስ ፲፫ ፥ ፴፩ - ፵፬
፴፩ ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤
፴፪ እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፥ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።
፴፫ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።
፴፬-፴፭ ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።
፴፮ በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፦ የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
፴፯ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
፴፰ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
፴፱ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
፵ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
፵፩ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
፵፪ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
፵፫ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
፵፬ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።
@petroswepawulos
@petroswepawulos
@petroswepawulos
አመታዊ እቅድ.docx 2016.docx
18.3 KB
shere አድርጉት ለሁላችንም ሚጠቅም እና ለራሳችን ልናደርገው ሚገባ ነው
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
✞የአምላክ ዐቃቤ ሕግ✞
.....
ገባሬ መንክራት በገድሉ ያወቅነው
የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው
ገብረ መንፈስ ቅዱስ
የአምላክ ዐቃቤ ሕግ
የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ

ፀሐይ ፀሐይ የምድራችን ፀሐይ
በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ
የመላዕክት ወዳጅ(፪)
ገብረሕይወት ሰማይ
አዝ= = = = =
መብረቅ መብረቅ ሰረገላው መብረቅ
የቃልኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ
የፍጥረቱ ደስታ (፪)
ገብረሕይወት ጻድቅ
አዝ= = = = =
ኮከብ ኮከብ ክብረ ገድላን ኮከብ
ዓለምን የሚያስንቅ መዐዛው የሚስብ
አርከ ሥሉስ ቅዱስ(፪)
ገብረሕይወት ኪሩብ
አዝ= = = = =
ስኂን ስኂን ፄና ልብሱ ስኂን
የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን
የሚነበብ መጽሐፍ(፪)
ገብረሕይወት ድርሳን
አዝ= = = = =
መቅረዝ መቅረዝ የማኅቶት መቅረዝ
ምድረከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ
የዝጊቲው ፈዋሽ(፪)
ገብረሕይወት ምርኩዝ

መዝሙር
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ ሲስተር ሕይወት ተፈሪ ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ሕይወት ወልዴ ዘውዱ ጌታቸው አዜብ ከበደ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በስድብ እና በዘለፋ የምንመልሰው ኃጢአተኛ አይኖርም አብዝተን በኃጢአቱ ስለወቀስነውም የምንታደገው ሰው የለም። እናስተውል ንሰሐ ለሁሉም የተሰጠች ናት። እግዚአብሔር እኛን ከነስንት ጉዳችን ተሸክሞን የለምን? ያየብንን ቢያሳይብን የሰማብንን ቢያሰማብን እንዴት ያለ ኃፍረት ውስጥ ገብተን ይሁን? ጌታችን አዳምንና ልጆቹን እንዴት እንዳዳናቸው እናውቃለን በቤተመንግስት ሲጠብቅ በበረት ተወለደ ተራበ ተጠማ ይህ ሁሉ ለማን የተደረገ ነው ለሰው ልጅ ሲባል አይደለምን። ጌታችን በምድር ሳለ ትልቁ መሣርያው ፍቅር ነበር ተንቀው ተጠልተው ከነበሩት ጋር መዓድ ተካፍሏል እንዴት እንዲ ካሉ ሰዎች ጋር ትቀመጣለህ ቢሉትም እሱ ግን እጅግ ኃጢአተኛ ለተባሉት ፍቅር ሰጥቶ አልፏል። ጥጦስን አስታወስከው ዘመኑን በሽፍታነትና በውንብድና የኖረ እግዚአብሔርን ያቃሉ ከሚባሉ ሰዎች ተርታ ማይመደበው ጥጦስ በመስቀል ላይ ሳለ በተናገራቸው አስደናቂ ቃላት ከአዳም ቀድሞ ገነት መግባቱን አስታውስ እኛ ወንበዴ ያልነውን እሱ ግን ማስተማርያ ያደርገዋል።የበደለውን ሰው በጥበብ አስተምረን መመለስ እንጂ አንግፉው ይበልጥ እግዚአብሔርን እንዲያውቅ እንርዳው እንጂ አምኖ የተናገረውን ኃጢአት ለስድብ አናድርገው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፍቅር የሰውን ልጅ መልሳ ሰው የምታደርግ መምህር ናት ማለቱን ማስታወሰ ይረባናል። የሐዋርያት የመጀመርያ ስብከት ፍቅር ናት አወሬ የተባሉትን የምታሰክን ድንቅ መንገድ።

ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
+ ከአንተ ባላውቅም ...+

በገነተ አበው (The Paradise of Fathers) መጽሐፍ ላይ ይህ ታሪክ ተጽፎአል::

አንድ መነኩሴ በበአቱ ቁጭ ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብ አንድ ቃል ሊገባው አልቻለም:: ለመረዳት በጣም ሲያስቸግረው "ይኼን ቃልስ እንዲገልጽልኝ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ አለብኝ" ብሎ ወሰነ:: ነቢያቱ ያደርጉት እንደነበረውም እግዚአብሔር የቃሉን ፍቺ እስኪገልጽለት ድረስ መጾምና መጸለይ ጀመረ:: ነገር ግን ለሰባ ሳምንታት ያህል እየጾመ ቢጠባበቅም ምንም ነገር ሊገለጽለት አልቻለም:: በየሳምንቱ መጨረሻ ቃሉን ደግሞ ሲያነበውም የበለጠ እየተወሳሰበበት ሔደ እንጂ ጨርሶ ሊገባው አልቻለም::

በመጨረሻም ተስፋ ቆረጠ:: ስለዚህ ሌላ መነኩሴ ጋር ሔዶ ስለዚህ ቃል ትርጉም ሊጠይቀው ወሰነ:: በአቱን ዘግቶ መንገድ ሊጀምር ሲዞር ግን የእግዚአብሔር መልአክ በፊቱ ቆሞ ታየው::

"አይዞህ አትፍራ የፈለግኸውን የቃሉን ትርጉም ልገልጽልህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬያለሁ" አለው::

መነኩሴው ግራ ገባው
"የጌታ መልአክ ሆይ ሰባ ሳምንት ሙሉ እየጾምሁ እንዲገልጥልኝ ስለምን ቆይቼ ምንም መልስ አላገኘሁም:: አሁን ተስፋ ስቆርጥ እግዚአብሔር ስለምን መለሰልኝ?" አለ በፍርሃት ውስጥ ሆኖ

"እግዚአብሔር ሰባ ሳምንታት ከጾምኸው ጾም ይልቅ ወንድምህን ለመጠየቅ በመሔድ ያሳየኸውን ትሕትና ተቀብሎታል" አለው::

አላዋቂ መስሎ መታየትን ያህል የምንፈራው ነገር የለም:: "አላውቀውም አንተ ንገረኝ" ከማለት ይልቅ ብዙ ሰው ሞት ይመርጣል:: ትንሽ ተምሬያለሁ የሚል ሰውማ ጥያቄ መጠየቅ ዲግሪውን ማቃጠል ይሆንበታል:: የብዙዎቻችን ትሕትና የሚፈቅድልን ሰዓት ለመጠየቅ ብቻ ነው:: "ከአንተ አላውቅም ..." ብለው የሚጀምሩ ዐረፍተ ነገሮች ራሱ ልብ ብለን ከሰማናቸው ይዘታቸው "ከእኔ አታውቅም" ነው::

የእውቀታችንን ውስንነት ለማመን የሚከብደን በሥጋችን ውስጥ ያለችው ለባዊት ነፍሳችን በሥጋዊ እውቀት ራስዋን መገደብ ስለምትቸገርም ነው:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "አሁን ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ" ብሎ የእውቀትን ውስንነት ማመን ግን ዕረፍት ይሠጣል:: 1ቆሮ. 13:12

በመንፈሳዊው ዓለም እንዲህ ሲሆን ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ እውነታ ነው:: "የቀለም ቀንድ" ፣ "የእውቀት ምንጭ" ፣ "መልስ በጉንጩ"፣ "ተጠያቂው" የሚለውን የክብር ሥፍራ ስንፈልግ በማናውቀው ጉዳይ ሌሎችን ከመጠየቅ ይከለክለናል:: አላውቀውም አላነበብኩትም አልሰማሁትም ከማለት ይልቅ ሁሉን አዋቂ ሆኖ ለመገኘት ስንል የምንበላቸው ዕፀ በለሶች ብዙ ናቸው::

"ብዙ የማውቀው ነበረ ሰዓት ገደበኝ እንጂ" ብሎ ውስን እውቀቱን ባሕር ለማድረግ የሚደክምና ሰዎች ከተናገረው ከጻፈው በላይ አድርገው እንዲያስቡት የሚገፋፋ ሰው የሚወለደው ካላዋቂነት ፍርሃት ውስጥ ነው:: በጥቂት ንባብ ውስጥ ራስን በጥልቅ ምሁር ዓይን ማየትና "እኔ የማውቀው ማወቄን ነው" ማለት የአላዋቂነት ፍርሃት የሚወልዳቸው ኢሶቅራጥሶች መርሕ ነው::

ከሌላው በታች አላዋቂ መስሎ መታየትን እንፈራለን:: ስለዚህ ሌላውን ከመጠየቅና እንደ ጃንደረባው "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" "ነቢዩ ይኼን ስለማን ተናግሮታል?" ብሎ ከመማር ይልቅ በራሳችን ለመረዳት ብንሟሟት እንመርጣለን:: ብዙ "የእምነት" denominations የተፈጠሩትም ሌላውን ከመጠየቅ ሞት በሚመርጡ ትዕቢተኞችና "እንደገባኝና እንደተረዳሁት" በሚል አስተሳሰባቸው እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል::

"ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር" ፊልጵ. 2:3

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
የሕይወት ውሃ ምንጭ 
                                                  
Size:- 36.6MB
Length:-1:45:05
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
መስከረም ሰባት በዚህች ቀን አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና ልደቷ ነው።

ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ('ጣ' ጠብቆ ይነበብ) ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት።

ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት። ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧት። (ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።)

ቅድስት ሐና ኢያቄምን አግብታ ስትኖር የቴክታና እና የጴጥሪቃ ምክነት በዘር ወርዶ መክና በመኖሯ የዐይኗ ማረፊያ የልቧ ተስፋ የሚሆን ልጅ እንዲስጣት ፈጣሪዋን ስትማጸን ኖራለች።

የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ አምላክ ልመናዋን ሰምቶ ሐምሌ ፴ ራእይ አየች። ራእዩንም ከባሏ ከኢያቄም ጋር ተወያየተው ምንጣፍ ለይተው ሱባኤ ገቡ።

ከአንድ ሱባኤ በኋላ ነሐሴ ፯ ቀን ጌታ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ እንደሚወልዱ አበሠራቸው። ከዚያም እመቤታችን ጸንሳ ልዩ ልዩ ተአምራትን አድርጋለች። ሳምናስን ከሞት አስነስታለች። በርሴባን ዐይኗን አብርታለች። ከዚያም በአይሁድ ተንኮልና አሳዳጅነት ወደ ሊባኖስ ተራራ ተሰዳ ድንግል ማርያምን ወልዳለች። በመውለዷም ሕዳሴ አካል አግኝታ ከኖረች በኋላ ዐርፋለች።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ቅድስት_ኤልሳቤጥ

በዚችም ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ እናት የከበረች ኤልሳቤጥ አረፈች። ቅድስት ኤልሳቤጥ ትውልዷ ከነገደ ሌዊ ነው:: ሐረገ ሙላዷም ከቅዱስ አሮን ካህን ወገን ይመዘዛል:: ከአሮን በቴክታና በጥሪቃ ወርዶ ሔርሜላ ላይ ይደርሳል::

ይህቺ ሔርሜላ የምትባል ደግ ሴት ማጣት ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) የሚባል የተባረከ ሰው አግብታ 3 ቡሩካት ልጆችን ወለደች:: የመጀመሪያዋን 'ማርያም' አሏት:: እርሷ ቅድስት ሰሎሜን ወለደች:: ሁለተኛዋን 'ሶፍያ' አሏት:: እርሷ ደግሞ ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች:: ሦስተኛዋ ግን የተለየች ናት:: 'ሐና' ብለው ሰየሟት:: እርሷም የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ወለደች:: በዚህም መሠረት ድንግል ማርያም: ቅድስት ኤልሳቤጥና ቅድስት ሰሎሜ የእህትማማች ልጆች ናቸው::

ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ጊዜ ስም አጠራሩ የከበረ: ደግ ካህን ለሆነ: ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት:: እነርሱም ልጅ አልነበራቸውም ነበርና በብስራተ መልአክ ቅድስት ኤልሳቤጥ 90 ካህኑ ዘካርያስ 100 ሳሉ መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁን ጸንሰች ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች::

ድንግል እመቤታችን የኤልሳቤጥን መጽነስ በሰማች ጊዜ ለሰላምታ ሄዳ ነበር። በዚያም ወቅት ቅድስት ኤልሳቤጥ መንፈስ ቅዱስ ስለ ሞላባት እመ ብርሃንን አመስግናታለች:: በማሕጸኗ ያለ የ6 ወር ጽንስም የእመ አምላክን ድምጽ ቢሰማ በደስታ ዘሏል:: ለፈጣሪውም ስግደተ-ስባሔ አቅርቧል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ አስፈጀ:: በዚህ ጊዜም እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ በልጅነቱ እዚያው በበርሃ እንዳለ በዚህች ቀን አርፋለች።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ_ሊቅ

በዚህችም ቀን የከበረና የተመሰገነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮስቆሮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አምስተኛ ነው።

ስለ ቀናች ሃይማኖትም ታላቅ ተጋድሎን ከተጋደለ በኋላ ዕረፍቱ በተሰደደበት በደሴተ ጋግራ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው ንጉሥ መርቅያኖስ ወደ ሰበሰበው ጉባኤ በጠሩት ጊዜ ሲደርስ ብዛታቸው ስደስት መቶ ሠላሳ ስድስት የሆነ ታላቅ ጉባኤን አየ። እንዲህም አለ ይህ ታላቅ ጉባኤ እስቲሰበሰብ ድረስ በሃይማኖት ላይ የተገኘው ጉድለት ምንድን ነው።

ይህ ጉባኤ የተሰበሰበው በንጉሥ ትእዛዝ ነው አሉት። እንዲህም አላቸው ይህ ጉባኤ ስለ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢሆን ኖሮ እኔ ተቀምጬ እግዚአብሔር በሰጠኝ በአንደበቴ እናገር ነበር ግን የዚህ ጉባኤ መሰብሰብ በንጉሥ ትእዛዝ ከሆነ የሰበሰበውን ጉባኤ ንጉሡ እንዳሻው ይምራ።

ከዚህም በኃላ አንዱን ክርስቶስን ከተዋሕዶ በኋላ ሁለት ባሕርይ ሁለት ምክር የሚያደርግ የክህደት ቃል በውስጡ የተጻፈበትን የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ልዮን የላከውን ደብዳቤ የከበረና የተመሰገነ ዲዮስቆሮስ ቀደደ።

በመንፈስ ቅዱስ የሚናገር የከበረ ዲዮስቆሮስም በጉባኤው ፊት እንዲህ ብሎ አስረዳ ሰው እንደመሆኑ ወደ ሠርግ ቤት የጠሩት ጌታችን ክርስቶስ አምላክ እንደመሆኑ ውኃውን ለውጦ ወይን ያደረገው ከሀሊ ስለሆነ ሰውነቱና መለኮቱ በሥራው ሁሉ የማይለይ አንድ ነው።

ደግሞ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቄርሎስ ከተናገረው የአካላዊ ቃል ተዋሕዶ እንደ ነፍስና ሥጋ እንደ እሳትና ብረት ተዋሕዶ ነው ያለውን ቃል ምስክር አድርጎ በማምጣትም አስረዳ። እሌህም የተለያዩ ሁለቱ ጠባዮች ስለ ተዋሕዷቸው አንድ ከሆኑ እንዲሁም የክብር ባለ ቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ አንድ መሲሕ አንድ ጌታ አንድ ባሕርይ አንድ ምክር ነው እንጂ ወደ ሁለት አይከፈልም አላቸው።

ከዚያም ከተሰበሰበው ጉባኤ ውስጥ ማንም ሊከራከረው የደፈረ የለም ከውስጣቸውም የእግዚአብሔር ጠላት ስለሆነው ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በኤፌሶን ጉባኤ አስቀድሞ ተሰብስበው የነበሩ አሉ።

ወደ ንጉሥ መርቅያኖስና ወደ ሚስቱ ንግሥት ብርክልያ ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከአባ ዲዮስቆሮስ በቀር ስለ ሃይማኖት ትእዛዛችሁን የሚቃወም የለም ብለው ነገር ሠሩበት።

ቅዱስ ዲዮስቆሮስንም ወደ ንጉሥ አቀረቡት ከእርሱም ጋር ታላላቅ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ከጉባኤው የሆኑ ነበሩ ከጥዋትም እስከማታ እርስበርሳቸው ሲከራከሩ ዋሉ። የከበረ ዲዮስቆሮስም የቀናች ሃይማኖቱን አልለወጠም ንጉሡና ንግሥቲቱ በእርሱ ተቆጥተው እንዲደበድቡት አዘዙ ስለዚህም ደበደቡት ጽሕሙን ነጩ ጥርሶቹንም ሰበሩ እንዲህም አደረጉበት።

ከዚህም በኃላ የተነጨውን ጽሕሙን ያወለቁትንም ጥሩሱን ሰብስቦ ወደ እስክንድርያ አገር ላካቸው እነሆ የቀናች ሃይማኖት ፍሬ ይህ ነው አላቸው። ለጉባኤውም የተሰበሰቡ ኤጲስቆጶሳት በዲዮስቆሮስ ላይ የደረሰውን መከራ በአዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ በእርሱ የደረሰ በእነርሱ ላይ እንዳይደርስ ስለዚህም ከመናፍቁ ንጉሥ ከመርቅያኖስ ጋር ተስማሙ። በሲኦል ውስጥ ይቆርጡት ዘንድ ባለው ምላሳቸውም ለክርስቶስ ሁለት የተለያዩ  ባሕርያት አሉት ብለው በንጉሡ መዝገብ ላይ በእጆቻቸው ጽፈው ፈረሙ። ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ተመልሶ ያን በውስጡ የጻፉበትን ደብዳቤ ያመጡለት ዘንድ ወደእሳቸው ላከ እነርሱም ላኩለት እነርሱ እንደጻፉ በውስጡ እርሱ የሚጽፍ መስሏቸዋልና።

እርሱ ግን አባቶቻችን ሐዋርያት ከአስተማርዋት ከቀናች ሃይማኖት በኒቅያ የተሰበሰቡ ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጲሳት አባቶቻችን  ከሠሩት ሕግ የሚወጣውን ሁሉ በደብዳቤው ግርጌ ጽፎ አወገዘ።

መና*ፍቁ ንጉሥም ተቆጥቶ ጋግራ ወደም ትባል ደሴት እንዲአግዙት አዘዘ ወደዚያም ወሰዱት።ከእርሱም ጋር የሀገረ ቃው ኤጲስቆጶስ አባ መቃርስ አብሮ ተሰደደ። ሌሎችም አራት መነኰሳት የሸሹ አሉ።

እሊህም ስድስት መቶ ሠላሳ ስድስት ኤጲስቆጶሳት ተቀምጠው በኬልቄዶን ለራሳቸው መመሪያ የሚሆናቸውን ሥርዓት ሠሩ።

የከበረ ዲዮስቆሮስንም በአጋዙት ጊዜ ከዚያች አገር ኤጲስቆጶስ ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት ኤጲስቆጶስ ንስጥሮሳዊ ስለሆነ ታላቅ ጉስቁልናንም አጎሳቁለው በእጆቹ ላይ ድንቆች ታላላቅ ተአምራቶችን እግዚአብሔር እስከገለጠ ድረስ።

የደሴቱም ሰዎች ሁሉ ሰገዱለት አከበሩት ከፍ ከፍም አደረጉት እግዚአብሔርም የመረጣቸውን በቦታው ሁሉ ያከብራቸዋልና።አባ ዲዮስቆሮስም አባ መቃርስን አንተ በእስክንድርያ አገር የሰማዕትነት አክሊልን ትቀበል ዘንድ አለህ አለው። ከዚህም በኃላ ከምእመናን ነጋዴዎች ጋር ወደ እስክንድርያ ላከው በእርሱ ላይ ትንቢት እንደተናገረ ገድሉን በዚያ ፈጸመ።

የከበረ አባት ዲዮስቅሮስ ግን መልካም ተጋድሎውን በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና እግዚአብሔርንም አገልግሎ ከዚች ኃላፊት ከሆነች ኑሮው ወጥቶ ሔደ የሃይማኖቱንም ዋጋ አክሊልን ተቀብሎ ወደ ዘላለም ዕረፍት ገባ ያረፈውም በዚያች በደሴተ ጋግራ ነው ሥጋውንም በዚያው አኖሩ።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
+++ ስለ ታሰሩ ሰዎች +++

አንዳንድ ነገሮች አሉ። እንዴት እንደምንጀምር እንጂ እንዴት እንደምናቆም ጨርሶ የማናውቃቸው። አጀማመሩን ስላወቅን እና ስለቀለለን ብቻ አቋቋሙም የዚያኑ ያህል ቀላል የሚመስለን። እውነታውስ? በነጻ ፈቃዳችን መርጠን እንጀምራለን። ነገር ግን ያ የተሳሳተውን ነገር መምረጥ በመቀጠላችን የመረጥነው እርሱን ያለመምረጥ ነጻነታችንን እስኪነጥቀንና ጌታ እስኪሆንብን እንደርሳለን።

በሱስ የተያዘ ሰው ከዚያ ነጻ ለመሆን ማናቸውንም ነገር ቢያደርግ ደስ ይለዋል። ግን ሱሱ ልማድ ሆኖበት አንቆ ይይዘዋል። በዚህ ከቀጠለ መጨረሻው ሞት እንደ ሆነ ቢያውቀውም፣ ራሱ በፈጠረው ነገር እንዲህ በመሰቃየቱ ምክንያት መልሶ ራሱን ቢጠላውም በእጁ የያዘውን የመጠጥ ብርጭቆ ግን ወርውሮ መስበር አይችልም። መላ ሰውነቱን ስለተቆጣጠረው እርሱ የጨበጠው ጠርሙስ እስረኛ ነው።

ይህን ግን ስለ መጠጥ ብቻ የምንናገር አይደለም። በጥቂቱ ብንጀምራቸውም በኋላ ግን አርቀን መጣል ያልቻልናቸው እና ሱስ ስለሆኑብንን ኃጢአቶች ሁሉ ይመለከታል።

እንዲህ በራሳችን ወህኒ ለታሰርን ምስኪኖች ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜ በቅዳሴዋ "እግዚአብሔር ከእስራታቸው ይፈታቸው ዘንድ ስለ ታሰሩ ሰዎች እንማልዳለን" ስትል ትማልዳለች። እኛም ከመዝሙረኛ ጋር "አቤቱ ስምህን አመሰግን ዘንድ፥ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት" እያልን ልንማጸነው ይገባል።(መዝ 142፥7) እኛ በራሳችን ላይ ያደረግነው የትኛውም ዓይነት እስራት የሲኦልን ደጆች ከሰባበረው የብረቱንም መወርወሪያ ከቆረጠው ከክርስቶስ ኃይል አይበልጥም። ስለዚህ ከፈቀድንለትና አብረነው ሠራተኛ ለመሆን ከወሰንን ዛሬም ከገባንበት ሲኦል ሊያወጣን የታመነ አምላክ ነው።

ሰው በራሱ ፍላጎት ብቻ ወደ ኃጢአት ጉድጓድ መግባት ቢችልም ያለ እግዚአብሔር ረድኤት ግን ከገባበት መውጣት አይችልም። ስለዚህ "እንዴት ከገባኹበት ጉድጓድ በራሴ መውጣት አልቻልኩም?!" እያልህ አትበሳጭ። ይልቅ ረድኤተ እግዚአብሔርን እየለመንህ በምትችለው ሁሉ ታገል።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ጸሎት ሰሚዋ ኩክ የለሽ ማርያም እና አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘብሔረ ቡልጋ

አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘብሔረ ቡልጋ የኩክ የለሽ ማርያም ገዳምን የመሰረቱ ሲሆን በመስከረም 23 ቀን 1908 በቡልጋ ወረዳ ተወለዱ፡፡እግዚአብሔር አምላክ በእርጅና ጊዜአቸው በ64 ዓመታቸው ለመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ ቤቱ የጠራቸው በአካለ ሥጋ በነበሩበት ጊዜም ነበር ከቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱሳን መላእክት ከጻድቃን ሰማዕታት ጋር ለመነጋገር የበቁ ታላቅ አባት ነበሩ፡፡
እግዚአብሔር ያከበረውን ማን ያዋርደዋል እንዳለ መጽሐፉ እኚህ ታላቅ አባት በሣርያ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሲያገለግሉ ቤተክርስቲያን ሲረዱ የቀዩ አባት ሲሆን ከዕለታት አንድ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ሲያከብሩ በዋዜማው ከቅዱስ ሚካኤል ጋር በመነጋገር የሥላሴን ዙፋን ገንትንና ሲኦልን ለማየት የበቁ አባት ናቸው፡፡


ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባ ኃይለ ጊዮርጊስ በእግዚአብሔር አጋዥነት በቅዱሳን መሪነት ገዳሙን የመሰረቱት ሲሆን ከድንጋይ ፍልፍል አራት / 4 / ቤተመቅደሶችንና ሌሎች የባህታውያን መኖሪያ ዋሻዎች የፈለፈሉ ሲሆን አብረዋቸው ቅዱሳን መላእክት እንደሚያግዟቸው በህይወት በነበሩበት ሰዓት ይናገሩ እንደነበር የገዳሙ አገልጋዮች ይናገራሉ፡፡አራቱ ቤተመቅደሶች፡-

1. የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ፍልፍል ዋሻ፡- ይህ ገዳም አባ ኃይለ ጊዮርጊስ በ1972 ዓ.ም ጀምረው በ1976 ዓ.ም ያጠናቀቁት ሲሆን ይህን ያህል ጊዜ ለምን እንደፈጀ የራሱ የሆነ ምክንያት አለውና በቦታው ተገኝተው ሚስጢሩን እንዲያውቁ ይመከራሉ

2. ኩክ የለሽ ማርያም ፍልፍል ዋሻ፡- በ1984 ዓ.ም ጀምረው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው ያጠናቀቁት፡፡ኩክ የለሽ ማርያም ማለት የጆሮ ኩክ የሌላት ቶሎ የሰዎችን ችግር የምትሰማ ለጠየቋትም ቶሎ ምላሽ የምትሰጥ እናት ማለት ነው፡፡ይህ ማለት ግን ሌሎች ቅዱሳን አይሰሙም ማለት አይደለም ፡፡ እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም አባ ኃይለ ጊዮርጊስ እጅግ አብዝታ ስለምትወዳቸው ኩክ የለሽ ማርያም ገዳምን እንዲመሰረቱ አድርጋቸዋለች፡፡ በጸበሏ በእምነቷ ብዙ ተዓምራቶችን እያደረገች ትገኛለች፡፡

3. የቅድስት ሥላሴ ፍልፍል ዋሻ፡- በ1984 ዓ.ም ጀምረው ከኩክ የለሽ ማርያም ፍልፍል ዋሻ ጋር አብሮ በአንድ ዓመት ውስጥ ነው የተጠናቀቀው ድንቅ ተዓምር እየተደረገበትም ይገኛል፡፡

4. ምን ያምር ቅዱስ ገብርኤል፡- በ1986 ዓ.ም ጀምረው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው ያጠናቀቁት፡፡ይህ ገዳም በቅዱስ ገብርኤል መሪነትና አጋዥነት በአባ ኃይለ ጊዮርጊስ ተፈለፈለ፡፡በዚህ ቤተመቅደስ ውስጥ ጸበል ፈልቆ ብዙ ተዓምራትን እያደረገ ይገኛል፡፡በአጠቃላይ በአራቱም ቤተመቅደስ በየዕለቱ ማዕጠንት ይታጠናል፡፡እንዲሁም በየወሩ ቅዳሴ ይቀደስባቸዋል፡፡ገዳሙ በ1972 ዓ.ም ተጀምሮ በ1986 ዓ.ም መጨረሻ ተጠናቆ በ1987 ዓ.ም በአባቶች ተባርኮ መነኮሳት በምነና ሕይወት ገብተዋል፡፡

እኚህ አባት ገዳሙን መስርተው ብዙ መንፈሳዊ አገልግሎት ካገለገሉ በኃላ በ1997 ዓ.ም መጋቢት 19 ቀን በዓለ እረፍታቸውን ካደረጉ በኃላ አጽማቸው በገዳሙ በጸሎት በአታቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ይህ ገዳም ከ25 በላይ መነኮሳት የሚኖሩበት ሲሆን በሽመናና በልማት ስራ ከጸሎት ጎን ለጎን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህን ታላቅ ገዳም የረገጠ ወንድ የ40 ቀን ህጻን ሴት የ80 ቀን ህጻን ይሆናል ተብሎ ቃል ኪዳን ተገብቶለታል እንዲሁም በቦታው የበረከት ሥራ የሰራ ጸሎት ያደረገ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ምሕረት እንደሚደረግለት ቃል ኪዳን ተገብቶለታል እርሶም በቦታው በመገኘት ለቦታው የተገባለትን ቃል ኪዳን ይሸምቱ።

ወስብሐት ለእግዚአብሐር
ምንጭ፡-ገዳሙ ያሳተመው ብሮሸር
አድራሻ፡- ደብረ ብርሃን በስተሰሜን ምስራቅ በኩል 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#መስከረም_8_ዘካርያስ_ይባላል

"ወናሁ አኀሥሥ ደመ እምእዴክሙ እምደመ አቤል ጻድቅ እስከ ደመ ዘካርያስ ወልደ በራክዩ ዘተቀትለ በማዕከለ ቤተ መቅደስ ወምሥዋዕ" ፦

(ከአቤል ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል አስከተገደለው እስከ በራክዩ ልጅ ዘካርያስ ድረስ የፈሰሰውን ደም ከእጃችሁ እፈልጋለሁ) ፤ ማቴ 23፡35፡፡

መስከረም 8 (ስምንት) የብቻው ተለይቶ "ዘካርያስ" ይባላል፤ የንጹሐን ካህናት ደም የፈሰሰበት መታሰቢያ ዕለት ነው፤ ያውም በሚያገለግሉበት በመሠዊያውና በመቅደሱ ደጃፍ በግፈኞች የተገደሉበት ።

ሁለት ዘካርያስ ተብለው የሚጠሩ ክህነትን ከትንቢት አስተባብረው የያዙ በተለያየ ጊዜ የተነሡ ሞታቸውና የደማቸው ጩኸት ተመሳሳይ የሆነ ፤ክርስቶስም ደማቸውን ከአይሁድ እጅ እንደሚፈልገው የተናገረላቸው ንጹሐን አበው ናቸው።
አንዱ በዜና መዋዕል ካልዕ ታሪኩ የተጻፈለት ሲሆን (2ኛ ዜና መዋ. 24፡21)፤
ሁለተኛው የዮሐንስ መጥምቅ አባት በሄሮድስ ክፋት በልጁ በቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመሠዊያው እንደታረደ አበው የሚነግሩን ታሪክ ነው።

ዘካርያስ ወልደ ዮዳሄን ሲገድሉት ላያዝኑለት ተነጋግረው ፤ ራርተው ላይተውት ተማምለው፤ ነፍሱ ሳትወጣ ላይለቁት ለሞቱ ቃል ኪዳን ገብተው ፤ ከታች ድንጋይ ከላይ ድንጋይ አድርገው በዐለት ላይ አጋድመው ቀጥቅጠው ነበር የገደሉት ፤ ይህን ያደረጉ ሰዎችም እሱን ሳይገድሉ እህል እንዳይቀምሱ ጭምርም ተማምለው ነበር፣ መሐላቸውን በቤተ መቅደሱ አደባባይ ያለ ማንም ከልካይ ፈጸሙበት፤ እሱም ሲሞት፣ ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት አንዲት ቃል አወጣ
"……እግዚአብሔር ይህንን ግፍ ይህንን ደም ይየው ይፈልገውም" (ዜና መዋ 24÷21)
በማለት የግፍ ሞት ጽዋውን ደም ገርገጭ አድርጎ ጠጣው!!!

በዚህም ምክንያት ደሙ ለብዙ ዓመታት ሲጮኽ እንደኖረ አበው ይነግሩናል።

ዛሬም እንደ ዘካርያስ በተወለዱበት ፤ ባደጉበትና ሀብት ንብረት ባፈሩበት ቀያቸው ተቀጥቅጠውና ታርደው የተገደሉ አባቶቻችን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ቁጥር ብዙ ነው!!!

የመግደል ኪዳን የሰይጣን መሐላ ያለ ማንም ከልካይ የተፈጸመባቸው ብዙ ናቸው!!!

ደማቸውም እስከ ሰማይ እየጮኸ ነው።
አገራችን የደም ምድር መሆኗ አዲስ አልሆን አለ …… ሞት ሲለመድ፤ መግደል ጀግንነት ሲሆን፤ ጩኸት አልደመጥ ሲል ....የግፍ ጽዋ መሙላት ምልክት ነው፡፡

"ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።"
(ማቴ 23 : 35) ብሎ ጌታችን የተናገረውም ዘካርያስ እግዚአብሔር እንዲያይለት በጠየቀው መሠረት ራሱ እግዚአብሔር ወልድ ፦
"……እፈልገዋለሁ" በማለት ማረጋገጡ ነው።

ዛሬም ቢሆን የንጹሐንን ደም የሚያፈሱ ግፈኞች የግፍ ጽዋቸውን ከእግዚአብሔር ይቀበላሉ ።

መስከረም ስምንትን (8)
• እንደ አቤል በየዋህነት የተገደሉትን አቤሎችንና
• እንደ ዘካርያስ በመቅደስና በአደባባይ የታረዱ ዘካርያሶች ካህናትን እያሰብን እናከብረዋለን።

እግዚአብሔር ሆይ ደማችንን ከገዳዮቻችን እጅ ፈልግ!!!

ኦ እግዚኦ ረስያ ለደምነ ማኅተመ ደመ ኵሎሙ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ!

❖ጌታ ሆይ አስከ ዛሬ የፈሰሰው ደማችንን የደማችን መፍሰስ ማብቂያ አድርግልን!!!!

ሀገራችንን ከረኀብና ከበሽታ ከእልቂት ይሠውርልን!

አሜን!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ - #መንፈሳዊው_መንገድ መጽሐፍ #አያሌው_ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
“አንድ ምንም እውቀቱና ልምዱ የሌለው ሰው ዝም ብሎ መሬት ስለ ቆፈረ ብቻ ወርቅ አያገኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምንም ረብሕና ጥቅም የሌለውን ድካም ያተርፋል እንጂ፡፡ ባስ ካለም የቆፈረው ጉድጓድ ተደርምሶበት ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚነበብና እንዴት መረዳት እንዳለበት ያለወቀ ሰውም ይህን ሰው ይመስላል፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
+ ዘኬዎስ አጭር ባይሆን +

ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::

እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው::

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው::

ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ::
እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው::
ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም::
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 23 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
1 ሰው ለ10 ሰው ሼር በማድረግ ቻሌንጁን ይቀላቀላሉ
#ድንግል_ማርያም_እኮ
1. እግዚአብሄርን ልጄ የምትል። ሉቃስ 2:48
2. አምላክን የወለደች። ማቴ. 1:18፣ ራእይ 12:5
3. በድንግልና የወለደች። ማቴ. 1:22፣ ኢሳ. 7:14
4. መልአክ የሰገደላት፤ ያከበራት። ሉቃስ 1:28
5. በድምጿ ከማህፀን ፅንስ ያዘለለች። ሉቃስ 1:41
6. እግዚአብሄር እናቴ የሚላት።
7. መላእክት የማይነኩትን፣ የማያዩትን፣ ፊቱ የማይቆሙትን የዳሰሰች፣ ያቀፈች፣ የወለደች፣ ጡቷን ያጠባች። ሉቃስ 2:3
8. ከልጁዋ እርገት በኅላ ያረገች። መሀሊይ 4:8
9. የአዳም እና ሄዋን እርግማን ያልደረሰባት። መዝ. 44/5:11 ፣ 45/6:4
10. በጌታችን ቀኝ የምትቆም። መዝ. 44/5:9
11. የትውልድ ሁሉ እናት የሆነች። መዝ. 86/7:5
12. ትውልድ ሁሉ ብፅይት የሚሏት። ሉቃስ 1:48
13. ሁሉንም አይነት ፀጋ የተሞላች። ሉቃስ 1:28
14. ከሴቶች ሁሉ ተለይታ ቡሩክት የሆነች። ሉቃስ 1:28
15. ቡሩክት የተባለች። ሉቃስ 1:45
16. የሰውን ችግር ቶሎ የምትረዳ። ዮሀንስ 2:3
17. ማህፀንሽ እና ጡቶችሽ የተባረኩ ናቸው የተባለላት። ሉቃስ 11:27
18. ፀሀይን የተጎናፀፈች፣ ጨረቃን ከእግሮቿ በታች የተጫማች፣ በእራሷ ላይ አስራ ሁለት የከዋክብት አክሊል ያላት። ራእይ 12:1
19. ዘንዶውም ያደረሰባት። ራእይ 12:13
20. ሁለት ትልልቅ የንስር ክንፍ የተሰጣት። ራእይ 12:14
21. የመላእክት እህት፣ የሰማእታት እናት የሆነች።
22. ለዘላለም ድንግል የሆነች። ሂዝቅኤል 44:1-3
23. የእግዚአብሄር ከተማ የተባለች። ኢሳ. 60:14
24. የእግዚአብሄር አብ ሙሽራ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ሆነች። መዝ. 131/2:14 ፣ ሉቃስ 1:41
25. በሀሳብ፣ በስጋ እና በነፍስ ፍፁም ድንግል የሆነች።
26. ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች።
27. በሰማያዊ ህብስት እና ፅዋ ያደገች።
28. በቤተ መቅደስ ያደገች። መዝ. 44/5:10
29. ሰው ሁሉ እናታችን ፅዮን የሚላት። መዝ. 86/7:5
30. በድምጿ መንፈስ ቅዱስ የሞላች። ሉቃስ 1:41
31. እግዚአብሄር በማህፀኗ ለማደር የመረጣት። መዝ. 131/2:12-13
32. በእለተ አርብ ልጁዋ የሰጠን እናታችን። ዮሀንስ 19:27
በዚህ ሁሉ የተመላች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ናት።
@yedingelsitota21
@yedingelsitota21
@yedingelsitota21
005
2024/09/24 08:27:22
Back to Top
HTML Embed Code: