Telegram Web Link
ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት፣ ብዙ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም፡፡ ነፍሳችን በኀጢአት እየተጨነቀች፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተጆቡና ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል? እንዲህ ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው፡፡

ክርስቶስ ከዚሁ ሥራ አውጥቶናል፡፡ ከሕፃንነት አዕምሮ ወደ ማወቅ አሸጋግሮናል፡፡ ከምድራውያን ለይቶ ከሰማያውያን ጋር ደባልቆናል፡፡ ስለዚህ “መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” እንደ ተባለ አፍአዊ ሳይኾን መንፈሳዊውን ብርሃን ልናበራ ይገባናል (ማቴ.5፡16)፤ በአዲሱ ዓመት፡፡ ይህም ብርሃን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያስገኝ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ! ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
እንደዚህ ያሉትን እወቋቸው 
                                                  
Size:- 27.8MB
Length:-1:19:49
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcrLibilery
@EotcrLibilery
@EotcrLibilery
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ዋዜማ ዘዓውደ ዓመት
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊

በ፩ ሃሌታ ብጹዕ አንተ ዮሐንስ፤ ዘሀለወከ ታእምር፤ ወተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር፤ ጸሊ በእንቲአነ፤ ውስተ ርእሰ ዓውደ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ፤ ባርከኒ፤ እንሣእ በረከተከ።

ምልጣን፦ውስተ ርእሰ ዓውደ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ፤ ባርከኒ፤ እንሣእ በረከተከ።

አመላለስ፦
ባርከኒ ባርከኒ/፪/
እንሣእ በረከተከ እንሣእ በረከተከ /፬/

በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
ይቤ ዮሐንስ ለልየ ርኢኩ፤ ወአነ ሰማዕቱ፤ አንሰ ኢየአምሮ፤ ዳዕሙ ከመ ያእምርዎ ፳ኤል አንሰ መጻእኩ።

እግዚአብሔር ነግሠ
ጸርሐ ዮሐንስ ወይቤ ድኅረ እምነቢያት እምቅድመ ምጽአተ ወልድ ቤዛ ኃጢአቶሙ አጥምቅ በማይ አንሰ ተፈኖኩ።

ምልጣን
ጸርሐ ዮሐንስ ወይቤ፤ ድኅረ እምነቢያት እምቅድመ ምጽአተ ወልድ ቤዛ ኃጢአቶሙ አጥምቅ በማይ፤ አንሰ ተፈኖኩ።

በ፭ እግዚኦ ጸራሕኩ ኀቤከ
እምከርሠ እሙ አእመረ ፤ እምከርሠ እሙ አእመረ ሰገደ ወአንፈርዓፀ።

ምልጣን
እምከርሠ እሙ አእመረ ሰገደ ወአንፈርዓፀ፤ ሰገደ ወአንፈርዓፀ፤ እምከርሠ እሙ አእመረ፤ ሰገደ ወአንፈርዓፀ።

ይትባረክ
ጸርሐት ቤተ ክርስቲያን ኀበ ዮሐንስ ወትቤሎ አንተኑ ክርስቶስ ወይቤላ አንሰ ኢኮንኩ ኪያሁ ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየዓትት ኃጢአተ ዓለም።

ምልጣን፦ነዋ በግዑ  ኃጢአተ ዓለም ዘየዓትት ነዋ በግዑ  ኃጢአተ ዓለም ዘየዓትት።

ሰላም
በ፬: ዘመጠነዝ ትርሢተ ክብር፤ ፈሪሃ ልዑል ትሕትና ወፍቅር፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ዘመላእክት ይሰግዱ ሎቱ፤ ኃይለ ልዑላን ኪያሁ ይሴብሑ፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ዘምስለ እግዚኡ ኪዳነ ዘአቀመ ወብዙኃነ አሕዛበ አእመነ፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ውስተ ሐቌሁ ቅናቱ ዘአዲም፤ ንብረቱ ገዳም ወኲሉ ነገሩ በሰላም፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ እግዚኡ ዘከመ ከለሎ፤ ዮም በምድር ተዝካሩ በሰማያት በላዕሉ፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ይቤሎ መድኃኒነ ለዮሐንስ፤ ዕውራን ይሬእዩ ወጽሙማን ይሰምዑ፤ እለ ለምጽ ይነጽሑ፤ እለ መጽኡ ኀቤየ።

ምልጣን፦ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ እግዚኡ ዘከመ ከለሎ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ዘመላእክት ይሰግዱ ሎቱ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ውስተ ሐቌሁ ቅናቱ ዓዲም ንብረቱ ገዳም ወነገሩኒ ሰላም።

አመላለስ፦
ውስተ ሐቌሁ ቅናቱ ዓዲም/፪/
ንብረቱ ገዳም ወነገሩኒ ሰላም/፬/
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ማኅሌት ዘዓውደ ዓመት
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ስርዓተ ነግሥ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለገበዋቲክሙ እለ ዕሩቃን እምልብሰ ወርቅ፤ ሥሉስ ቅዱስ ሥርግዋነ መፍርህ መብረቅ፤ መንገለ(ኀበ) ፍኖቱ ምጽዋት ለቆርነሌዎስ ጻድቅ፤ ይምርሐኒ ወንጌልክሙ እግዚአ ፍኖት ረቂቅ፤ ዘጸያሔሁ ዮሐንስ መጥምቅ።

ዚቅ
ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ፤ እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ።

ዓዲ
ወንጌል ቅዱስ ዘሰበከ ዮሐንስ፤ ቃለ ወልደ እግዚአብሔር።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኃደረ ላዕሌሃ፤ ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።

ነግሥ
ምስለ ራጉኤል ስዑል በነበልባል ወዮሐንስ ድንግል፤ ወበርተሎሜዎስ ሐዋርያ ሰባኬ ወንጌል፤ ወኢዮብ ዓዲ ተወካፌ ቊስል፤ ዓውደ ዓመት ለባርኮ እምጽርሐ አርያም ጌልጌል፤ ማርያም ንዒ ለምሕረት ወሣህል።

ወረብ
ዓውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዓውደ ዓመት/፪/
ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል/፪/

ዚቅ
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ዮሐንስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ።

ዓዲ
በምድረ ጽዮን ኢይኩን ሐከክ፤ ወበገራኅታ ኢይብቊል ሦክ፤ ጸሊ ኀበ አምላክ ራጉኤል መልአከ፤ ዓውደ ዓመት ከመ ይትባረክ።

መልክዐ ዮሐንስ
በስመ እግዚአብሔር እሳት በሐቅለ ኅሊና ነዳዲ፤ ወበስመ ማርያም ድንግል መጥበቢተ ዓለም አባዲ፤ ማኅቶተ ጸዳል ዮሐንስ ጽልመተ አበሳ ሰዳዲ፤ ከመ እዜኑ ኂሩተከ እደ ኃጣውእየ ይፍዲ፤ በአየረ ሰማይ ይጸርሕ ቃልከ ዓዋዲ።

ዚቅ
እገኒ ለከ እግዚኦ በኲሉ ልብየ፤ ወእዜኑ ኂሩተ ዚአከ፤ እትፌሣሕ ወእትሐሠይ በአድኅኖትከ።

ወረብ
እገኒ ለከ እግዚኦ በኲሉ ልብየ/፪/
እትፌሣሕ ወእትሐሠይ በአድኅኖትከ/፪/

ዓዲ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ማኅቶተ ጥበብ ውስተ አልባቢነ አኅቱ፤ ኀበ አዘዝከነ ኑፈር ወን

መልክዐ ዮሐንስ
ሰላም ለሥዕረተ ርእስከ እንተ ደለዎ እኳቴ፤ ወለርእስከ ሰላም ዘተመትረ ከመ ናቡቴ፤ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ፤ መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገረ ጽድቅከ ስቴ፤ ያስተፌሥሕ መላእክተ ወሰብአ መዋቴ።

ወረብ
"ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ"/፪/ ወላዴ መጥቅዕ/፪/
ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ ወላዴ መጥቅዕ/፪/

ዚቅ
ውስተ ርእሰ ዓውደ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ፤ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ።

መልክዐ ዮሐንስ
ሰላም ለአዕይንቲከ እለ ሠኑየ ይትኌለቁ፤ ወለአእዛኒከ ሰላም እለ ይትላጸቁ፤ ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ፤ እሳተ ነዳዴ ኢተክህሎሙ ያጥምቁ፤ ራጉኤል በትጋሁ ወኢዮብ በጽድቁ።

ወረብ
"እሳተ ነዳዴ" ኢተክህሎሙ ያጥምቁ/፪/
ዮሐንስ ከማከ ሶበ ፈተዉ ወጽሕቁ/፪/

ዚቅ
ሰላማዊ ብእሲሁ፤ ቅዱሳት እደዊሁ  እለ አጥመቃሁ፤ ለመድኃኔዓለም።

መልክዐ ዮሐንስ
ሰላም ለአማዑቲከ እግዚአብሔር ዘገብሮ፤ ወለንዋየ ውስጥከ ሰላም መንጦላዕተ ሥጋከ እንተ ሰወሮ፤ ዮሐንስ ልብው መዝገበ ጥበብ ወአእምሮ፤ እፎ ኢያጽራከ ለሀቅለ ገዳማት ፃዕሮ፤ ፍጹመ መኒነከ አብያተ ዘውቅሮ።

ወረብ
"አብያተ ዘውቅሮ"/፪/ መኒነከ/፪/
ፍጹመ መኒነከ ዮሐንስ ልብው/፪/

ዚቅ
አብያተ ዘውቅሮ መኒነከ፤ በተዘከሮ ማኅደር ዘበሰማያት፤ ፀጒረ ገመል ረሰይከ ዓራዘከ።

መልክዐ ዮሐንስ
አምኃ ስብሐት አቅረብኩ ለመልክዕከ በጽዋዔ፤ እንዘ አስተዋድድ ቃለ መጠነ ራብዕ ሱባኤ፤ ተወክፈኒ ዮሐንስ ምስለ በርተሎሜዎስ ቀርነ ጉባኤ፤ ከመ ተወክፈ እግዚእከ ቅድመ ወንጌላዊት ትንሣኤ፤ እምደ አሐቲ ብእሲት ጸራይቀ ክልዔ።

ዚቅ
ዮሐንስ እዴከ መጥወኒ፤ ወበርተሎሜዎስ አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ።

ወረብ
ዮሐንስ እዴከ መጥወኒ/፪/
ወበርተሎሜዎስ አቡየ ለባርኮ ቅረበኒ/፪/

አንገርጋሪ
ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ፤ ዓርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ፤ ወአዝማዱ በሥጋ ትሰመይ፤ ተፈኖከ ታርኁ አናቅጸ ጽድቅ።

አመላለስ፦
ተፈኖከ ታርኁ/፪/
ታርኁ አናቅጸ ጽድቅ/፬/

ወረብ
ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ነቢየ ልዑል/፪/
ዓርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ ነቢየ ልዑል/፪/

እስመ ለዓለም፦
በመንፈስ የሐውር ወበኃይለ ኤልያስ፤ አልቦ፤ዘየዓብዮ ለዮሐንስ

አመላለስ፦
አልቦ ዘየዓብዮ/፪/
አልቦ ዘየዓብዮ ለዮሐንስ/፬/
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
እንኳን አደረሳችሁ፡፡ አደረሰን፡፡

✿ለሁላችንም የሰላም ፡ የተፋቅሮ ፡ የበረከት እና የንስሃ ዘመንን አምላከ ቅዱሳን ይስጠን፡፡

✿ለዓለም ሰላምን ፡ ለአብያተ ክርስቲያናት ደህንነትን ፡ ለሃገራችንም በጎውን ዘመን ይስጥልን፡፡

✿እንደ ሰው አስበን ፡ እንደ ክርስቲያን መኖሩን ያድለን፡፡

✿ድሃ ተበደለ ፡ ፍርድ ተጓደለ የሚል መሪን አይንሳን፡፡

✿የአባቶቻችንን ዘመን ይመልስልን፡፡

✿የከርሞ ሰውም ይበለን ፡፡

✿ቸሩ እግዚአብሔር አይተወን፡፡ አይጣለንም፡፡

✿"የአንድ ገብስ እሸት፡፡
የአንድ ላምም ወተት፡፡"
ከተባለለት የተባረከው ዘመን ያድርሰን፡፡

✿የታመሙትን ፈውሶ፡፡
✿የወጡትን በሰላም መልሶ፡፡
✿ያለቀሱትን እንባቸውን አብሶ፡፡
✿የወደቁትን አንስቶ፡፡
✿በግፍ የታሰሩትን ፈትቶ፡፡
✿የሞቱትንም ነፍሳቸውን ይማርልን፡፡

ቸሩን ዘመን ይስጠን፡፡

✞ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በረድኤት አትለየን፡፡ ✞

አሜን፡፡


@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።”

(1ኛ ጴጥሮስ 4፥3)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#በዓለ_ርዕሰ_ዐውደ_ዓመት_ዮሐንስ_ወቅዱስ_ራጉኤል
#እንኳን_አደረሳቹ

#አዲስ_ዓመት

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የመሸጋገሪያው ዕለት በየዓመቱ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ የዘመን መለወጫ፣ እንቁጣጣሽ፣ ሌላም መጠሪያ ስሞቹ ናቸው፡፡ በግእዝ ርእሰ ዐውደ ዓመትም ይባላል፡፡ ይህ በዓል የዓመት መጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን በየዓመቱ ወሮች በመጀመሪያ ቀን ይከበራል፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል 12 ሰዓት ይሆናል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ሲቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ለዘመን መታወቂያው ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትንም ፈጠረ” ይላልና /ሔኖክ. 21፥49/፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ በፍል ውኃ አጥለቅልቆ በኃጢአት ሕይወት ይኖሩ የነበሩት የኖኅ ዘመን ሰዎች ቀጥቶ ካጠፋ በኋላ ከንፍር ውኃ ምድር የተገለጠችበት ወር ነው /ኩፋሌ. 7፥1/፡፡ “በመጀመሪያው ወር ምድር ታየች የንፍር ውኃም ከምድር ደረቀ” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት አድርገው የአቡሻኸር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስቀምጣሉ፡፡


የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናዊ ሥርዐት ያጠኑ ሊቃውንት ደግሞ አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን መሆኑን አስመልክተው በክታባቸው እንዳስቀመጡት በአራቱ ወንጌላውያን ዘመኑን ይከፍሉታል፡፡ ምክንያቱም በዘመነ ዮሐንስ ተፀንሶ በዘመነ ማቴዎስ ተወልዶአል፡፡ በዘመነ ማርቆስ ተጠምቋል፡፡ በዘመነ ሉቃስ ተሰቅሎ ዓለምን ከፍዳና ከመርገም ነጻ አውጥቷል፤ እያሉ ታሪካዊ ሐረጋቸውን ጠብቆ አራቱ ወንጌላውያን ተከትለው ያለ እንቅፋት እንደሚጓዙ ያስረዳሉ::

#እንቁጣጣሽ

ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሳባ የጠቢቡ ሰሎሞንን ዝና ሰምታ ኢየሩሳሌም ተጉዛ ስትመለስ “እንቁ ለጣትሽ /ለጣትሽ እንቁ/ በማለት ከእንቁ የተሠራ የጣት ቀለበት ንጉሥ ሰሎሞን እጅ መንሻ እንዲሆናት አበርክቶላት ነበርና ይህን ታሪክ መነሻ አድርገው “እንቁጣጣሽ” የሚለው ስያሜ ከዚያ እንደመጣ የታሪክ ድርሳናት ያስረዱናል ፡፡ በኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ዕለት ምድሪቱ በክረምቱ ዝናብ ረስርሳ ድርቀቷ ተወግዶ በአርንጓዴ እጸዋት ተውባ ሜዳው፣ ሸለቆውና ተራራው በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠው የሚታዩበት ወቅት በመሆኑ ዕለቱ “እንቁጣጣሽ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በዚህ ወቅት ሕፃናትና ልጃገረዶች ነጭ ባሕላዊ ልብስ በመልበስ ለምለም ቄጤማና አደይ አበባ በመያዝ በአካባቢያቸው በመዞር አዲስ ዘመን መበሠሩን “እንኳን አደረሳችሁ” በማለት በቸርነቱ ዓመታትን የሚያፈራርቀውን እግዚአብሔርን በዝማሬ ያመሰግናሉ፡፡

መልካም_አዲስ_ዓመት

#ራጉኤል ሊቀ መላእክት:-

ራጉኤል ማለት የብርሃናት አለቃ ማለት ነው። የብርሃናት አለቃ ሲባል ፀሐይን፣ ጨረቃን እና ከዋክብትን በማመላለስና ለሰው ልጆች፣ ለአዝርዕት፣ ለእንስሳት፣ ለአራዊት ሁሉ ብርሃንን የሚመግብ ነው ማለት ነው። አንድም ራጉኤል ማለት የሚበቀል ማለት ነው። የሚበቀል ነው ማለት በቀል የሚገባው ለጠላት ነው የሰው ልጅ ጠላት ደግሞ ዲያብሎስ ነው፤ ስለሆነም ቅዱስ ራጉኤል እግዚአብሔርን አምነው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው በፍርሐተ እግዚአብሔር አምልኮቱን ለሚፈጽሙ ሁሉ ጠላት ዲያብሎስን የሚያርቅላቸው ወደ እነርሱም ፈጥኖ በመድረስ የሚታደጋቸው ነው ማለት ነው። ሔኖክ 6:4፡፡ አንድም ራጉኤል ማለት የኃያላን ኃያል እግዚአብሔር ማለት ነው። የኃያላን ኃያል ያለው የእግዚአብሔርን ኃያልነት ከምድር ፍጥረታት ዘንድ ኃያል ከሚባሉት ሁሉ ሊገለጽ የማይችል ኃያልነቱን ለመግለጽ ኃያልነቱም ከ እስከ የሌለው መሆኑን ለመግለጽ የተቀመጠ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ኃያል የኃያላን ኃያል መሆኑን የሚገልጽ ትርጉም አለው።

አንድም ራጉኤል ማለት ጽኑ እግዚአብሔር ማለት ነው። የእግዚአብሔር አምላክን ጽኑነት ለማጉላት ሲል ጽኑ አለው። እግዚአብሔር የማይወላውል የማይዋዥቅ የማይከዳ ነው ለማለትም ሲል ይህ ስያሜ ተሰጠው። የእግዚአብሔርን ጽናት የሚያሳይ ትርጉም ያለው ስያሜ ነው። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ራጉኤል አገልግሎት እና ስልጣን፡- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዚህ ዓለም በ64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ ሥጋዋ ወደ ዕፀ ሕይወት ሲነጠቅ (ሲያርፍ) አብሮ ለሔደው እና ስጋዋን በእጣን ሲያጥን ለነበረው ለፍቁረ እግዚ ለቅዱስ ዮሐንስ ኅብስትን የመገበ መልአክ ነው።  በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ የሆነ በእግዚአብሔር ፊት ግሩም ያማረ ሥራው የሰመረ እስከዛሬ የሞት ወጥመድ ያልያዘው የሞት ጥላ ያላረፈበት ነብዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡

እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው። (ድርሳነ ራጉኤል ዘ ጥቅምት ገጽ 23) አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ለመተካት ዓለምን የመለወጥ ሥልጣን የተሰጠው ቅዱስ መልአክ ነው። ከእግዚአብሔር የጌትነቱ አዳራሽ ይገባና ይወጣ ዘንድ ስልጣን ያለው ከኪሩቤልና ከሱራፌል ጋር ከፈጣሪ የጌትነት ዙፋን ፊት የሚቆም ነው። ሎጥን ሚስቱንና ልጆቹን ከእሳተ ጎመራ ያዳነ የበለአምን እርግማን ወደ በረከት የለወጠ እርሱ ነው።  በቅዱስ ራጉኤል ስነ ሥዕል ላይ የምናየው ይህ ባለ አራት እራስ ንስር ከአርባእቱ ኪሩቤል አንዱ ገጸ ንስር ነው። የሥላሴን የጌትነት ዙፋን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳት ናቸው። የሚሸከሙት ሲባል ጫማ የሰውን ልጅ እንደሚሸከመው እንጂ ችለውትስ አይደለም። እነርሱም የሰው ገጽ፣ የእንስሳ ገጽ፣ የንስር ገጽ እና የአንበሳ ገጽ ያላቸው ናቸው። ይህንንም ነብዩ ሕዝቅኤል "ለእያንዳንዱ እንስሳትም የተለያዩ አራት ገጾች ነበሩት። ይህውም በስተቀኝ በኩል የእንስሳ መልክ፣ በስተ ግራ የላም ገጽ፣ በበስተ ኋላም የንስር ገጽ የሚመስሉ ነበሩ" ብሏል ሕዝ 1፡6-13፡፡ ከዚህ የምንገነዘበው ነገር ቢኖር አራት ገጽ ካላቸው ኪሩቤል መካከል አንዱ ንስር መሆኑን ነው። ቅዱስ ራጉኤል ደግሞ የእነዚህ ኪሩቤል አለቃቸው (የጌትነቱ ዙፋን ጠባቂ) በመሆኑ በዚህ ምክንያት ማለትም እነርሱ ዙፋኑን ተሸካሚ እርሱ ደግሞ አጠገባቸው መቆሙ መንበሩን ጠባቂ በመሆኑ በዚህ አይነት የአገልግሎት ድርሻ አብረው ሊሳሉ ችለዋል። ቅዱስ ያሬድም በድጓው "አርባእቱ እንስሳ አልቄንጥሩ እንደሚባለው ንስር ፊት ለፊት አይታዩም አንዱም በመራቸው ይሔዳሉ እነርሱም እያንዳንዳቸው አራት ገጽ ሲኖራቸው ሳያርፉና ሳይደክሙ የሚያመሰግኑ ናቸው" በማለት ጽፏል።
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
#እግዚአብሔር_የሚወዳችሁ_እናንተም_የምትወዱት_ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡

ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ይቀላቀሉ)
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
#ምትረተ_ርእሱ_ለቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ

• ከመስከረም 1 ጀምሮ እስከ መስከረም 7 ድረስ ያለው ወቅት(ሳምንቱ) ዮሐንስ ይባላል፡፡
• ዮሐንስ ማለት ጸጋ ወሀብት ፣ ርኅራኄ ወሣህል፤ ፍሥሐ ወሐሤት (ጸጋ ስጦታ፣ ምሕረትና ይቅርታ፤ ተድላና ደስታ ) ማለት ነው፡፡
• ሰባቱ ዕለታት የመንፈሳዊ ጸጋውና ሀብቱ ምሳሌዎች ናቸው፦ ክህነት፣ትንቢት፣ስብከት፣ ብህትውና፣ድንግልና፣ጻድቅነት፣ሰማዕትነት፡፡
• ዮሐንስ የተፀነሰውና የተወለደው፤ማስተማርም የጀመረው ከጌታ 6 ወራት ቀድሞ ነው፡፡
• በወቅቱ የነበረውን ማኅበረሰባዊ ወይም ሕዝባዊ ክፋትን እንዳይወርስ ሲባል ያደገው በምድረ በዳ ከአራዊት ጋር ነው ፣
• ከእግዚአብሔር ውጪ ሌላ እንዳይሰማ ሲባል እህት ወንድም አልነበረውም፤ እናት አባቱንም በሕፃንነቱ አጥቷል!
• ከአውሬ ጋር ማደጉ በዛ ዘመን ሰው ከአራዊት ይከፋ ነበር ማለት ነውን?....እንዲያማ ባይሆን ዮሐንስም ጌታም "የአራዊት ልጆች" የሚለውን ቃል ባልተጠቀሙም ነበር! ማቴ 3፡7፤ 12፡34፡፡፡፡

የተላከው በወቅቱ ለነበረው ማኅበረሰብእ ምልክት እንዲሆን ፤ ሕዝቡን ለጌታ እንዲያሰናዳ፣ የጻድቃንን መንገድ ለኃጥአን ለማስተማር ፤ የከዳተኞችን መንገድ ወደ ጻድቃን ጥበብ ለመመለስ ፤ የሱን ትውልድ ልብ ከአባቶቹ ልብ ጋር ለማገናኘት ፣ የተፈረካከሰውን ልበ አይሁድ ለጌታው ለማስመቸትና ለመጠገን ነበር ፤ ሉቃ 1፡14-17፡፡

• ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በተላከበት ዘመን አይሁድ ለስምንት ቡድን ተበጣጥሰው ነበር እነርሱም፦
1. ጸሐፍት
2. ፈሪሳውያን
3. መጸብሐን
4. ሊቃነ ካህናት
5. ረበናት
6. መገብተ ምኩራብ
7. ሰዱቃውያን
8. መላህቅተ ሕዝብ (እልመተዝእላን)
❖ይህ ሁሉ ቡድን ከዮሐንስና ከጌታ ሞት በስተቀር በምንም የማይስማማ ነበር! ይህም ለመጥፋታቸው ምልክት ነበር፡፡ " እርስ በእርስዋ የምትለያይ መንግሥት..." እንዳለ ጌታችን (ማቴ 12፡22)፡፡

• ማኅበረሰብእ ሊጠፋ ሲል የአባቶቹን መንገድና ወግ መርሳት ዋና ምልክት ነው፤ መለያየትም የሚፈጠረው ታሪክን በሚጠብቅና ታሪክን በሚያፈርስ ትውልድ መካከል ነው፤ ለመፍረስ የተፈረደበት ማኅበረሰብእ ነጋሪት እየተመታበት አይሰማም፤ ምልክት እያየ አያምንም፤ እንዲያውም እውነት የሚነግረውን ሰው አንገት ይቆርጣል።

• የአይሁድ ሀገርና ማኅበረሰብእ የዮሐንስን፤ የጌታንና የሐዋርያትን ትምህርት ባለመስማት ጠፍቷል፤ ይህንን መጥፋታቸውን በተመለከተ ጌታ እያለቀሰ ነግሯቸው ነበር! ሉቃ 19፡41፡፡፡

• ዛሬም ዮሐንሶች አሉ! እውነትን የሚገልጡ፤ ምልክት ሆነው የተሰጡ ፤ የትውልዱን ልብ ከአባቶች ልብ ጋር ለማገናኘት የተላኩ አሉ፤ እየተናገሩም ነው!

• ሄሮድሶችም አሉ! የእውነትን አንገት ለመቅላት ለአመንዝሮቹና ለዘፋኞቹ ቃል የገቡ ይህንኑም በታማኝነት የሚፈጽሙ ፤ ለሮማውያን የሚያሸረግዱ፤ ለአጥፊዎቹ ጥብቅና የቆሙ፣ እነ ዮሐንስ የሠሩትን የወንጌል ድልድይ ፤ የተስተካከለውን (ኦርቶዶክሳዊውን) መንገድ የሚያፈራርሱ ሄሮድሳውያን አሉ!

ነገር ግን የዮሐንስ አንገት እውነት ናት! በክንፍ እየበረረች ዓለምን ታስተምራለች፣ እውነት ሞትን የማሸነፍ ዓቅም አላት፣ሕያዊት ማለትም እውነት ናት ።

እውነታችን አትቀበርም፤ አትሸፈንምም! ሊያፍኗት በሚፈልጉት መጠን ትገለጣለች፤ ሊቀብሯት በሚፈልጉት መጠን ትንሣኤን ትሰብካለች፡፡

እውነተኞችን ማሰርና መግደል በሐዲስ ኪዳን በዮሐንስ መጥምቅ ተጀምሯል!

ዮሐንስ ሲታሰር ግን "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" የሚለው ቃል አልታሰረም፤ ጌታ ይህንኑ እያስተማረ ተገለጠ! (ማቴ 4፡17)

እኛ እስራኤል ዘነፍስ (ኦርቶዶክሳውያን) ይህንን ቃል እንስማ፤ ጥርጊያውና እናቅና፤ የጠመመውን እናቃና ፤ ታጋሾች እንሁን!......እንደማመጥ፤ እንሰማማ! ዮሐንስን እንስማው!!!

በረከተ ዮሐንስ መጥምቅ
ወበረከተ ዮሐንስ ወንጌላዊ ሥዩም በዝንቱ ዘመን
በሁላችን ላይ ይደርብን!

ሀገር የሆነችውን የቤተ ክርስቲያናችን ደግ ደጓን ያሰማን!!!!

አሜን!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥ ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ ይበለን።"

(መዝ. 90፥15

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ቅዱሳን አባቶቻችን ሁል ጊዜ ከወደቃችሁ በኋላ ወዲያውኑ መነሳትና ወደ እግዚአብሔር መመለስ አስፈላጊ ነው ይሉናል፡፡ ሁላችንም ያለማቋረጥ ኃጢአትን እንሠራለን፤ ተንሸራተንም እንወድቃለን፡፡ ምንም እንኳን በቀን መቶ ጊዜ ብንወድቅም ወደ ኋላ ዞር ብለን ሳናይ ተነስተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለብን የሆነው ሆኗል፤ ያ ጊዜም አልፏል፡፡ ከእግዚአብሔር እርዳታ እንጠይቅ፤ ተስፋችንን ከውስጣችን ሊያጠፋ ለሚፈልገው ዲያብሎስ፤ "እግዚአብሔር ከእኔ በላይ እኔን ይወደኛል ይቅርም ይለኛል" እንበለው፡፡

(አረጋዊ ታዴዎስ) @EotcLibilery @EotcLibilery @EotcLibilery
#ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ሆይ

"የብርሃኑ ጸዳል እጅግ በሚያበራ ዓምደ ብርሃን ለተቀረፀ ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ ክቡሩ አባት ሆይ በኃጢያት ድጥ ላይ ለመውደቅ የሚፍገመግሙትን በኃይል ክንድህ ፈጥነህ የምትደግፍ ነህና በዓለም ላይ መልካም ዝናን ለአተረፈው ስም አጠራርህ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች ግብፅም ትዘምራለች"

    መልክዐ ገብረመንፈስ ቅዱስ

ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሆይ ስምህን እየጠራን ዝክር ላደረግን ፀበልህን ለጠጣን እምነትህን ለተቀባን በተቀደሰዉ የመታሰቢያህ ቅዱስ ቦታህ በመገኘት ለተማጸንህና ለጸለይን ሁሉ ፈዉስንና ምሕረትን ስጠን
ከሰለጠነብን ጽኑ የሥጋ ይሁን የነፍስ ደዌ እንድንድን፣ ስለኃጥያታችን ፀፀትና መመለስን ስለ እዉነት በእውነት እንድንቆም የእግዚአብሔርን ፍቅር አዉቀን ትእዛዛቱን የምንፈጽምበት ጽናት ብርታት እንድናገኝ ስምህን እየጠራን እንማጸንሃለን !!!
             
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ጉባኤ_ሐዲስ_ኪዳን
(ለማስታወስ)
#ማቴ_8_ክፍል_አምስት
“በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።”
  — ማቴዎስ 8፥16-17
ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ።”
  — ማቴዎስ 8፥18
• ብዙዎች መሆናቸው ከነፍስ ኃጢአት የተነሣ ብዙዎች የአጋንንት ማደሪያ የነበሩ መሆናቸውን ያሳያል

• መላው የሰው ልጅ በእግረ አጋንንት እየተጠቀጠቀ የነበረ መሆኑን ለማመልከት
• የአጋንንትን በሰው ልጅ ላይ መሠልጠን ለማስረዳት
#መናፍስትን በቃሉ አወጣ፤ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ

• መናፍስትን በቃል ማስወጣት፡-
•  የማዘዝ ሥልጣንን የሚገልጽ ነው፤
•  በቃሉ ዓለማትን የፈጠረ መሆኑን የሚያስረዳ ነው ፤
• ምሥጢሩ፡- አካላዊ ቃል ወልድ ዲያብሎስን ድል አድርጎ እኛን ማዳኑን ያጠይቃል
• የታመሙትን መፈወስ፡- የታመሙ ማለት ስቃይ ያለባቸው ፤ ሌሊትም ቀንም በህመም ስሜት የሚሰቃዩ ማለት ነው፤ ከስቃያቸው እንዲያርፉ ከድካማቸው እንዲፈቱ ማድረጉን ያመለክታል፤
•  ምሥጢሩ ፡- ከስቃየ ሲኦል ከጻዕረ ሞት ከሙስና መቃብር ሊያድነን መምጣቱን ያስረዳል
ክፍል አምስት
• ‹‹ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ›› ማቴ 8፡18
• የከበቡት ሰዎች መልኩን ማየት የሚፈልጉ (እስመ መብዝኅተ ዓለም ዘይተልውዎ ለመድኅን ኮኑ ይፈቅዱ ይርአዩ ብርሃነ ዐቢየ ወስነ ብሩሀ ዘይወጽእ እምገጹ፤ ዮሐ.አፈ)፤ ተአምራት የሚፈልጉ ፤ ፈውስ የሚፈልጉ ናቸው
• ምሥጢሩ ፡- በትንቢት መነጽርነት የተመለከቱት ነቢያት በትንቢት በተስፋ በሱባዔ ከበቡት ማለት ነው
• አንድም አብነት የሚያደርጉት ሐዋርያት ፤ ሰማዕታት፤ ሊቃውንት መምህራን ፤ ምእመናን በአሚን/ በሃይማኖት ከበቡት ማለት ነው
መሻገር
• ጌርጌሴኖን የአጋንንት መንደር ነው፤ የመቃብር የሲኦል የገሃነም ምሳሌ ነው (28)
• ወደ ማዶ እንዲሻገሩ ማዘዙ የሰው ልጅ ከበደል በኋላ በሥጋ ወደ መቃብር ፤ በነፍስ ወደ ሲኦል ወደ ገሃነም እንዲወርድ ተፈርዶበት የነበረውን ያሳያል
• አርሱ በመርከብ ተሸግሮ ይፈውሳቸዋል፤ በሥጋ ማርያም ተገልጦ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ታሪካችንን መቀየሩን ያመለክታል ፤
• ወደ ማዶ መሻገር ማለት ነቢያት ዘመነ ክርስቶስን በሩቅ እንደተመለከቱት በእምነት እንደተሻገሩት የሚያሳይ ነው (እነርሱም በአካለ ነፍስ ሲኦል ወርደው ነበር)
• በሐዲስ ኪዳን ነፍሳት በመስቀል ትርክዛው ባሕረ እሳት እየተቀዘፈላቸው በዕለተ ዓርብ ከሲኦል ወጥተው ወደ ገነት እንደሚሻገሩ የሚያሳይ ነው (ማዕዶት የሚባለው ይህ ነው፤ ከጌርጌሶኖን )
• ሐዋርያት ፤ ሰማዕታት፤ ሊቃውንት ፤መነኮሳት፤ መምህራን፤ ምእመናን መከራውን በጥብዐት እንዲሻገሩት የሚያሳይ ነው

....ይቀጥላል
ይቆየን!

ሁላችንን ወደ ንስሐ ሕይወት ያሻግረን🙏

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
#መስከረም_5

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም አምስት በዚች ቀን #ቅድስት_ሶፊያ_ሰማዕት ከሁለት ልጆቿ ጋር በሰማዕትነት አረፈች፣ #አቡነ_አሮን_መንክራዊ እረፍት ነው፣ #ቅዱስ_ማማስ_ሰማዕት በሰማዕትነት አረፈ፣ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ #አፄ_ልብነ_ድንግል እረፍቱ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሶፊያ_ሰማዕት

መስከረም አምስት በዚች ቀን የከበረች ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ አክሶስናና በርናባ ከሚባሉት ጋር በሰማዕትነት ሞተች ።

ዘመነ ሰማዕታት በሚል በሚታወቀው 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ብዙ ቅዱሳት እናቶቻችን ስለ ፍቅረ ክርስቶስ አንገታቸውን ሰጥተዋል:: አንዳንዶቹ ደግሞ ሕይወታቸው እጅግ የሚያምር ነበር:: ከእነዚህ ቅዱሳት እናቶቻችን አንዷ ዛሬ የምናከብራት ሐጊያ ሶፊያ ናት::

በዚህ ስም ከሚጠሩት አንዷ ስትሆን በቀደመ ሕይወቷ ክርስቶስን አታውቅም ነበር:: ጣዖትን የሚያመልኩ ወላጆቿ አሳድገው አጋቧት:: ከትዳሯም 2 ቡሩካት ሴቶች ልጆች ወልዳለች:: ስማቸውም አክሶስናና በርናባ ይባላል:: ልጆቿ ልብ እያገኙ በሔዱ ጊዜ ቅድስት ሶፍያ ስለ እውነተኛው አምላክ ትመራመር ገባች::

በወቅቱ የነበሩ ብዙ ሃይማኖቶችን መዘነች:: ከክርስትና በቀር ግን ሌሎቹ ሚዛን እንደማይመቱም አስተዋለች:: "እውነኘተኛው አምላክ ሆይ! ምራኝ እርዳኝም" ስትል ጸለየች:: መድኃኔዓለም ለጠሩት አያሳፍርምና ፈጥኖ በጐውን ጐዳና አሳያት።

ድኅነት ለልጆቿም ይሆን ዘንድ ሁለቱንም ጠርታ ስለ ክርስትና አማከረቻቸው:: ደስ ብሏቸው ተቀበሏት:: እርሷም ጊዜ ሳታጠፋ ወደ ዻዻስ ሒዳ ማሕተመ ክርስትና: ሃብተ ውልድናን ትቀበል ዘንድ ከልጆቿ ጋር ተጠመቀች:: በቅድስናና ደስ በሚያሰኝ አኗኗርም እስከ መከራ ቀን ቆየች::

የመከራ ጊዜ ሲደርስም ልጆቿን ጠርታ "ስለ ክርስቶስ ፍቅር እንሙት" አለቻቸው:: ቡሩካቱ አክሶስናና በርናባም ደስ እያላቸው "እሺ" አሏት:: ወዲያውም በመኮንኑ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ከመካድና ከስቃይ ሞት የትኛውን እንደሚመርጡ ቢጠየቁ እነርሱ መሞትን መረጡ:: ወደ እሥር ቤትም ከተቷቸው::

ቅድስት ሶፍያ 2 ልጆቿ ይጸኑላት ዘንድ አዘውትራ ገድለ ሰማዕታትን እና ክብራቸውን ትተርክላቸው ነበር:: በተለይ የታላቁዋን አንጌቤናይት (እመቤት) ሶፍያንና የ3 ልጆቿን (ዺስጢስ: አላዺስና አጋዺስ) ተጋድሎ እየነገረች ታጸናቸው ነበር።

ከእሥር በኋላ ግርፋት ታዞባቸው እናት ራቁቷን ስትገረፍ መልአክ ወርዶ ሲጋርዳት ልጆች በማየታቸው ደስ አላቸው:: ቅድስት ሐጊያ ሶፍያና 2 ልጆቿ እጅግ የበዛ ስቃይን ስለ ቀናች እምነት ተቀበሉ:: ምላስ እስከ መቆረጥም ደረሱ:: በመጨረሻ ግን በዚህች ቀን ተገድለው አክሊለ ሰማዕታትን ገንዘብ አደረጉ

የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የሁሉን ቅዱሳን ቤት ሠርቶ የእርሷን በመዘንጋቱ ለራሱ ባሰራው ቤተ መንግስት ላይ ተአምር ታይቷል። ለ3 ያህል ጊዜ ስሙን ሲያስቀርጽ መልአክ እየወረደ ይፍቀው የሶፍያንም ስም ይጽፈው ነበር።

በመጨረሻም ንጉሡ ልጁን እስከ መገበር ደርሶ ቤተ መንግስቱ የቅድስት ሶፍያና የ2 ልጆቿ ቤተ ክርስቲያን ለመሆን በቅቷል:: ምንም ለ3 ጊዜያት ያህል ሙሉ እድሳት ቢደረግለትም ዛሬ አሕዛብ የያዙትን ይህንን ቅርስ ንጉሡ የሠራው ከ1700 ዓመታት በፊት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አሮን_መንክራዊ

በዚህች ቀን አቡነ አሮን መንክራዊ ዕረፍታቸው ነው፡፡ አቡነ አሮን ወላጅ አባታቸው የላስታው ጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ናቸው፡፡ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የላስታ ነገሥታት የዘር ሐረጋቸው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡

ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ ‹‹የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት›› ወይም ‹‹የላስታ መንግሥት›› በመባል ይታወቃል፡፡ የንጉሥ ሰሎሞን ዘር የሆነው መራ ክርስቶስ 3 ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም ጠንጠውድም፣ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ናቸው፡፡ ጠንጠውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፣ ገብረ መስቀልም አቡነ አሮንን ወለደ፣ ግርማ ስዩም ይምርሐነ ክርስቶስን ወለደ፣ ዣን ስዩም ደግሞ ገብረ ማርያምንና ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ ማርያምም ነዓኲቶ ለአብን ወለደ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሕዝብንም በቅድስናና በንጽሕና አገልግለው አልፈዋል፡፡

አቡነ አሮን ግን ገና በ7 ዓመታቸው ነው ዓለምን ፍጹም ንቀው በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እጅ የመነኮሱት፡፡ በ16 ዓመታቸውም ዋልድባ ገዳም ገብተዋል፡፡ ነሐሴ 5 ቀን ገና ሲወለዱ ሙት አስነሥተዋል፡፡ በሀገራችን እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሲሰብኩ የሸዋው ንጉሥ አንኮበር ድረስ ጠርቷቸው ሲሔዱ አዋሽ ወንዝ ሞልቶባቸው አገኙት፡፡ ሲሻገሩም ዳዊታቸውን ወስደባቸው፡፡ ‹‹ልጆቼን አመነኮስክብኝ›› በሚል ሰበብ ንጉሡ 7 ዓመት በግዞት አስሮ አስቀመጣቸው፡፡ ነገር ግን ከ7 ዓመት በኋላ አቡነ አሮን ተመልሰው በአዋሽ ወንዝ ሲመጡ መልአክ መጣና ‹‹መቋሚያህን ወደ ወንዙ ላክ›› አላቸው፡፡ መቋሚያቸውንም ቢልኩ ከ7 ዓመት በፊት ወደ ወንዙ ገብቶባቸው የነበረውን ዳዊታቸውን ይዘው አወጡ፡፡ ዳዊቱም በውኃው አልራሰም ነበር፣ ይልቁንም አቧራውን አራግፈው ፈጣሪያቸውን አመስግነው ዳዊታቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡ ያ ዳዊታቸው ዛሬም ድረስ በጋይንት አበርጉት ቅዱስ ሚካኤል ይገኛል፡፡

ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ውስጥ የሚገኘው እጅግ አስደናቂ ገዳማቸው ፍልፍል ዋሻ ሲሆን ጣራው ክፍት ነው፣ ክፍት በሆነው ጣራ በኩል ፀሐይ ሲገጣ ስለሚያቃጥል ጥላ ይይዛሉ ነገር ግን የጻድቁ ግዝት ስላለበት ዝናብ ወደ መቅደሱ ፈጽሞ አይገባም፡፡ እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ አቡነ አሮን በዋድላ ሜዳ አልፈው ሲሄዱ አንችም ሜዳ ላይ እንደ ኢያሱ ፀሐይን በቃላቸው ገዝተው አቁመዋታል፡፡

ከታች ጋይንት ተነሥተው መንገድ ሲሄዱ በሰንበት ቀን በሬ ጠምዶ ሲያርስ የነበረን ገበሬ ‹‹ለምን በሰንበት ታርሳለህ?›› ቢሉት ‹‹ምቀኛ መነኩሴ›› ብሎ በጅራፉ ቢገርፋቸው በሬዎቹ ግን ፈጽሞ አልንቀሳቀስ ብለው ቆመዋል፡፡ በዚህ የተናደደው ገበሬም አቡነ አሮንን መሬት ላይ ጥሎ ገረፋቸው፡፡ እሳቸውም ተነሥተው ሲሄዱ ዛፎች ተነቅለው እየተከተሏቸው፣ ቃልም አውጥተው በሰው አንደበት አመስግነዋቸዋል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ማማስ_በሰማዕት

በዚህችም ቀን ቅዱስ ማማስ በሰማዕትነት ሞተ የአባቱ ስም ቴዎዶስዮስ የእናቱም ያኖች ናቸው። በንጉሥ ዑልያኖስ ዘመንም ስለ ሃይማኖታቸው ይዘው አሠሩአቸው በእሥር ቤትም ሳሉ አረፉ።

አንዲት ክርስቲያናዊት ሴት መጥታ ይህን ሕፃን ወስዳ እንደ ልጅዋ አድርጋ አሳደገችው። ስሙንም ማማስ ብላ ሰየመችው ትርጓሜውም። የሙት ልጅ ማለት ነው አባትና እናት የለውምና።
@petroswepawulos
@petroswepawulos
@petroswepawulos
የመስከረም ፭ #ግጻዌ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻

ዘነግህ ምስባክ

‹‹ቡዙኀ ገብርከ እግዚኦ አምላኪየ መንክረከ። ወአልቦ ዘይመስሎ ለሕሊናከ። አይዳዕኩ ወነገርኩ ወበዝኀ እምኊልቊ።››

‹‹አቤቱ አምላኬ፥ ያደረግኸው ተአምራት ብዙ ነው፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ።››
🌻📖 መዝሙር ፴፱፥፭

የዕለቱ ምንባባት

🌻📖 ዮሐንስ ፩ ፥ ፲፭ - ፳፭
፲፭ ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ እንዲህም ብሎ ጮኸ፦ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል፤ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነበረ።
፲፮ እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤
፲፯ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ።
፲፰ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
፲፱ አይሁድም፦ አንተ ማን ነህ? ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።
፳ መሰከረም አልካደምም፤ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ።
፳፩ እንኪያስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም አለ። ነቢዩ ነህን? አይደለሁም ብሎ መለሰ።
፳፪ እንኪያስ፦ ማን ነህ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት።
፳፫ እርሱም፦ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ፦ የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ።
፳፬-፳፭ የተላኩትም ከፈሪሳውያን ነበሩና፦ እንኪያስ አንተ ክርስቶስ ወይም ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካይደለህ፥ ስለ ምን ታጠምቃለህ? ብለው ጠየቁት።

🌻📖 ፩ኛ ጢሞቴዎስ ፭ ፥ ፩ - ፯
፩-፪ ሽማግሌ የሆነውን አትገሥጸው፥ እርሱን ግን እንደ አባት፥ ጎበዞችን እንደ ወንድሞች፥ የሸመገሉትን ሴቶች እንደ እናቶች፥ ቆነጃጅቱን እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና ለምናቸው።
፫ በእውነት ባልቴቶች የሆኑትን ባልቴቶች አክብር።
፬ ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ፥ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና።
፭ ብቻዋንም ኖራ በእውነት ባልቴት የምትሆን በእግዚአብሔር ተስፋ ታደርጋለች፥ ሌትና ቀንም በልመና በጸሎትም ጸንታ ትኖራለች፤
፮ ቅምጥሊቱ ግን በሕይወትዋ ሳለች የሞተች ናት።
፯ ያለ ነቀፋ እንዲሆኑ ይህን ደግሞ እዘዝ።

🌻📖 ፩ኛ ጴጥሮስ ፫ ፥ ፭ - ፲
፭ እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ ለባሎቻቸው ሲገዙ ተሸልመው ነበርና፤
፮ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ።
፯ እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።
፰ በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፥ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፥ እንደ ወንድሞች ተዋደዱ፥ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ፤
፱ ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።
፲ ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤

🌻📖 ሐዋርያት ፲፮ ፥ ፰ - ፲፮
፰ በሚስያም አጠገብ አልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።
፱ ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው፦ ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር።
፲ ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፥ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና።
፲፩ ከጢሮአዳም ተነሥተን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ በነገውም ወደ ናጱሌ በመርከብ ሄድን፤
፲፪ ከዚያም ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ እርስዋም የመቄዶንያ ከተማ ሆና የወረዳ ዋና ከተማና ቅኝ አገር ናት፤ በዚህችም ከተማ አንዳንድ ቀን እንቀመጥ ነበር።
፲፫ በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን።
፲፬ ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ የሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።
፲፭ እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።
፲፮ ወደ ጸሎት ስፍራም ስንሄድ፥ የምዋርተኝነት መንፈስ የነበረባት ለጌቶችዋም እየጠነቈለች ብዙ ትርፍ ታመጣ የነበረች አንዲት ገረድ አገኘችን።
@petroswepawulos
@petroswepawulos
@petroswepawulos
ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹አዋልደ ንግሥት ለክብርከ። ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት።››

‹‹የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።››
🌻📖 መዝሙር ፵፬፡፱


✝️የዕለቱ ወንጌል

🌻📖 ማቴዎስ ፲፫ ፥ ፴፩ - ፵፬
፴፩ ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሰው ወስዶ በእርሻው የዘራትን የሰናፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፤
፴፪ እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፥ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።
፴፫ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።
፴፬-፴፭ ኢየሱስም ለሕዝቡ ይህን ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፤ በነቢዩም፦ በምሳሌ አፌን እከፍታለሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውንም እናገራለሁ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ያለ ምሳሌ አልተናገራቸውም።
፴፮ በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው፦ የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
፴፯ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
፴፰ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
፴፱ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
፵ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
፵፩ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
፵፪ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
፵፫ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
፵፬ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።
@petroswepawulos
@petroswepawulos
@petroswepawulos
2024/09/23 10:18:48
Back to Top
HTML Embed Code: