Telegram Web Link
👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉​​ ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ይቀላቀሉ
Channel link
@tewahdo_haymanotea
#በቤተክርስቲያን #ያሉ #ነገሮች #ምሳሌዎቻቸው

፩) ቤተክርስቲያን____የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ
፪) መቅደስ____የቀራንዮ ምሳሌ
፫) ታቦት፣መንበር___የእመቤታችን ምሳሌ
፬) ኵስኵስት_የእመቤታችን ምሳሌ
፭) ማይ_የማይ ሕይወት ክርስቶስ
፮) መሠረቱ__ከአዳም እስከ ኖኅ ያሉ የአስሩ አበው ምሳሌ

፯) ሦስት ደጃፍ____የሥላሴ ምሳሌ
፰) ትልልቅ መስኮቶች___የዐበይት ነቢያት ምሳሌ
፱) ትንንሽ መስኮቶች____የደቂቀ ነቢያት ምሳሌ
፲) የውስጥ አዕማድ_የሐዋርያት ምሳሌ
፲፩) የውጭ አእማድ_የ፸፪ቱ አርድእት ምሳሌ
፲፪) ፬ ማዕዘን__የአራቱ ወንጌላውያን፣ የኪሩቤል ምሳሌ

፲፫) መብራት_የሊቃውንት ምሳሌ
፲፬) በሮች____የቅዱሳን አበው ምሳሌ
፲፭) ጠርብ___የሰማእታት ምሳሌ
፲፮) ማገር___የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ
፲፯) ሣሩ_ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ምሳሌ
፲፰) መጋረጃ_የመላእክት፣የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ

፲፱) የሰጎን እንቁላል___የተዘክሮተ እግዚአብሔር ምሳሌ

፳) አፀደ ቤተክርስቲያን፣ ቅጽረ ቤተክርስቲያን__የመላእክት ምሳሌ

፳፩) ደጀሰላም___የገነት ምሳሌ
፳፪) ሁለቱ ቅጽር__አንዱ የናጌብ አንዱ የአድማስ ምሳሌ ናቸው። ሁለት ቅጽር ማለት እንደ ጎንደር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን እንደ አዲስ አበባ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሁለት ቅጽር ያለው ቤተክርስቲያንን ያመለክታል።

ምንጭ:- ፲፬ቱ መጽሐፈ ቅዳሴ አንድምታ ትርጓሜ

በቴሌግራም @EotcLibilery ይከታተሉን
ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ  ፳፭ /፳፻፲፭ ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  እንዲገኙ  የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ።

ኢኦተቤ ቴቪ  ሐምሌ ፳፪/፳፻፲፭  ዓ/ም

በትግራይ ክልል በአክሱም  ርእሰ አድባራት ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ ፲፮/፳፻፲፭ ዓ/ም  የተፈጸመውን  ኢ ቀኖናዊና ሕገወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት አስመልክቶ ለመምከር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለሐምሌ ፳፭/፳፻፲፭ዓ/ም  መጠራቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያናችን የገጠማት ፈተና  ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መሠረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ምክክር እንዲደረግበት የተጠራ  አስቸኳይ  ምልዓተ ጉባኤ  መኖሩ ቢታወቅም አንዳንድ ብፁዓን አባቶች ግን ከወዲሁ  በተለያየ ምክንያት እንደማይካፈሉ እየገለጹ ይገኛሉ።

ስለሆነም ከአቅም በላይ ያጋጠመ ችግር ቢኖርም እንኳ  ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉዳይ የሚበልጥ ባለመኖሩና   የቤተ ክርስቲያን ቀኖናና አንድነት በከፍተኛ ደረጃ ሲፈተን እያዩ በጉባኤው  አለመገኘት የተጠሩለት የቤተ ክርስቲያን እውነትን የመጠበቅ ተልእኮ እንደመግፋት ስለሚያስመስል  በሀገር ውስጥና በሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት የምትገኙ  ብፁዓን አባቶች በተጠራው ቀን በጉባኤ እንድትገኙ በድጋሜ ጥሪ እናስተላልፋለን ብሏል።

በመሆኑም  በተጠራው ምልዓተ ጉባኤ  የማይገኙ  አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በእነሱ ላይ የሚወስነውን  ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል በማለት   የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

መረጃውን ያደረሰን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ነው።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ሱባዔ_እንዴት_እንግባ?


1.ሱባዔ መያዝ ስለፈለግንበት ጉዳይ ማሰብ እና መለየት፡- ዓላማ የሌለን ዝርው የሆነ ያልተሰበሰበ አእምሮ ይዘን እንዳንገባ ፤ ከቅዱሳን በረከት ለመሳተፍ፤ወይም የግል ሕይወት ጉዳይ፡- ሥራ፣ትምህርት፤ትዳር…የሀገርና የቤተ ክርስቲያን የመሳሰሉትን ጉዳዮች ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡

2. ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ስለ ሱባዔ በደንብ ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል፡- መጀመሪያ ከንስሐ አባቶቻችን ጋር መመካከር፤ ቀጥሎም ስለ ሱባዔ ከሚያውቁ መንፈሳውያን አባቶች መጠየቅ ያስፈልጋል፤ ብዙዎችን ሱባዔ ማለት ቀልድ የሚመስላቸው ዝምም ብለው የሚጀምሩት ጉዳይ ሆኗል፤ በዚህም ምክንያት የብዙዎች ሕይወት የሰይጣን መጫወቻ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡

3.ስለምንቆይባቸው የቀናት ብዛት በሚገባ በማሰብ መወሰን፡ -ሱባዔ ማለት ቀጥታ ትርጉሙ ሰባት ማለት ይሁን እንጂ የግድ ግን ሰባት ቀን ወይም ሰባት ዓመት መኖር ማለት አይደለም፤ ይህ ለተሰጣቸውና ከዓለም ሙሉ ሕይወታቸውን ላገለሉ ሰዎች እንጂ ለዓለማውያን የተሰጠ አይደለም፤ ሃያ አራት ሰዓት ወይም 48 ሰዓት ወይም ደግሞ 72 ሰዓት (ሦስት ቀናት) ሊሆን ይችላል፤ ከዚህ ጀምሮ እንደየዓቅማችን 7፣14፣21….ቀናት እያልን ልናሳድገው እንችላለን፡፡ ይህም የሚጠቅመን ምናልባት ባለማወቅ ከጀመርነው በኋላ ፈተናው ሲፀናብን እንዳናቋርጥና ከእግዚአብሔር ጋር እንዳንጣላ ነው፤ይህንንም ጌታችን በምሳሌ እንዲህ ሲል አስተምሮናል "ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ኪሳራውን የማይቆጥር ማነው? ያለዚያ መሠረቱን ቢመሠርት ሊደመድመውም ቢያቅተው ያዩት ሁሉ፡-ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ" (ሉቃ 14፡28-30) በማለት አጋንንት፤ የመናፍቃን መሳለቂያ እንዳንሆን ያስጠነቅቀናል፡፡

4. የምንጸልያቸውን ጸሎቶች መለየት፡- በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ብዙ ዓይነት ጸሎት መኖሩ ይታወቃል፤ሁሉንም እንጸልያለን ብንል ዓይናችን ይፈዛል አንደበታችን ይላሻል፤ ስለዚህም በየሰዓቱና በየዕለቱ የምንጸልያቸውን ጸሎቶች በመለየት ሳናስታጉል በትጋት መጸለይ አለብን፤ በጸሎት ጊዜም ሰጊድ(ስግደት)፤አስተብርኮ(መንበርከክ)፤ አንቃዕድዎ(ማንጋጠጥ) ከእንባ ጋር መረሳት የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው፤ እነዚህንም ያስተማረን ራሱ ጌታችን መሆኑን ልብ ይሏል! ማቴ 26፡39፤ሉቃ 22፡42፤ዮሐ 11፡41፡፡

5.የምንመገባቸውን የምግብ ዓይነቶች ለይቶ መወሰንና እናም የመመገቢያ ሰዓትን ማወቅ፡- ምግብ መጠጥ ኃጢአት ምንጮች ናቸው፤ በተለይም አብዝቶ መመገብ ልዩ ልዩ ዓለማዊ ነገሮችን እንድናስብ ከማድረጉ በተጨማሪ እንዳንጸልይና እንዳንሰግድ በማድረግ ይጫነናል፤ ስለዚህ የምንመገበው ለቁመተ ሥጋ ያህል ብቻ እና በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ብቻ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆኑን ሠለስቱ ደቂቅ እና ነቢዩ ዳንኤል ናቸው፤ዳን 21 ቀናት) ሳዝን ነበርኩ ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም" (ዳን 10፡2-4)፡፡

6. ለሱባዔ በወሰንባቸው ጊዜያት ከማንኛውም ዓለማዊ ጉዳይ ጋር ያለንን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ለማቋረጥ መወሰን፡- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥርዓተ ጸሎትን ሲያስተምረን "አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በሥውር ላለው አባትህ ጸልይ በሥውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል“ (ማቴ 6፡6) ብሎ እንደነገረን በሱባዔ ጊዜ መገናኘት ያለብን ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ነው፤ ማንኛውም ጉዳያችን እና ማንነታችንም ሳይቀር በእርሱ እጅ መውደቅ አለበት፡፡

የልብ ሱባዔ እኖዲሆን የልብ ጸሎት እንድንጸልይ እግዚአብሔር ይርዳን!!!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
✝️ ያልተቋረጠ የክህነት ቅብብሎሽ✝️
፩) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
፪) ቅዱስ ማርቆስ
፫) አናንዮስ
፬) መልዮስ
፭) ካርዳኖስ
፮) ፐሪሙስ
፯) ዮስጦስ
፰) ኦማንየስ
፱) ማርያኒስ
፲) ክላንድንያስ
፲፩) አግሪጳኖስ
፲፪) ዩልያኖስ
፲፫) ዲሜጥሮስ ፩ኛ (ባሕረ ሐሳብ የተገለጠለት)
፲፬) ኤራቅሊስ
፲፭) ዲዮናስዮስ
፲፮) ማክሲመስ
፲፯) ቴዎናስ
፲፰) ጴጥሮስ ፩ኛ (ተፍጻሜተ ሰማዕት)
፲፱) አኪላስ
፳) እለእስክንድሮስ ፩ኛ (የጉባኤ ኒቅያ አፈጉባኤ)
፳፩) አትናቴዎስ
፳፪) ጴጥሮስ ፪ኛ
፳፫) ጢሞቴዎስ ፩ኛ (የጉባኤ ቁስጥንጥንያ አፈጉባኤ)

፳፬) ቴዎፍሎስ
፳፭) ቅዱስ ቄርሎስ ፩ኛ (የጉባኤ ኤፌሶን አፈ ጉባኤ

፳፮) ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፩ኛ
፳፯) ጢሞቴዎስ ፪ኛ
፳፰) ጴጥሮስ ፫ኛ
፳፱) አትናቴዎስ ፪ኛ
፴) ዮሐንስ ፩ኛ
፴፩) ዮሐንስ ፪ኛ
፴፪) ዲዮስቆሮስ ፪ኛ
፴፫) ጢሞቴዎስ ፫ኛ
፴፬) ቴዎዶስዮስ ፩ኛ
፴፭) ጴጥሮስ ፬ኛ
፴፮) ድምያኖስ
፴፯) አንስታትዮስ
፴፰) እንድራኒቆስ
፴፱) ብንያሚ ፩ኛ
፵) አጋቶን
፵፩) ዮሐንስ ፫ኛ
፵፪) ይስሐቅ
፵፫) ስምዖን ፩ኛ
፵፬) እለእስክንድሮስ ፪ኛ
፵፭) ቆዝሞስ ፩ኛ
፵፮) ቴዎድሮስ ፩ኛ
፵፯) ሚካኤል ፩ኛ
፵፰) ሚናስ ፩ኛ
፵፱) ዮሐንስ ፬ኛ
፶) ማርቆስ ፪ኛ
፶፩) ያዕቆብ
፶፪) ስምዖን ፪ኛ
፶፫) ዮሴፍ ፩ኛ
፶፬) ሚካኤል ፪ኛ
፶፭) ቆዝሞስ ፪ኛ
፶፮) ሱንትዩ ፩ኛ
፶፯) ሚካኤል ፫ኛ
፶፰) ገብርኤል ፩ኛ
፶፱) ቆዝሞስ ፫ኛ
፷) መቃርዮስ ፩ኛ
፷፩) ቴዎፋኖስ
፷፪) ሚናስ ፪ኛ
፷፫) አብርሃም
፷፬) ፊላታዎስ
፷፭) ዘካርያስ
፷፮) ሱንትዩ ፪ኛ
፷፯) ክርስቶዶሉስ
፷፰) ቄርሎስ ፪ኛ
፷፱) ሚካኤል ፬ኛ
፸) መቃርዮስ ፪ኛ
፸፩) ገብርኤል ፪ኛ
፸፪) ሚካኤል ፬ኛ
፸፫) ዮሐንስ ፭ኛ
፸፬) ማርቆስ ፫ኛ
፸፭) ዮሐንስ ፮ኛ
፸፮) ቄርሎስ ፫ኛ
፸፯) አትናቴዎስ ፫ኛ
፸፰) ገብርኤል ፫ኛ
፸፱) ዮሐንስ ፯ኛ
፹) ቴዎዶስዮስ ፪ኛ
፹፩) ዮሐንስ ፰ኛ
፹፪) ዮሐንስ ፱ኛ
፹፫) ብንያሚ ፪ኛ
፹፬) ጴጥሮስ ፬ኛ
፹፭) ማርቆስ ፭ኛ
፹፮) ዮሐንስ ፲ኛ
፹፯) ገብርኤል ፬ኛ
፹፰) ማቴዎስ ፩ኛ
፹፱) ገብርኤል ፭ኛ
፺) ዮሐንስ ፲፩ኛ
፺፩) ማቴዎስ ፪ኛ
፺፪) ገብርኤል ፮ኛ
፺፫) ሚካኤል ፭ኛ
፺፬) ዮሐንስ ፲፪ኛ
፺፭) ዮሐንስ ፲፫ኛ
፺፮) ገብርኤል ፯ኛ
፺፯) ዮሐንስ ፲፬ኛ
፺፰) ገብርኤል ፰ኛ
፺፱) ማርቆስ ፭ኛ
፻) ዮሐንስ ፲፭ኛ
፻፩) ማቴዎስ ፫ኛ
፻፪) ማርቆስ ፮ኛ
፻፫) ማቴዎስ ፬ኛ
፻፬) ዮሐንስ ፲፮ኛ
፻፭) ጴጥሮስ ፭ኛ
፻፮) ዮሐንስ ፲፯ኛ
፻፯) ማርቆስ ፯ኛ
፻፰) ዮሐንስ ፲፰ኛ
፻፱) ማርቆስ ፰ኛ
፻፲) ጴጥሮስ ፮ኛ
፻፲፩) ቄርሎስ ፬ኛ
፻፲፪) ዲሜጥሮስ ፪ኛ
፻፲፫) ቄርሎስ ፭ኛ
፻፲፬) ዮሐንስ ፲፱ኛ
፻፲፭) መቃርዮስ ፫ኛ
፻፲፮) ዮሳብ ፪ኛ
፻፲፯) ቄርሎስ ፮ኛ
፻፲፰) አቡነ ባስልዮስ ዘኢትዮጵያ
፻፲፱) አቡነ ቴዎፍሎስ ዘኢትዮጵያ
፻፳) አቡነ ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
፻፳፩) አቡነ መርቆሬዎስ ዘኢትዮጵያ
፻፳፪) አቡነ ጳውሎስ ዘኢትዮጵያ
፻፳፫) አቡነ ማትያስ ዘኢትዮጵያ

የክህነት ምንጭ ከሆነው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ እስከአሁኑ ፓትርያርካችን እስከ አቡነ ማትያስ ያለው የክህነት ቅብብሎሽ ከላይ ያለውን ይመስላል። የእያንዳንዱ ቄስ፣ ዲያቆን፣ ጳጳስ ክህነት ቢቆጠር ነቁ እና የክህነቱ ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

በጉልበት ራሳቸውን የሾሙ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ባፈነገጠ መልኩ የተሿሿሙ ሰዎች ክርስቶሳዊ የሆነው ክህነት የላቸውም። ይህም ማለት ቀድሰው ምሥጢራትን አይለውጡም። ጸጋ እግዚአብሔርን አያሰጡም። ስለዚህ ሕገወጥነትን አምርረን ልንቃወም ይገባናል።
          
©ዘአማን
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/23 22:17:36
Back to Top
HTML Embed Code: