መናፍቃን ማንኛውንም ጥያቄ ሲጠይቅወት መልሱ ይኸው ሼር አድርጉት መረጃው ለሁሉም ይድረስ
፨፨፨ለመናፍቃን የማያዳግም መልስ፨፨፨
የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ
1: ሥለ ሥላሴ
የእግዚአብሔር አንድነትና ሶስትነት:-
✞ዘፍ 1:26 ዘፍ 3:22
✞ዘፍ 11:18 ዘፍ 18:1-2
✞ኢሳ 48:26 ማቴ 3:16-17
✞ማቴ 28:19 ሉቃ 1:35
✞ዮሐ 7:28-29 ዮሐ 14:25-26
✞የሐ.ስራ 3:14 1ኛ ቆሮ 12:4-7
✞2ኛ ቆሮ 13:14 ኤፌ 4:4-7
2: የእመቤታችን ቅድስናዋ ፣ ክብሯ ፣ ድንግልናዋንና
አማላጅነቷ:-
✞መዝ 9:11 መዝ 13:10
✞መዝ 44:9 መዝ 86:5
✞መዝ 131:13 መዝ 44:2
✞መኃ 4:12 ኢሳ 7:14
✞ኢሳ 49:23 ኢሳ 60:14
✞ማቴ 1:23 ሉቃ 1:28
✞ሉቃ 1:42 ዮሐ 2:1-11
✞ዮሐ 19:16 ሮሜ 11:26-27
✞2ኛ ቆሮ 11:2 ራዕ 12:16
3: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ እንጅ አማላጅ
አይደለም፡-
✞ዘፍ 3:22 1ኛ ሳሙ 16:1
✞ኢሳ 9:6 ዳን 7:14
✞ሆሴ 13:4 ዘካ 9:9-10
✞ሚክ 5:2 ሉቃ 1:32-33
✞ዮሐ 10:30 ሉቃ 2:12
✞ዮሐ 14:7 ሮሜ 9:5
✞ቆላ 2:9-10 ቲቶ 2:11-13
✞ዕብ 1:3-4 ዕብ 1:10-11
✞1ኛ ጴጥ 3:23 1ኛ ዮሐ 2:23
✞ራእ 3:22 ራእ 22:12-13
4: ስለታቦት እና ፅላት
✞ዘፃ 24:12 ዘፃ 25:10
✞ዘፃ 25:21 ዘፃ 26:34
✞ዘፃ 31:18 ዘፃ 32:15
✞ዘፃ 34:1 ዘፃ 34:28
✞ዘፃ 37:1 ዘፃ 40:20
✞መኃ 7:89 ኢያ 3:3
ኢያ 7:6 2ኛ ቆሮ 6:16
5: ሥለ ፆም የመጽሐፍ ቅዱስ ማሥረጃ:-
✞ዘፃ 34:28 ዘፃ 9:9
✞ሳሙ 20:26 1ሳሙ 7:6
✞1ሳሙ 31:13 2ኛ ሳሙ 1:12
✞2ኛ ሳሙ12:16 ዕዝ 8:21
✞ዕዝ 68:10 ዕዝ 108:24
✞ኢሳ 48:3 ኤር 36:9
✞ዳን 9:3 ዳን 20:2-3
✞ኢዩኤ 2:14 ኢዩኤ 2:12
✞ዩና 3:5 ማቴ 4:2
✞ማቴ 6:16:18 ማቴ 9:14-15
✞ማቴ 17:21 ማር 2:18
✞ማር 9:29 ሉቃ 2:37
✞ሉቃ 18:12 የሐ.ስራ 13:3 ✞የሐ.ስራ 14:23 2ኛ ቆሮ
11:17
6: መስቀል በመጽሐፍ ቅዲስ:-
✞ማቴ 10:38 ማቴ 16:20
✞ማር 8:34 የሐ.ስራ 5:30
✞1ኛ ቆሮ 1:18 ገላ 3:13
✞ገላ 6:13 ፊል 2:8
✞ፊል 3:18
7: ጥምቀትን በተመለከተ:-
✞ሕዝ 36:25 ማቴ 3:5-6
✞ማቴ 26:19-20 ማር 1:4-5
✞ማር 16:16 ሉቃ 3:21
✞ዮሐ 3:5 ዮሐ 3:22
✞ኤፌ 4:5 ገላ 3:26-27
✞የሐዋ 19:4 የሐዋ 18:8
✞የሐዋ 13:24 የሐዋ 10:47
✞የሐዋ 9:18 1ኛ ቆሮ 1:16
✞1ኛ ቆሮ 10 :2 1ኛ ቆሮ 12:13
8:ስዕለትን በተመለከተ:-
✞ዘኁ 28:20 ዘኁ 21:2
✞ዘፃ 23:21 መሳ 11:30
✞መዝ 49:14 መዝ 75:11
✞1ኛ ሳሙ 1:11 መክ 5:4-5
✞ዮና 2:10 ናሆ 1:15
✞የሐዋ 18:18
9: ፃድቃን ሠማዕታት ያማልዳሉ:-
✞ዘፍ 18:17-18 ዘፍ 18:23:24
✞ዘፍ 20:7 ዘፍ 33:3
✞ዘፍ 42:6 1ኛ ሳሙ 28 :14
✞2ኛ ሳሙ 1:2 2ኛ ነገ 1:13
✞2ኛ ነገ 2:15 2ኛ ነገ 4:9
✞2ኛ ነገ 4:32-35 መዝ 88:34
✞ማቴ 18:18 ዮሐ 20:23
✞የሐዋ 10:25 የሐዋ 16 :29
✞1ቆሮ 6:1-2 ፊሊ 4:6
✞1ኛጢሞ 5:17 ያዕ 5:14
✞ራዕ 14:13
10: መላዕክት ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ:-
✞መዝ 148:2 ኢሳ 6:3
✞ማቴ 4:12 ማቴ 18:10
✞ማቴ 25:31 ማር 8:38
✞ራእ 1:11 ሉቃ 1:19
11: መላዕክት ፀሎታችን ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ:-
✞ጦቢ 12:15 ሉቃ 15:10
✞የሐዋ 10:4 እዩብ 25:3
✞ኤር 33:22 ዳን 7:10
✞ሄኖ 10:1 ራዕ 5:11
12:ለመላዕክት የአክብሮት ስግደት ይገባል:-
✞ዘፍ 19:1 ማኅ 22:31
✞ኢያ 5:14 ዳን 8:16-17
13:መላዕክት አብሣሪያን ናቸው:-
✞ዘፍ 16:11 ሉቃ 1:13
✞ሉቃ 1:19 ሉቃ 1:30-31
✞ሉቃ 2:10-11
14:መላዕክት በአደጋ ጊዜ ፈጥነው ይደረሣሉ:-
✞ዘፍ 22:11-12 መዝ 90:11-12
✞ዳን 6:22 ዳን 10:13
✞ማቴ 2:13 የሐዋ 5:19-20
✞የሐዋ 12:7
15: ፀበል መርጨት ያስፈልጋል:-
✞ዘኁ 19:20
በተጨማሪም ሁላችንም እያንዳንዱን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ደጋግመን እናንብበው እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋልና ጥበቡን ይስጠን አሜን
@Nigatu5

የቁባቱን በድን የቆራጠው ካህን! (መሳ. 19-20)
በእስራኤል ልጆች ታሪክ ውስጥ አያሌ አስከፊ ተግባራት ተከናውነዋል፤ ዛሬ የምናየው ይህ አንዱ ነው፤ “በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ በሌለበት ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ማዶ የተቀመጠ ሌዋዊ ነበረ፤” (መሳ. 19፥1) ይላል፣ በመሳፍንት መጽሐፍ ውስጥ ከተቀመጡት የብንያም ሰዎችን የሥነ ምግባር ብልሹነትና በምላጭ ጫፍ ላይ መቆማቸውን ከሚያሳዩት ታሪኮች አንዱን ለመተረክ ሲነሳ።
በርግጥ ሌዋዊው ካህን ቁባቱን ፍለጋ ከኤፍሬም ወደ ቤተልሔም መሄዱ፣ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባቱን ያሳያል፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው ተግባር አልነበረም፤ በተጨማሪም፣ እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች መሳፍንትን የሰጠው፣ ርሱ ብቻውን በነርሱ ላይ ሊነግሥ ነበር። ነገር ግን ለጌታ ከመታዘዝ ይልቅ፣ የሃይማኖት መሪዎቿ ድካምና ኃጢአት እያየለባቸውና እየባሰባቸው ሲሄድ በተደጋጋሚ እንመለከታለን።
ካህኑ ቁባቱን አጊኝቶአት ይዞ፣ ከቤተልሔም ወደ ኤፍሬም በሚመለስበት ጊዜ እግረ መንገዱን ጊብዓ በምትባል በብንያማውያን ከተማ መሸበትና አደረ።
የከተማዪቱ ሰዎች ግን ልክ እንደ ሰዶምና ገሞራ ሰዎች፥ እጅግ አስጸያፊ ተግባር የሚፈጸሙ ነበሩ። በእንግድነት ወደ ነርሱ የመጡትን ካህንና ቁባቱን ከማስተናገድ ይልቅ፣ በካህኑ ላይ የሰዶማዊነት ነውር ሊፈጽሙበት ፈልገው አሳዳሪውን ሽማግሌ፣ እደ ሰዶም ሰዎች ግድ አሉት። ሽማግሌው፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ። ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት፥ እነሆ፥ አሉ፥ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዱአቸው፤ እንደ ወደዳችሁም አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አታድርጉ” (19፥23-24) ብሎ ቢለምናቸውም፣ ሰዎቹ ግን ሊሰሙ ፈጽሞ አልወደዱም። በመጨረሻም ግን ሽማግሌው የገዛ ሴት ልጁንና የሌዋዊውን ቁባት አውጥቶ ሰጣቸው።
ሰዎቹ፣ የሌዋዊው ቁባት እስክትሞት ድረስ በመፈራረቅ ሌሊቱን ሙሉ አመነዘሩባት። ሽማግሌው እንደ ሎጥ፣ ራሱን ከማኅበረ ሰቡ ርኩሰት የጠበቀና ያገለለ መኾኑ እጅግ ያስደንቃል፤ ተግባራቸውንም “ክፉ ነገር” ብሎ መጥራቱ ይኸንኑ ያሳያል፤ ሌዋዊው ግን ያሳየው ግዴለሽነትና ደንታ ቢስነት ያሳዝናል።
ሌዋዊው የቁባቱን ሬሳ 12 ቦታ ቆራረጠና ለእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንዳንዱን ቁራጭ ላከ። ይህም ነገር የ12ቱን ነገዶች ቁጣ ቀሰቀሰና ምን እንደ ተፈጸመ ለማየት መጡ። ታሪኩን በሰሙ ጊዜ፥ ይህን ኃጢአት የፈጸሙትን ሰዎች አሳልፈው እንዲሰጧቸው ብንያማውያንን ጠየቁ። ብንያማውያን ተቃወሙ፥ የርስ በርስ ጦርነት ተነሣ። በጦርነቱም 40000 እስራኤላውያንና 25100 ብንያማውያን ሞቱ። የብንያማውያን ሴቶችና ልጆች በሙሉ ተገደሉ። ከብንያም ነገድ በሙሉ የተረፉት 600 ሰዎች ብቻ ነበሩ።
ሌሎች እስራኤላውያን፥ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ የኾነው የብንያም ነገድ ሊጠፉ እንደ ኾነ ተገነዘቡ፤ ስለዚህ ለእነዚህ 600 ብንያማውያን 600 ሚስቶች የሚገኙበትን ዘዴ ፈጠሩ። በዚህም የብንያምን ነገድ ጨርሶ ከመጥፋት አዳኑት።
ሰዎች ራሳቸው የሚፈልጉትን ነገር ብቻ ሲያደርጉ፥ ኃጢአታቸው አድጎ በርካታ ሰዎችን እንደሚነካና እንደሚያጠፋ አይገነዘቡም። ኀጢአትና ኀጢአተኝነት የመዛመትና ሌላውን የመውረስ ጠባይ አለው፤ የጊብዓ ሰዎች ኃጢአት በሺህ የሚቆጠሩ የበርካታ እስራኤላውያንን ሞትና የብንያም ነገድን ወደ ውድመት የሚያደርስ ጥፋት አስከትሎ ነበር። የአንድ ካህን ሕገ እግዚአብሔር መጣስና የብንያም ነገድ ሰዶማዊነት መኾን፣ ፍጻሜውን መራራ አድርጎታል። ኀጢአት በማናቸውም መንገድ የፍጻሜ መንገዱ ጣፋጭ አይኾንም!
እንግዶችን በማስተናገድ አንዳንዶች ራሱ እግዚአብሔርን ሌሎች ደግሞ መላእክትን ተቀብለው ነበር፤ የብንያም ሰዎች ግን እንግዶቻቸውን ለነውር ተግባር ፈለጉ፡፡ ወንዶቹ ኀፍረተ ቢስና ፍትሕ አልባ ነበሩ፡፡ ምናልባት ታሪኩ ሊረሳ እንጂ ሊተረክ የሚገባው አይመስልም፤ ግን እንድንተርከው ታዝዘናል፡፡ የሴቲቱ ታሪክ አሳዛኝና ልብ ሰባሪ ነው፤ የሚቆምላትና የሚከላከልላት አልነበረም፡፡ ሌዋዊው ሊንከባከብ ከአባትዋ ቤት ቢያወጣትም፣ ነገር ግን ለርኩሳንና ለማይራሩ ሰዎች አሳልፎ ሰጣት፡፡ በዚያ ሙሉ ሌሊት የተፈጸመባትን ርኩሰት ማስተዋልና ርኅራኄ ሊያሳያት ሲገባ ግን አላደረገም፤ ብሎም የቀብር ክብርዋን በመንፈግ ሰውነቷን ቆራረጠው!
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ያሉ ታሪኮች መቀመጣቸው፣ ሰው ከእግዚአብሔር ፊትና ከአገዛዙ ሲለይ፤ በራሱም መንገድ መልካም መስሎ የታየውን የሚያደርግ ከኾነ ፍጻሜው ይኸው መኾኑን ያሳያል፡፡ ወዳጆቼ! ዛሬም በምድራችን ላይ የምንሰማቸው አያሌ ክፉ ተግባራት፣ ከዚህ እውነታ እምብዛም የራቁ አይደሉም! ከኀጢአታችን ለመታቀብና ለመተው፤ ብሎም ንስሐ ገብቶ ለመመለስ ፈቃደኞች ባልኾንን መጠን፣ የኀጢአት ፍሬና መከር መብላታችንና ማጨዳችን አይቀሬ ነው! “ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።” (ሆሴ. 6፥1) የሚለው የጌታ ቃል ዛሬም ሕያው ነውና እንመለስ!

ሰው አዝርእትን አትክልትን ይመስላል። አዝርእት ተዘርተው፣ አብቅለው፣ አብበው፣ አፍርተው ከጎተራ ይቀመጣሉ። ሰውም ተጸንሶ፣ ተወልዶ፣ በመልካም ሥራ አብቦ፣ ፍሬ ትሩፋትን አፍርቶ ከመንግሥተ ሰማያት ይገባል።
ፍጥረታትን በጽሙና ሆነን ብንመረምራቸው ፍቅርን፣ ትሕትናን፣ ትዕግሥትንና የመሳሰሉትን እንማርባቸዋለን። ጊዜያችንን በሚጠቅም ነገር እናውለው። ሞት መኖሩን አስበን እንኑር። ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ነገ በሥነ ምግባር ልንሻሻል ይገባናል።
ሠናይ ጊዜ

Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (🌼 £itsum 🌼)
+ ስለቅዱሳንና ቅድስና ጥቂት +
በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳን ሲባል፡- ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ሰማዕታት፣ ሊቃውንት፣ መናንያን /ገዳማውያን/፣ ደጋግ ሰብአ ዓለም ይጠቀሳሉ፡፡ ቅዱሳን ዜግነትና ተቋማዊ አጥር ባይኖርባቸውም በልማድ እንደየሚከበሩበት ቦታ ስፋትና ጥበት አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ እየተባሉ ይለያሉ፡፡ የቅድስና አሰጣጡ አስቀድሞ በጉባኤ ደረጃ አልነበረም፡፡ ሰማዕታት የሆኑ እንደሆነ ምስክርነቱ የአደባባይ ነውና በቶሎ ቅድስና ያገኛሉ፡፡ አንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና ቅዱስ ባስልዮስ ያሉ በአፍም በመጻፍም የገነኑ አበው ግብርና ቅድስናቸው ከመጉላቱ የተነሣ ከቤተ ክህነቱ ቀድሞ ምዕመኑ በቅድስና ጠርቷቸዋል፡፡ ቅድስናው በገቢረ ተአምርና በራእይ የሚገለጥም አለ፡፡
በዚህ ዘመን ግን ከሞላ ጎደል በሁሉም ሐዋርያዊ ትውፊትን በሚከተሉ አብያተ ክርስቲያናት ቅድስና በቃለ ሲኖዶስ ይሰጣል፡፡ የእኛም አካሄድ ተመሳሳይ ነው፡፡ አንድ አባት ቅዱስ ከተባለ በኋላ ስለሚደረገው ልዩ ልዩ ተግባር በ #ወልታ_ጽድቅ ወይም በዲያቆን ሰሎሞን #የኢትዮጵያ_ቤተ_ክርስቲያን_ወርቃማ_ዘመናት ወይም ደግሞ በዶ/ር ሐዲስ የሻነው የትምህርተ ሃይማኖት መጻሕፍት ማንበብ ይቻላል፡፡ ቅድስና በየጊዜው የሚጨመር ነው፤ አይቆምም፡፡ በሌላ በኩል በበጎ የሚነሣው አባት ላይ ከጊዜ በኋላ የሃይማኖት ህፀፅ የተገኘ እንደሆነ የሚታረምበት ዕድል ስለመኖሩ የአርጌንስ ታሪክና የእኛ ሲኖዶስ የግብፆችን የስንክሳር ስርዋጽ ያረመበት ድርጊት ይጠቁመናል፡፡
በ1960ዎቹ ተጀምሮ ሲካሄድ ቆይቶ እንደ መቀዛቀዝ ባለው የኦሪየንታል-ምሥራቃውያን ኢመደበኛ ንግግር የቅድስና አሰጣጥን፣ ማንና እንዴት ቅዱስ ይባል ማለትን ለነገረ መለኮትና ለታሪክ ምሁራን በመተው በግራ ቀኝ ወገኖች የተላለፈው ግዝት እንዲነሣ ሐሳብ ቀርቦ ነበረ፡፡ ሐሳቡ እስካሁን ዳር አልደረሰም ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያናችን በ1988 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ በተቋቋመ የጳጳሳትና የሊቃውንት ኮሚቴ የተዘጋቸው የእምነት፣ ሥርዓትና የውጭ ግንኙነት መጽሐፍ በኬልቄዶናውያን ላይ የተላለፈው ግዝት እንደማይነሣ፣ በእነርሱ ስር ያሉ አበውንም በቅድስና መቀበል እንደማይችል በአጽንዖት ገልጧል፡፡ ቀድመው በስንክሳራችን በገቡት የሃይማኖት ጀርባቸው ከወደ ኬልቄዶን በሚመዘዝ አበው ላይ ግን ያሳረፈው ውሳኔ የለም፡፡
---
( ደብተራ በአማን ነጸረ )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

#የካህኑን እጅ በደም ተነክሮ ሲያዩት ደንግጠው ወደቁ
አንድ ዓለምን ትተው የመነኑ ገዳማዊ በቅዱስ ስጋውና በክቡር ደሙ ላይ ዲያብሎስ ጥርጣሬ እየፈጠረ ይዋጋቸው ጀመር፡፡ ሁልጊዜም ሲቆርቡ ካሕኑ የሚሰጧቸው ህብስትና ዲያቆኑ የሚያቀብላቸው ወይን ብቻ ነው የሚታያቸውና መች ነው እውነተኛ ስጋና ደም የሚሆነው በሚለው ጥያቄ ተነስተው በጊዜ ብዛት ወደ ጥርጣሬ ሊገቡ ሆነ፡፡
በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ከእሳቸው በዓት አጠገብ ያሉ የበቁ አባት ዘንድ በመመጣት ችግሩን ይነግራቸዋል፡፡ እኒህ የበቁ አባትም ወደ ጎረቤታቸው ይመጡና ችግሩን የራሳቸው አስመስለው “አባቴ የምስጢረ ቁርባን ነገር ግራ አጋባኝ፣ አእምሮዬ እውነተኛ ስጋውና ደሙ ሆኖ የሚለወጠው መች ነው? እያለ በጥያቄ ሰላም ነሳኝ ይሏቸዋል፡፡
በነገሩ የተገረሙት አባትም እኔም እኮ የምነግረው አጥቼ እንጂ ተመሳሳይ ጥያቄ ወደ አእምሮዬ መመላለስ ከጀመረ ከራርሟል ይሏቸዋል፡፡ እርግጠኛ ለመሆን በቅዳሴ ጊዜ ካህኑ ስጋውንና ደሙን ሲፈትቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሆነው በማስቀደስ ለማየት ተስማሙ፡፡ በቅዳሴ ጊዜም ካህኑ ሕብስቱን አንስተው ሲፈትቱ ሰይጣን የሚፈትናቸው አባት የካህኑ እጅ በደም ተነክሮ ሲያዩት ደንግጠው ወደቁ፡፡ አስገራሚው ነገር ከሁለቱ ባሕታውያን ውጪ ራሳቸው ቀዳሹ ካሕንም ሆኑ ሌሎቹ ልኡካን ይህን ምስጢር አላዩም፡፡
ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ በሕብስትና በወይን መልክ ይሰጠን እንጂ የክርስቶስ አማናዊ ስጋና ደም ነው፡፡ ይህ ትልቅ ምስጢር የሚፈጸምባት ስርዓተ ቅዳሴው የሚካሄድባት ቅድስት ቤተክርስቲያንም የምስጢር መፈጸሚያ ስፍራ ነች፡፡ ለዚህም ነው ይህን ምስጢር የምንካፈልባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መርዳት፣ መስራት የሚገባው፡፡

(መስከረም ፲፯ን ከ16ቱ አብያተ ክርስቲያናት የት ሊያከብሩ ዐስበዋል?)
#መስከረም ፲፯፤ #በዓለ_አስተርእዮተ_መስቀለ_ኢየሱስ፡፡
#በአዲስ_አበባ_የመስቀለ_ኢየሱስ_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፫ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ቀጨኔ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መርካቶ) → ቀጨኔ (መድኀኔ ዓለም)፤
፪. ደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም ቤ/ክ፤
አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ቀበና (ራሽያ/እንግሊዝ/ ኤምባሲ ጀርባ)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቀበና፡፡
፫. ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ገብረ ክርስቶስ ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ዘነበ ወርቅ (አለርት ሆስፒታል)፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት → ዘነበ ወርቅ (አየር ጤና በሚለው ታክሲ)
ወይም ከሜክሲኮ (ጦር ኃይሎች) → ዘነበ ወርቅ
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የመስቀለ_ኢየሱስ_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲፫ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም፤ መስቀሉ በክብር ያረፈባት፤ ባለ መስቀልኛ ቦታ
አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ አምባሰል፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → አምባሰል (ግሸን)፡፡
፪. ዓሲምባ መስቀለ ኢየሱስ ቤ/ን ፤ በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመን የተመሠረተ፤ በአባ ዘወንጌል አስተባባሪነት ሕንፃ ቤ/ኑ በአዲስ መልክ የታነጸ፡፡
አድራሻው፤ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት ፥ ኢርብ ወረዳ → ዓሲምባ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → ዓዲግራት → 80 ኪ.ሜ. ዓሲምባ፡፡
፫. ደብረ ሊባኖስ ገዳም መስቀል ቤት፤ (በዓመት አንዴ ብቻ የሚቀደስበት)፡፡
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ፥ ደብረ ሊባኖስ ገዳም፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ሊባኖስ (ገዳም)፡፡
፬. ደብረ ብርሃን ጎሽባዳ አዳኙ መስቀለ ኢየሱስ፤ (መስቀሉ ያረፈበት)
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ደብረ ብርሃን፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → (17 ኪ.ሜ.) ጎሽ ባደ፡
፭. ባሶና ሞይ ሜዳ መስቀለ ኢየሱስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ (መስቀሉ ያረፈበት)
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ባሶና ወረዳ ሞይ ሜዳ ቀበሌ፥ መስቀለ ኢየሱስ ንዑስ ቀበሌ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → ባሶና /ሞይ ሜዳ/፡፡
፮. ቡልጋ ሀገረ ማርያም ግርማ አገር መስቀለ መስቀለ ኢየሱስ ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ቡልጋ ሀገረ ማርያም ወረዳ፥ ግርማ አገር ቀበሌ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → በደብረ ብርሃን መስመር → ቡልጋ/ግርማ አገር ቀበሌ/፡፡
፯. አንኮበር መስቀለ ኢየሱስ፤
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ አንኮበር፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → (42 ኪ.ሜ.) አንኮበር፡፡
፰. ደራ ቁላላ መስቀለ ኢየሱስ ከምትባል አጥቢያ
አድራሻው፤ ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ደራ ወረዳ፥ ቁላላ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር → ወረታ → ደራ ወረዳ /ቁለላ/፡፡
፱. ደራ ጉንደ መስቀል መካነ ሰላም መስቀለ ኢየሱስ ገዳም፤
አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ደራ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደራ መካነ ሰላም፡፡
፲. ወላይታ ኮንታ አደ ኦፋ መስቀለ ኢየሱስ እና ቁስቋም ማርያም ቤ/ን ፤
አድራሻው፤ ወላይታ ኮንታ ሀገረ ስብከት ፥ በዳሞት ጋሌ ወረዳ፥ አደ ኦፋ ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ወላይታ፡፡
፲፩. ሐዋሳ ሎቄ ደብረ መድኀኒት መስቀለ ኢየሱስ ቤ/ን ፤
አድራሻው፤ አዋሳ ሲዳሞ ሀገረ ስብከት ፥ አዋሳ ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → አዋሳ፡፡
፲፪. ሰባት ቤት ጉራጌ እዣ ኩበና ሚካኤል፤ (በድርብነት ይከብራል)፡፡
አድራሻው፤ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ፥ እዣ (ከደቡቡ ቁልቢ ደብረ ወርቅ አትርፎ ጊዮርጊስ ቤ/ን አጠገብ)፡፡
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ጉራጌ/እዣ/፤
፲፫. ዶዶላ መስቀለ ኢየሱስ፤
አድራሻው፤ ደቡብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ፥ ዶዶላ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሻሸመኔ → ዶዶላ፡፡

የሕይወት ዛፍ፦ በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ
//__
በገነት ውስጥ ያለችውን የሕይወት ዛፍ መኖሯን የሰማነው አዳም ከገነት በተሰደደበት ጊዜ ነበር። ሞትን የሚያስፈርደውን ዛፍ በልቷልና እጁን እንዳይሰድና ከሕይወትም ዛፍ እንዳይበላ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደው መንገድ የምትገለባበጥ የእሳት ሰይፍ በእጃቸው የያዙ መላእክት ይጠብቋት ነበር። ዘፍ. 3፥22 ይህችን የሕይወት ዛፍ ፍሬዋን እንበላ ዘንድ ተመልሰን ገነት እስከምንገባ ድረስ እግዚአብሔር አልተወንም። እኛ ወደ ገነት የምንገባው በአካለ ነፍስ እንጅ በአካለ ሥጋ ባለመሆኑ በገነት ያለችውን የሕይወት ዛፍ ፍሬዋን ለመብላት የምትችለው ሥጋችን በመቃብር ውስጥ ታድራለች። ነፍሳችንም ከሥጋችን ተለይታ ወደ ተዘጋጀላት ገነት ትገባለች። እግዚአብሔር ቸር ነውና የሕይወትን ዛፍ ሳናያት ፍሬዋንም ሳንመገብ እንዳንቀር በመካከላችን አምጥቶ ተከለልን ያችም የሕይወት ዛፍ በመካከላችን የበቀለው ቅዱስ መስቀል ነው። አባ ጊዮርጊስ በውዳሴ መስቀል መጽሐፉ ቅዱስ መስቀልን የሕይወት ዛፍ ብሎ ነው የሚጠራው። ለመዳን ያበቃንንን የሕይወት ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስን የተመገብነው በመስቀል ላይ አግኝተነው ስለሆነ ነው። በገነት ሳለን ያልተመገብነው ይህ የሕይወት ምግብ በገነት ሳለን ከበላነው የሞት ፍሬ ይልቅ በእጅጉ ጠቀመን። እግዚአብሔር ያዘጋጀልንን የሕይወት ዛፍ ፍሬዋን በስንፍናችን ምክንያት ሳንበላት ለሥጋችን አድልተን የበለስን ፍሬ በላን። እግዚአብሔር ክፉዎች አይሁድ የሕይወትን ዛፍ እንዲተክሉት አደረገ። ሲተክሉት ፍሬው ዓለምን እንደሚያድን ቢያውቁ ኖሮ ባልተከሉትም ነበር። እግዚአብሔር ባወቀ ዕፀ መስቀል ተተከለ፤ ፍሬውም የክርስቶስ ሥጋና ደም ሆነ።
#የሕይወት_ማዕድ
ነቢዩ ዳዊት “ወሠራእከ ማዕደ በቅድሜየ፤ በፊቴ ማዕድን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ራሴን በዘይት ቀባህ” መዝ. 23፥5 በሚለው መዝሙሩ ውስጥ ማዕድ ብሎ የጠራው ቅዱስ መስቀልን ነው። የዘለዓለም ምግብ ክርስቶስን የተመገብንበት ይህ ቅዱስ መስቀል ሁልጊዜም በቤተ ክርስቲያን ፊት እንደተዘረጋ ይኖራል። አይሁድ ያቀረቡት የሞት ምልክት አድርገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን የሕይወት ምልክት አደረገው። ጠላቶቻችን ሲሆኑ ይህንን የከበረ ማዕድ በፊታችን አቀረቡልን። ቅዱስ ዳዊት “በዱር መካከል አገኘነው” መዝ. 132፥6 ብሎ በሌላ መዝሙር የዘመረለት የጌታ መስቀል በዘመናት ሁሉ ስንፈልገው የነበረ መድኃኒት ነው። ለቁስለኛ ከመድኃኒት በቀር ምን ያስፈልገዋል? ለተራበ ሰውስ ከምግብ ውጭ ምን እንዲያቀርቡለት ይሻል? እነሆ ቅዱስ መስቀል ለሕሙማን ፈውስ ለተራቡትም ምግብን ይዞ በዱር መካከል ካሉ ዕፀዋት ተለይቶ የሕይወትን ፍሬ አፍርቶ አገኘነው። እንደ አብርሃም ያለ ቅድስና ሳይኖረን አብርሃም በጉን ታስሮ ያገኘበትን ዕፀ ሳቤቅ ከነበጉ አገኘነው ዘፍ. 22፥13። አብርሃም ያቀረበውን በግ ዛሬም በፊታችን ቀርቦ እንመገበዋለን፤ የአብርሃም በግ በይስሐቅ ፋንታ ተሠዋ፤ እኛ ያገኘነው የእግዚአብሔር በግ ክርስቶስ ግን ስለ ዓለም ሁሉ ተሠዋ። አብርሃም ያቀረበው በግ የታሰረበት ዕፀ ሳቤቅ ጌታ የተሰቀለበት የቅዱስ መስቀል ምሳሌ ነበር። የሀገራችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ “ዕፀ ሳቤቅ ብሂል ዕፀ ሥርየት መስቀል፤ ዕፀ ሳቤቅ የተባለ የሥርየት እንጨት መስቀል ነው” ብሎ እንደተረጎመው።
#የመስቀሉ_መጥፋት
ለቁስላችን ፈውስን፤ ለረሀባችን ምግብን፤ ለድካማችን ኃይልን ያገኘንበትን መስቀል ጌታ ካረገ በኋላ አይሁድ ከፊታችን አጠፉብን። እነሱ ያሰቡት በእንጨት ተሰቅሎ የሞተ ሁሉ የተረገመ ነው ስለተባለ ክብር ይግባውና በፊታችን ክርስቶስ እንደተረገመ ሰው እንዲቆጠር ነበር። ነገር ግን ከሰዎች ሁሉ እርግማንን የሚያርቅ ሆነ። በገነት ካሉ ዕፀዋት መካከል የምንታረቅበትን ፍሬ ይዞ የተገኘ ዛፍ የለም። በቀራንዮ የተተከለው መስቀል ግን ከእግዚአብሔር ጋር የምንታረቅበትን ፍሬ ያስገኘ በመሆኑ በገነት ካሉት ዛፎች ይልቅ የጠቀመን ይህ ነው። በገነት ሳለን የሰማነውን እርግማን ያስወገደልን የክርስቶስ መስቀል ነው። አይሁድ እና አጋንንት ይህንን አላሰቡም። ለሰው ልጅ ጥቅም ይሰጣል ብለው ሳያስቡ ለሰዎች ጠቅሞ ቢያገኙት መልሰው በቆሻሻ መድፊያ ቦታ ጣሉትና ሁሉም ሰው የቤት ጥራጊ እንዲደፋበት አዘዙ። ለሦስት መቶ ዓመታት ቅዱስ መስቀል ከምዕመናን ፊት ተሠውሮ ነበር። መጀመሪያ “በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይሰደድ” ዮሐ. 9፥22 ብለው ዐዋጅ እንደነገሩ አሁንም በመስቀሉ ላይ ቤቱን ጠርጎ ያልደፋ ይቀጣል ብለው ዐዋጅ ስለነገሩ መስቀሉ በጎልጎታ ተቀብሯል። ቅዱስ ያሬድ “በጎልጎታ ዘደፈኑ አይሁድ ዮም ተረክበ ዕፀ መስቀል፤ በጎልጎታ አይሁድ የቀበሩት ዕፀ መስቀል ዛሬ ተገኘ” ብሎ በዘመረው ዝማሬ የትና ማን እንደቀበረው አስረጂ ነው።
#ሐዋርያት ሲቀበር ለምን ዝም አሉ? ፈጥነው ከተቀበረበት ያላወጡትስ ለምንድነው?
በዘመኑ ሐዋርያት ወንጌልን ለማዳረስ በየሀገሩ ሁሉ እስከ ዓለም ዳርቻ ይዞሩ ስለነበር መስቀሉን ፍለጋ ወደ ኢየሩሳሌም አልተመለሱም። የሚድኑ ነፍሳትን ፍለጋ ከሮማ ነገሥታትና ከአጋንንትም ጋር ጦርነት ላይ ስለነበሩ ሰዎችን ከኃጢአት ነጻ ለማውጣት እንጅ መስቀሉን ከተቀበረበት ለማውጣት ሳይሞክሩ በሰማዕትነት በየሀገረ ስብከታቸው አረፉ። በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዘመነ ሰማዕታት ሲያልፍና ቤተ ክርስቲያንም ከነገሥታት እስራትና ግድያ ስታርፍ መስቀሉን የሚፈልግ ትውልድ ተነሣ። ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሰላምና በዘመነ ሰማዕታት ልትሠራው የሚገባትን ለይታ ካላወቀች ዓለምን አሸንፋ መቀጠል አትችልም። በዘመነ መከራ ወንጌል ወደ መስበክ ምዕመናንን በክህደት በኃጢአት እንዳይያዙ የመጠበቅ ሥራ ላይ ትኩረት ማድረግ አለባት። በሰላም ዘመን ዳግሞ ማለትም አብያተ ክርስቲያናት ተከፍተው፣ ሃይማኖቱ የቀና ምግባሩ የጸና ንጉሥ አንግሠው በትምህርቱ መናፍቃንን የሚገሥጽ በትሩፋቱ ምዕመናንን የሚያንጽ ጳጳስ አግኝተው በተቀመጡበት ሰዓት የቤተ መቅደስ ሕንጻ ብትገነባና ሌሎችንም ምዕመናንን ከመጠበቅ ወንጌልን ከማስፋት ተጨማሪ የሆኑ ሥራዎችን ብፀራ አያስነቅፋትም። ለዚህ ነው በሐዋርያት ዘመን መስቀሉን የመፈለግ ሥራ ያልተጀመረው የሚቀድም ሥራ ስለነበረ ነው።
#የዕሌኒ_መነሣት
ንግሥት ዕሌኒ በክርስቶስ ፍቅር ልቧ የታሰረች ሴት ነበረች። የመስቀሉ ዜና በምድር ላይ ጠፍቶ ስለነበረ ወደ እግዚአብሔር ለማመልከት ሱባኤ ገብታለች። የዓለም ነገር አይገርማችሁም? መስቀሉ በተተከለበት ስፍራ የተቀበሩ ብዙዎቹ ሙታን ተነሥተዋል፤ መስቀሉ ከቆመበት አካባቢ የነበሩ መቃብሮች ተከፍተዋል፤ መስቀሉ ቀራንዮ ላይ ከቆመ በኋላ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀዷል፤ በዚህ መስቀል ላይ የተሰቀለው ክርስቶስ ከሞተ በኋላ ጎኑን ቢወጉት ከጎኑ ውኃና ደም ሲፈስ ታይቷል። ይህ የሕይወት ውኃ የፈለቀበት ምንጭ ቅዱስ መስቀል ሲጠፋ ከሥሩ የተነሡ ሙታን እንዴት ዝም አሉ? ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ጎኑን የወጋው ወታደር የጠፋች ዐይኑ የበራችለት የመስቀሉ ጥላ ሲያርፍበት የጌታም ከጎኑ የፈሰሰ ደሙ ሲረጭበት ነበር ይህ ዓይኑ የበራችለት ሰው ስለመስቀሉ መጥፋተ እንዴት አልጠየቀም? ለመስቀሉ ቤት ሠርቶ ሊያኖር የሞከረ ሰው እንዴት አልተገኘም? ዓለም ምን እንደሚፈልግ ተመልከቱ። የሚጠቅመውን አያውቅም። ለሚጠቅመው ነገር ስፍራ አያዘጋጅም። ያ ሁሉ ተአምራት የተደረገበትን መስቀል በማይገባ ስፍራ ጣሉት፤ ከዐይናችን ሰወሩት። ዕሌኒ ሱባኤ እስከገባች ድረስ ስለመስቀሉ በትክክል