Telegram Web Link
" የልባችሁን አእምሮ አድሱ " ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ጳጕሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት " ሁለመናችንን በሐዲስ ምግብ እየመገበ የሚጠብቀን አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2016 ዓ.ም ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2017 ዓ.ም በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ " በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም " በገሃዱ ዓለም የማያረጅ እና የማይታደስ የለም መታደስ ባይኖር ኖሮ ሕይወታውያን ፍጡራን በሕይወት መካከል መቀጠል አይችሉም ነበር፤ የዘመን መታደስ የስነ ፍጥረት አንዱ አካል ስለሆነ በየጊዜው ይታደሳል። እኛ ሰዎችም በየጊዜው እንድንታደስ እግዚአብሔር አዞናል ፤ ዘመንም እንደሌላው ያረጃል ይታደሳል ፤ ዛሬ አሮጌውን ሸኝተን አዲሱን የምንቀበልበት ዘመን ላይ እንገኛለን።

የተወደዳችሁ ምእመናን ፍጥረታትን ማደስ የእግዚአብሔር ሥራ ቢሆንም ከፈጣሪ በተሰጠው ሥልጣን ሰውም የማደስና የመምራት ሥልጣን አለው። ዛሬ ዓለማችን በመታደስ ሳይሆን በማርጀት ላይ የምትገኘው ከሰዎች ድርጊት የተነሳ ነው። እየተፈጠረ ያለው ችግር ከሰው አጠቃቀም ስህተት እንደሆነ እየሰማን እና እያየን ነው።

ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ ሰው ምደረ በዳውን ወደ ሐመልማለ ገነት የሚቀይርበትንም ሁኔታ እያየን ነው ፣ይህ ሰው የማልማትም ሆነ የማጥፋት ሚና እንዳለው ያሳያል። ሰዎች የላቀ እድገትን ሲያስመዘግቡ በመታደስ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል። የዚህን ተቃራኒ ይዘው የተጓዙ ከሆነ ማርጀትን ይዘው እየተጓዙ ስለሆነ በመታደስ መኖር አለብን።

የተወደዳችሁ ምእመናን የክርስትና ሃይማኖት የመጨረሻ ግብ የፍጥረታት መታደስ ነው። ከሞት በኋላ ትንሳኤ ፤ ከዚያም እንከን የሌለው ጣዕመ ሕይወት አለ ብሎ ሰውን ለዘለዓለማዊ ሕዳሴ ማብቃት ነው። ከዚህ አንጻር ሰው ማርጀት ሳይሆን መታደስ እንዳለበት ፤ እግዚአብሔር የፍጥረቱን መታደስ በሰማይ ብቻ ሳይሆን በምድርም ስለሚፈልገው ዘመንን እየለወጠ ይመግበናል። ስለዚህ እኛስ ለመታደስ ተዘጋጅተናል ወይ ብለን ራሳችንን መጠየቅና መልሱን ማግኘት ወሳኝ ነው። ለመታደስም ቆራጥ ውሳኔ በመወሰን አዲሱን ዘመን ልንጠቀምበት ይገባናል።

እኛ ኢትዮጵያን ቀድሞ እንበልጣቸው ከነበሩት ሁሉ ወደ ኋላ እየቀረን ከችግሮቻችን ላለመላቀቅ ውል የገባን እስኪመስል ድረስ እየቀጠልንበት ነው። ኢትዮጵያን የመሰለች ሀገር ይዘን እንዲህ ሆነን ስንገኝ ከስንፍናችን በቀን ምንም የጎደለን እንደሌለ ሌሎችም የሚያውቁት ነው። ስለዚህ ለእኔ ለእኔ በመባባል የሕዝባችንን ሰቆቃ አናስረዝም። ኢትዮጵያ የሁሉም ናት ፤ በእኩልነት እና በአንድነት ሀገራችንን እናድስ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ከ3000 ዓመታት ውስጥ ከእግዚአብሔር ተለይተን አናውቅም። በዚህም ተጠቃሚዎች እንጂ ተገጂዎች የሆንበት ጊዜ የለም ፤ ሕዝቡም በፈጣሪው የሚያምን ስለሆነ ከዚህ ውጭ እንምራው ብንል ግን ያጋጠመንን ችግር ማስቀጠል ነው የሚሆነው ስለዚህ የሁሉም መነሻ ውጣዊ አእምሮአችኝ ነውና እሱን በማደስ በአዲሱ ዓመት ሀገራችንን እንድናድስ ጥሪ እናቀርባለን።

አዲሱ ዘመን በውይይት ፣ መለያየትን በአንድነት ፣ አለመግባባትን በእርቅ ፈትተን ሁላችንም በመታደስ ማማ ላይ የቆመ ማኅበረሰብን ለመገንባት ጥረት እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።"

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

ጳጕሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#በዓለ_ርዕሰ_ዐውደ_ዓመት_ዮሐንስ_ወቅዱስ_ራጉኤል
#እንኳን_አደረሳቹ

#ዐዲስ_ዓመት

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የመሸጋገሪያው ዕለት በየዓመቱ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ የዘመን መለወጫ፣ እንቁጣጣሽ፣ ሌላም መጠሪያ ስሞቹ ናቸው፡፡ በግእዝ ርእሰ ዐውደ ዓመትም ይባላል፡፡ ይህ በዓል የዓመት መጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን በየዓመቱ ወሮች በመጀመሪያ ቀን ይከበራል፡፡ ያን ጊዜ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር እኩል 12 ሰዓት ይሆናል፡፡ ዓመቱን ጠንቅቀው ሲቆጥሩ 364 ቀናት ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “ለዘመን መታወቂያው ይሆን ዘንድ ፀሐይና ጨረቃ ከዋክብትንም ፈጠረ” ይላልና /ሔኖክ. 21፥49/፡፡ በሌላ በኩልም በዘመነ ኖኅ በፍል ውኃ አጥለቅልቆ በኃጢአት ሕይወት ይኖሩ የነበሩት የኖኅ ዘመን ሰዎች ቀጥቶ ካጠፋ በኋላ ከንፍር ውኃ ምድር የተገለጠችበት ወር ነው /ኩፋሌ. 7፥1/፡፡ “በመጀመሪያው ወር ምድር ታየች የንፍር ውኃም ከምድር ደረቀ” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መሠረት አድርገው የአቡሻኸር ሊቃውንት የዘመን መለወጫን ታሪካዊ አመጣጥ ያስቀምጣሉ፡፡


የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀኖናዊ ሥርዐት ያጠኑ ሊቃውንት ደግሞ አዲስ ዓመት መስከረም አንድ ቀን መሆኑን አስመልክተው በክታባቸው እንዳስቀመጡት በአራቱ ወንጌላውያን ዘመኑን ይከፍሉታል፡፡ ምክንያቱም በዘመነ ዮሐንስ ተፀንሶ በዘመነ ማቴዎስ ተወልዶአል፡፡ በዘመነ ማርቆስ ተጠምቋል፡፡ በዘመነ ሉቃስ ተሰቅሎ ዓለምን ከፍዳና ከመርገም ነጻ አውጥቷል፤ እያሉ ታሪካዊ ሐረጋቸውን ጠብቆ አራቱ ወንጌላውያን ተከትለው ያለ እንቅፋት እንደሚጓዙ ያስረዳሉ::

#እንቁጣጣሽ

ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሳባ የጠቢቡ ሰሎሞንን ዝና ሰምታ ኢየሩሳሌም ተጉዛ ስትመለስ “እንቁ ለጣትሽ /ለጣትሽ እንቁ/ በማለት ከእንቁ የተሠራ የጣት ቀለበት ንጉሥ ሰሎሞን እጅ መንሻ እንዲሆናት አበርክቶላት ነበርና ይህን ታሪክ መነሻ አድርገው “እንቁጣጣሽ” የሚለው ስያሜ ከዚያ እንደመጣ የታሪክ ድርሳናት ያስረዱናል ፡፡ በኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ዕለት ምድሪቱ በክረምቱ ዝናብ ረስርሳ ድርቀቷ ተወግዶ በአርንጓዴ እጸዋት ተውባ ሜዳው፣ ሸለቆውና ተራራው በአደይ አበባ ተንቆጥቁጠው የሚታዩበት ወቅት በመሆኑ ዕለቱ “እንቁጣጣሽ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በዚህ ወቅት ሕፃናትና ልጃገረዶች ነጭ ባሕላዊ ልብስ በመልበስ ለምለም ቄጤማና አደይ አበባ በመያዝ በአካባቢያቸው በመዞር አዲስ ዘመን መበሠሩን “እንኳን አደረሳችሁ” በማለት በቸርነቱ ዓመታትን የሚያፈራርቀውን እግዚአብሔርን በዝማሬ ያመሰግናሉ፡፡

መልካም_አዲስ_ዓመት

#ራጉኤል ሊቀ መላእክት:-

ራጉኤል ማለት የብርሃናት አለቃ ማለት ነው። የብርሃናት አለቃ ሲባል ፀሐይን፣ ጨረቃን እና ከዋክብትን በማመላለስና ለሰው ልጆች፣ ለአዝርዕት፣ ለእንስሳት፣ ለአራዊት ሁሉ ብርሃንን የሚመግብ ነው ማለት ነው። አንድም ራጉኤል ማለት የሚበቀል ማለት ነው። የሚበቀል ነው ማለት በቀል የሚገባው ለጠላት ነው የሰው ልጅ ጠላት ደግሞ ዲያብሎስ ነው፤ ስለሆነም ቅዱስ ራጉኤል እግዚአብሔርን አምነው ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው በፍርሐተ እግዚአብሔር አምልኮቱን ለሚፈጽሙ ሁሉ ጠላት ዲያብሎስን የሚያርቅላቸው ወደ እነርሱም ፈጥኖ በመድረስ የሚታደጋቸው ነው ማለት ነው። ሔኖክ 6:4፡፡ አንድም ራጉኤል ማለት የኃያላን ኃያል እግዚአብሔር ማለት ነው። የኃያላን ኃያል ያለው የእግዚአብሔርን ኃያልነት ከምድር ፍጥረታት ዘንድ ኃያል ከሚባሉት ሁሉ ሊገለጽ የማይችል ኃያልነቱን ለመግለጽ ኃያልነቱም ከ እስከ የሌለው መሆኑን ለመግለጽ የተቀመጠ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ኃያል የኃያላን ኃያል መሆኑን የሚገልጽ ትርጉም አለው።

አንድም ራጉኤል ማለት ጽኑ እግዚአብሔር ማለት ነው። የእግዚአብሔር አምላክን ጽኑነት ለማጉላት ሲል ጽኑ አለው። እግዚአብሔር የማይወላውል የማይዋዥቅ የማይከዳ ነው ለማለትም ሲል ይህ ስያሜ ተሰጠው። የእግዚአብሔርን ጽናት የሚያሳይ ትርጉም ያለው ስያሜ ነው። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ራጉኤል አገልግሎት እና ስልጣን፡- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከዚህ ዓለም በ64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ ሥጋዋ ወደ ዕፀ ሕይወት ሲነጠቅ (ሲያርፍ) አብሮ ለሔደው እና ስጋዋን በእጣን ሲያጥን ለነበረው ለፍቁረ እግዚ ለቅዱስ ዮሐንስ ኅብስትን የመገበ መልአክ ነው።  በብርሃናት ሁሉ ላይ የሰለጠነ መልአክ ነው። ከአዳም ሰባተኛ ትውልድ የሆነ በእግዚአብሔር ፊት ግሩም ያማረ ሥራው የሰመረ እስከዛሬ የሞት ወጥመድ ያልያዘው የሞት ጥላ ያላረፈበት ነብዩ ሔኖክ "ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው" ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡

እግዚአብሔር ዓለምን ይቆጣጠር ዘንድ የሾመው ታላቅና ቅዱስ መልአክ ነው። (ድርሳነ ራጉኤል ዘ ጥቅምት ገጽ 23) አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ለመተካት ዓለምን የመለወጥ ሥልጣን የተሰጠው ቅዱስ መልአክ ነው። ከእግዚአብሔር የጌትነቱ አዳራሽ ይገባና ይወጣ ዘንድ ስልጣን ያለው ከኪሩቤልና ከሱራፌል ጋር ከፈጣሪ የጌትነት ዙፋን ፊት የሚቆም ነው። ሎጥን ሚስቱንና ልጆቹን ከእሳተ ጎመራ ያዳነ የበለአምን እርግማን ወደ በረከት የለወጠ እርሱ ነው።  በቅዱስ ራጉኤል ስነ ሥዕል ላይ የምናየው ይህ ባለ አራት እራስ ንስር ከአርባእቱ ኪሩቤል አንዱ ገጸ ንስር ነው። የሥላሴን የጌትነት ዙፋን የሚሸከሙ አርባዕቱ እንስሳት ናቸው። የሚሸከሙት ሲባል ጫማ የሰውን ልጅ እንደሚሸከመው እንጂ ችለውትስ አይደለም። እነርሱም የሰው ገጽ፣ የእንስሳ ገጽ፣ የንስር ገጽ እና የአንበሳ ገጽ ያላቸው ናቸው። ይህንንም ነብዩ ሕዝቅኤል "ለእያንዳንዱ እንስሳትም የተለያዩ አራት ገጾች ነበሩት። ይህውም በስተቀኝ በኩል የእንስሳ መልክ፣ በስተ ግራ የላም ገጽ፣ በበስተ ኋላም የንስር ገጽ የሚመስሉ ነበሩ" ብሏል ሕዝ 1፡6-13፡፡ ከዚህ የምንገነዘበው ነገር ቢኖር አራት ገጽ ካላቸው ኪሩቤል መካከል አንዱ ንስር መሆኑን ነው። ቅዱስ ራጉኤል ደግሞ የእነዚህ ኪሩቤል አለቃቸው (የጌትነቱ ዙፋን ጠባቂ) በመሆኑ በዚህ ምክንያት ማለትም እነርሱ ዙፋኑን ተሸካሚ እርሱ ደግሞ አጠገባቸው መቆሙ መንበሩን ጠባቂ በመሆኑ በዚህ አይነት የአገልግሎት ድርሻ አብረው ሊሳሉ ችለዋል። ቅዱስ ያሬድም በድጓው "አርባእቱ እንስሳ አልቄንጥሩ እንደሚባለው ንስር ፊት ለፊት አይታዩም አንዱም በመራቸው ይሔዳሉ እነርሱም እያንዳንዳቸው አራት ገጽ ሲኖራቸው ሳያርፉና ሳይደክሙ የሚያመሰግኑ ናቸው" በማለት ጽፏል።

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
​​መናፍቃን ማንኛውንም ጥያቄ ሲጠይቅወት መልሱ ይኸው ሼር አድርጉት መረጃው ለሁሉም ይድረስ
፨፨፨ለመናፍቃን የማያዳግም መልስ፨፨፨
የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ

1: ሥለ ሥላሴ

የእግዚአብሔር አንድነትና ሶስትነት:-
✞ዘፍ 1:26 ዘፍ 3:22
✞ዘፍ 11:18 ዘፍ 18:1-2
✞ኢሳ 48:26 ማቴ 3:16-17
✞ማቴ 28:19 ሉቃ 1:35
✞ዮሐ 7:28-29 ዮሐ 14:25-26
✞የሐ.ስራ 3:14 1ኛ ቆሮ 12:4-7
✞2ኛ ቆሮ 13:14 ኤፌ 4:4-7

2: የእመቤታችን ቅድስናዋ ፣ ክብሯ ፣ ድንግልናዋንና
አማላጅነቷ:-

✞መዝ 9:11 መዝ 13:10
✞መዝ 44:9 መዝ 86:5
✞መዝ 131:13 መዝ 44:2
✞መኃ 4:12 ኢሳ 7:14
✞ኢሳ 49:23 ኢሳ 60:14
✞ማቴ 1:23 ሉቃ 1:28
✞ሉቃ 1:42 ዮሐ 2:1-11
✞ዮሐ 19:16 ሮሜ 11:26-27
✞2ኛ ቆሮ 11:2 ራዕ 12:16

3: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ እንጅ አማላጅ
አይደለም፡-

✞ዘፍ 3:22 1ኛ ሳሙ 16:1
✞ኢሳ 9:6 ዳን 7:14
✞ሆሴ 13:4 ዘካ 9:9-10
✞ሚክ 5:2 ሉቃ 1:32-33
✞ዮሐ 10:30 ሉቃ 2:12
✞ዮሐ 14:7 ሮሜ 9:5
✞ቆላ 2:9-10 ቲቶ 2:11-13
✞ዕብ 1:3-4 ዕብ 1:10-11
✞1ኛ ጴጥ 3:23 1ኛ ዮሐ 2:23
✞ራእ 3:22 ራእ 22:12-13

4: ስለታቦት እና ፅላት

✞ዘፃ 24:12 ዘፃ 25:10
✞ዘፃ 25:21 ዘፃ 26:34
✞ዘፃ 31:18 ዘፃ 32:15
✞ዘፃ 34:1 ዘፃ 34:28
✞ዘፃ 37:1 ዘፃ 40:20
✞መኃ 7:89 ኢያ 3:3
ኢያ 7:6 2ኛ ቆሮ 6:16

5: ሥለ ፆም የመጽሐፍ ቅዱስ ማሥረጃ:-

✞ዘፃ 34:28 ዘፃ 9:9
✞ሳሙ 20:26 1ሳሙ 7:6
✞1ሳሙ 31:13 2ኛ ሳሙ 1:12
✞2ኛ ሳሙ12:16 ዕዝ 8:21
✞ዕዝ 68:10 ዕዝ 108:24
✞ኢሳ 48:3 ኤር 36:9
✞ዳን 9:3 ዳን 20:2-3
✞ኢዩኤ 2:14 ኢዩኤ 2:12
✞ዩና 3:5 ማቴ 4:2
✞ማቴ 6:16:18 ማቴ 9:14-15
✞ማቴ 17:21 ማር 2:18
✞ማር 9:29 ሉቃ 2:37
✞ሉቃ 18:12 የሐ.ስራ 13:3 ✞የሐ.ስራ 14:23 2ኛ ቆሮ
11:17

6: መስቀል በመጽሐፍ ቅዲስ:-

✞ማቴ 10:38 ማቴ 16:20
✞ማር 8:34 የሐ.ስራ 5:30
✞1ኛ ቆሮ 1:18 ገላ 3:13
✞ገላ 6:13 ፊል 2:8
✞ፊል 3:18

7: ጥምቀትን በተመለከተ:-

✞ሕዝ 36:25 ማቴ 3:5-6
✞ማቴ 26:19-20 ማር 1:4-5
✞ማር 16:16 ሉቃ 3:21
✞ዮሐ 3:5 ዮሐ 3:22
✞ኤፌ 4:5 ገላ 3:26-27
✞የሐዋ 19:4 የሐዋ 18:8
✞የሐዋ 13:24 የሐዋ 10:47
✞የሐዋ 9:18  1ኛ ቆሮ 1:16
✞1ኛ ቆሮ 10 :2 1ኛ ቆሮ 12:13

8:ስዕለትን በተመለከተ:-

✞ዘኁ 28:20 ዘኁ 21:2
✞ዘፃ 23:21 መሳ 11:30
✞መዝ 49:14 መዝ 75:11
✞1ኛ ሳሙ 1:11 መክ 5:4-5
✞ዮና 2:10 ናሆ 1:15
✞የሐዋ 18:18

9: ፃድቃን ሠማዕታት ያማልዳሉ:-

✞ዘፍ 18:17-18 ዘፍ 18:23:24
✞ዘፍ 20:7 ዘፍ 33:3
✞ዘፍ 42:6 1ኛ ሳሙ 28 :14
✞2ኛ ሳሙ 1:2 2ኛ ነገ 1:13
✞2ኛ ነገ 2:15 2ኛ ነገ 4:9
✞2ኛ ነገ 4:32-35 መዝ 88:34
✞ማቴ 18:18 ዮሐ 20:23
✞የሐዋ 10:25 የሐዋ 16 :29
✞1ቆሮ 6:1-2 ፊሊ 4:6
✞1ኛጢሞ 5:17 ያዕ 5:14
✞ራዕ 14:13

10: መላዕክት ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ:-

✞መዝ 148:2 ኢሳ 6:3
✞ማቴ 4:12 ማቴ 18:10
✞ማቴ 25:31 ማር 8:38
✞ራእ 1:11 ሉቃ 1:19

11: መላዕክት ፀሎታችን ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ:-

✞ጦቢ 12:15 ሉቃ 15:10
✞የሐዋ 10:4 እዩብ 25:3
✞ኤር 33:22 ዳን 7:10
✞ሄኖ 10:1 ራዕ 5:11

12:ለመላዕክት የአክብሮት ስግደት ይገባል:-

✞ዘፍ 19:1 ማኅ 22:31
✞ኢያ 5:14 ዳን 8:16-17
13:መላዕክት አብሣሪያን ናቸው:-
✞ዘፍ 16:11 ሉቃ 1:13
✞ሉቃ 1:19 ሉቃ 1:30-31
✞ሉቃ 2:10-11

14:መላዕክት በአደጋ ጊዜ ፈጥነው ይደረሣሉ:-

✞ዘፍ 22:11-12 መዝ 90:11-12
✞ዳን 6:22 ዳን 10:13
✞ማቴ 2:13 የሐዋ 5:19-20
✞የሐዋ 12:7

15: ፀበል መርጨት ያስፈልጋል:-
✞ዘኁ 19:20

በተጨማሪም ሁላችንም እያንዳንዱን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ደጋግመን እናንብበው እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋልና ጥበቡን ይስጠን
አሜን

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
የቁባቱን በድን የቆራጠው ካህን! (መሳ. 19-20)


በእስራኤል ልጆች ታሪክ ውስጥ አያሌ አስከፊ ተግባራት ተከናውነዋል፤ ዛሬ የምናየው ይህ አንዱ ነው፤ “በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ በሌለበት ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ማዶ የተቀመጠ ሌዋዊ ነበረ፤” (መሳ. 19፥1) ይላል፣ በመሳፍንት መጽሐፍ ውስጥ ከተቀመጡት የብንያም ሰዎችን የሥነ ምግባር ብልሹነትና በምላጭ ጫፍ ላይ መቆማቸውን ከሚያሳዩት ታሪኮች አንዱን ለመተረክ ሲነሳ።

በርግጥ ሌዋዊው ካህን ቁባቱን ፍለጋ ከኤፍሬም ወደ ቤተልሔም መሄዱ፣ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባቱን ያሳያል፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው ተግባር አልነበረም፤ በተጨማሪም፣ እግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች መሳፍንትን የሰጠው፣ ርሱ ብቻውን በነርሱ ላይ ሊነግሥ ነበር። ነገር ግን ለጌታ ከመታዘዝ ይልቅ፣ የሃይማኖት መሪዎቿ ድካምና ኃጢአት እያየለባቸውና እየባሰባቸው ሲሄድ በተደጋጋሚ እንመለከታለን።


ካህኑ ቁባቱን አጊኝቶአት ይዞ፣ ከቤተልሔም ወደ ኤፍሬም በሚመለስበት ጊዜ እግረ መንገዱን ጊብዓ በምትባል በብንያማውያን ከተማ መሸበትና አደረ።

የከተማዪቱ ሰዎች ግን ልክ እንደ ሰዶምና ገሞራ ሰዎች፥ እጅግ አስጸያፊ ተግባር የሚፈጸሙ ነበሩ። በእንግድነት ወደ ነርሱ የመጡትን ካህንና ቁባቱን ከማስተናገድ ይልቅ፣ በካህኑ ላይ የሰዶማዊነት ነውር ሊፈጽሙበት ፈልገው አሳዳሪውን ሽማግሌ፣ እደ ሰዶም ሰዎች ግድ አሉት። ሽማግሌው፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር፥ እባካችሁ፥ አታድርጉ፤ ይህ ሰው ወደ ቤቴ ገብቶአልና እንደዚህ ያለ ኃጢአት አትሥሩ። ድንግል ልጄና የእርሱም ቁባት፥ እነሆ፥ አሉ፥ አሁንም አወጣቸዋለሁ፤ አዋርዱአቸው፤ እንደ ወደዳችሁም አድርጉባቸው፤ ነገር ግን በዚህ ሰው ላይ እንደዚህ ያለ ኃጢአት አታድርጉ” (19፥23-24) ብሎ ቢለምናቸውም፣ ሰዎቹ ግን ሊሰሙ ፈጽሞ አልወደዱም። በመጨረሻም ግን ሽማግሌው የገዛ ሴት ልጁንና የሌዋዊውን ቁባት አውጥቶ ሰጣቸው።

ሰዎቹ፣ የሌዋዊው ቁባት እስክትሞት ድረስ በመፈራረቅ ሌሊቱን ሙሉ አመነዘሩባት። ሽማግሌው እንደ ሎጥ፣ ራሱን ከማኅበረ ሰቡ ርኩሰት የጠበቀና ያገለለ መኾኑ እጅግ ያስደንቃል፤ ተግባራቸውንም “ክፉ ነገር” ብሎ መጥራቱ ይኸንኑ ያሳያል፤ ሌዋዊው ግን ያሳየው ግዴለሽነትና ደንታ ቢስነት ያሳዝናል።

ሌዋዊው የቁባቱን ሬሳ 12 ቦታ ቆራረጠና ለእያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ አንዳንዱን ቁራጭ ላከ። ይህም ነገር የ12ቱን ነገዶች ቁጣ ቀሰቀሰና ምን እንደ ተፈጸመ ለማየት መጡ። ታሪኩን በሰሙ ጊዜ፥ ይህን ኃጢአት የፈጸሙትን ሰዎች አሳልፈው እንዲሰጧቸው ብንያማውያንን ጠየቁ። ብንያማውያን ተቃወሙ፥ የርስ በርስ ጦርነት ተነሣ። በጦርነቱም 40000 እስራኤላውያንና 25100 ብንያማውያን ሞቱ። የብንያማውያን ሴቶችና ልጆች በሙሉ ተገደሉ። ከብንያም ነገድ በሙሉ የተረፉት 600 ሰዎች ብቻ ነበሩ።

ሌሎች እስራኤላውያን፥ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ የኾነው የብንያም ነገድ ሊጠፉ እንደ ኾነ ተገነዘቡ፤ ስለዚህ ለእነዚህ 600 ብንያማውያን 600 ሚስቶች የሚገኙበትን ዘዴ ፈጠሩ። በዚህም የብንያምን ነገድ ጨርሶ ከመጥፋት አዳኑት።

ሰዎች ራሳቸው የሚፈልጉትን ነገር ብቻ ሲያደርጉ፥ ኃጢአታቸው አድጎ በርካታ ሰዎችን እንደሚነካና እንደሚያጠፋ አይገነዘቡም። ኀጢአትና ኀጢአተኝነት የመዛመትና ሌላውን የመውረስ ጠባይ አለው፤ የጊብዓ ሰዎች ኃጢአት በሺህ የሚቆጠሩ የበርካታ እስራኤላውያንን ሞትና የብንያም ነገድን ወደ ውድመት የሚያደርስ ጥፋት አስከትሎ ነበር። የአንድ ካህን ሕገ እግዚአብሔር መጣስና የብንያም ነገድ ሰዶማዊነት መኾን፣ ፍጻሜውን መራራ አድርጎታል። ኀጢአት በማናቸውም መንገድ የፍጻሜ መንገዱ ጣፋጭ አይኾንም!

እንግዶችን በማስተናገድ አንዳንዶች ራሱ እግዚአብሔርን ሌሎች ደግሞ መላእክትን ተቀብለው ነበር፤ የብንያም ሰዎች ግን እንግዶቻቸውን ለነውር ተግባር ፈለጉ፡፡ ወንዶቹ ኀፍረተ ቢስና ፍትሕ አልባ ነበሩ፡፡ ምናልባት ታሪኩ ሊረሳ እንጂ ሊተረክ የሚገባው አይመስልም፤ ግን እንድንተርከው ታዝዘናል፡፡ የሴቲቱ ታሪክ አሳዛኝና ልብ ሰባሪ ነው፤ የሚቆምላትና የሚከላከልላት አልነበረም፡፡ ሌዋዊው ሊንከባከብ ከአባትዋ ቤት ቢያወጣትም፣ ነገር ግን ለርኩሳንና ለማይራሩ ሰዎች አሳልፎ ሰጣት፡፡ በዚያ ሙሉ ሌሊት የተፈጸመባትን ርኩሰት ማስተዋልና ርኅራኄ ሊያሳያት ሲገባ ግን አላደረገም፤ ብሎም የቀብር ክብርዋን በመንፈግ ሰውነቷን ቆራረጠው!

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ያሉ ታሪኮች መቀመጣቸው፣ ሰው ከእግዚአብሔር ፊትና ከአገዛዙ ሲለይ፤ በራሱም መንገድ መልካም መስሎ የታየውን የሚያደርግ ከኾነ ፍጻሜው ይኸው መኾኑን ያሳያል፡፡ ወዳጆቼ! ዛሬም በምድራችን ላይ የምንሰማቸው አያሌ ክፉ ተግባራት፣ ከዚህ እውነታ እምብዛም የራቁ አይደሉም! ከኀጢአታችን ለመታቀብና ለመተው፤ ብሎም ንስሐ ገብቶ ለመመለስ ፈቃደኞች ባልኾንን መጠን፣ የኀጢአት ፍሬና መከር መብላታችንና ማጨዳችን አይቀሬ ነው! “ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ፤ እርሱ ሰብሮናልና፥ እርሱም ይፈውሰናል፤ እርሱ መትቶናል፥ እርሱም ይጠግነናል።” (ሆሴ. 6፥1) የሚለው የጌታ ቃል ዛሬም ሕያው ነውና እንመለስ!

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ሥር ሰዳችሁ እደጉ 
                                                  
Size:- 68.3MB
Length:-1:13:47
       
     በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ሰው አዝርእትን አትክልትን ይመስላል። አዝርእት ተዘርተው፣ አብቅለው፣ አብበው፣ አፍርተው ከጎተራ ይቀመጣሉ። ሰውም ተጸንሶ፣ ተወልዶ፣ በመልካም ሥራ አብቦ፣ ፍሬ ትሩፋትን አፍርቶ ከመንግሥተ ሰማያት ይገባል።

ፍጥረታትን በጽሙና ሆነን ብንመረምራቸው ፍቅርን፣ ትሕትናን፣ ትዕግሥትንና የመሳሰሉትን እንማርባቸዋለን። ጊዜያችንን በሚጠቅም ነገር እናውለው። ሞት መኖሩን አስበን እንኑር። ከትላንት ዛሬ፣ ከዛሬ ነገ በሥነ ምግባር ልንሻሻል ይገባናል።

ሠናይ ጊዜ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (🌼 £itsum 🌼)
+ ስለቅዱሳንና ቅድስና ጥቂት +

በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳን ሲባል፡- ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ሰማዕታት፣ ሊቃውንት፣ መናንያን /ገዳማውያን/፣ ደጋግ ሰብአ ዓለም ይጠቀሳሉ፡፡ ቅዱሳን ዜግነትና ተቋማዊ አጥር ባይኖርባቸውም በልማድ እንደየሚከበሩበት ቦታ ስፋትና ጥበት አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ እየተባሉ ይለያሉ፡፡ የቅድስና አሰጣጡ አስቀድሞ በጉባኤ ደረጃ አልነበረም፡፡ ሰማዕታት የሆኑ እንደሆነ ምስክርነቱ የአደባባይ ነውና በቶሎ ቅድስና ያገኛሉ፡፡ አንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅና ቅዱስ ባስልዮስ ያሉ በአፍም በመጻፍም የገነኑ አበው ግብርና ቅድስናቸው ከመጉላቱ የተነሣ ከቤተ ክህነቱ ቀድሞ ምዕመኑ በቅድስና ጠርቷቸዋል፡፡ ቅድስናው በገቢረ ተአምርና በራእይ የሚገለጥም አለ፡፡

በዚህ ዘመን ግን ከሞላ ጎደል በሁሉም ሐዋርያዊ ትውፊትን በሚከተሉ አብያተ ክርስቲያናት ቅድስና በቃለ ሲኖዶስ ይሰጣል፡፡ የእኛም አካሄድ ተመሳሳይ ነው፡፡ አንድ አባት ቅዱስ ከተባለ በኋላ ስለሚደረገው ልዩ ልዩ ተግባር በ #ወልታ_ጽድቅ ወይም በዲያቆን ሰሎሞን #የኢትዮጵያ_ቤተ_ክርስቲያን_ወርቃማ_ዘመናት ወይም ደግሞ በዶ/ር ሐዲስ የሻነው የትምህርተ ሃይማኖት መጻሕፍት ማንበብ ይቻላል፡፡ ቅድስና በየጊዜው የሚጨመር ነው፤ አይቆምም፡፡ በሌላ በኩል በበጎ የሚነሣው አባት ላይ ከጊዜ በኋላ የሃይማኖት ህፀፅ የተገኘ እንደሆነ የሚታረምበት ዕድል ስለመኖሩ የአርጌንስ ታሪክና የእኛ ሲኖዶስ የግብፆችን የስንክሳር ስርዋጽ ያረመበት ድርጊት ይጠቁመናል፡፡

በ1960ዎቹ ተጀምሮ ሲካሄድ ቆይቶ እንደ መቀዛቀዝ ባለው የኦሪየንታል-ምሥራቃውያን ኢመደበኛ ንግግር የቅድስና አሰጣጥን፣ ማንና እንዴት ቅዱስ ይባል ማለትን ለነገረ መለኮትና ለታሪክ ምሁራን በመተው በግራ ቀኝ ወገኖች የተላለፈው ግዝት እንዲነሣ ሐሳብ ቀርቦ ነበረ፡፡ ሐሳቡ እስካሁን ዳር አልደረሰም ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያናችን በ1988 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ በተቋቋመ የጳጳሳትና የሊቃውንት ኮሚቴ የተዘጋቸው የእምነት፣ ሥርዓትና የውጭ ግንኙነት መጽሐፍ በኬልቄዶናውያን ላይ የተላለፈው ግዝት እንደማይነሣ፣ በእነርሱ ስር ያሉ አበውንም በቅድስና መቀበል እንደማይችል በአጽንዖት ገልጧል፡፡ ቀድመው በስንክሳራችን በገቡት የሃይማኖት ጀርባቸው ከወደ ኬልቄዶን በሚመዘዝ አበው ላይ ግን ያሳረፈው ውሳኔ የለም፡፡
---

( ደብተራ በአማን ነጸረ )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
2024/09/23 04:30:53
Back to Top
HTML Embed Code: