Telegram Web Link
በአንዳንድ ጉዳዮች "በግብፅ ቤተክርስቲያን ስለሚደረግ በእኛም ይደረግ አታካብዱ" የሚሉ ሰዎች አሉ። ጉዳዮችን ከባለጉዳዮች ለይተን ብንመረምራቸው መልካም ነው። ግብርን ከገባሪው ለይተን ብንነቅፍ ጥሩ ነበረ። ይህ አልሆነም። በጊዜው ጊዜ እንዲሆን ምኞቴ ነው። አለማቀፋዊ ሲኖዶስ የወሰነውን ጉዳይ አምስቱም አኃት አብያተ ክርስቲያን ይተገብሩታል። በአካባቢያዊ ሲኖዶስ የተወሰነ ጉዳይ በተለይ ሥርዓት ተኮር የሆነው ግን በአካባቢ ይተገበራል። አለማቀፋዊ ሲኖዶስ የሚባሉት እንደ ጉባኤ ኒቅያ፣ እንደ ጉባኤ ኤፌሶን፣ እንደ ጉባኤ ቁስጥንጥንያ ያሉት ናቸው። አካባቢያዊ የሚባሉት እንደ ጉባኤ ዕንቆራ፣ እንደ ጉባኤ አንጾኪያ፣ እንደ ጉባኤ ግንግራ ያሉት ናቸው።

በዶግማዊ ጉዳዮች ሁለቱም ጉባኤያት በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት አላቸው። ሥርዓት ተኮር ጉዳዮች ላይ ግን የእኛን እንደ ግብፅ ካልሆነ የግብፅን እንደእኛ ካልሆነ ማለት አይገባንም። ከነጫማ ተገብቶ የሚቀደስበት ሀገር ሊኖር ይችላል። እኛጋም ከእነጫማችን እንግባ አይባልም። እኛጋ ታቦት አለን። ታቦት የሌላቸው ይኖራሉ። እኛም አይኑረን አይባልም። መንጦላዕቱን ገልጠው ለምእመናን ሁሉ እያሳዩ የሚቀድሱ አሉ። እኛጋ ይህ የለም። እንደነርሱ ካልሆነ አንልም። የእነርሱን ምክንያት አላውቅም። የእኛ ግን መጋረጃ መኖሩ ጌታ በአደባባይ ሲሰቀል ፀሐይ ለመጨለሟ ምሳሌ ነው።

አንዳንድ ጉዳዮችን ደግሞ ከግለሰቦች ብንለያቸው መልካም ነው። ግለሰቦች ሕግ ሆነው አያውቁም። እነርሱም የሚዳኙበትን ሕግ ነው ማየት ያለብን። አቡነ እገሌ የተባሉ ጳጳስ የፈቀዱት ነገር ሁሉ ትክክል ነው አይባልም። መጽሐፍ ላይ ያለውን ከተናገሩ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ብለን እንመርቃቸዋለን። ከተጻፈው ሥርዓት ያፈነገጠ ነገር ከተናገሩ ግን ተቀባይነት አይኖራቸውም። ጉባኤያዊት ቤተክርስቲያን በሥርዓት በቀኖና የደነገገችውን ጉዳይ ማንም ቢናገረው ደስ ይለናል። ከተቃወመው ደግሞ እርሱም በሥርዓቱ ይመዘናል እንጂ የሰውየው ግላዊ ንግግር እንደ ሥርዓት ተደርጎ መያዝ የለበትም።

አንዳንድ ነገርን ደግሞ ከድርጊቱ ጀርባ ያለውን ኅሊና ብናየው ጥሩ ነው። ያልተለመደ አዲስ ነገር ሰው ይዞ ሲወጣ ፍቅርን ለመግለጥ ነው ወይስ ትኩረት ለመሳብ??? ትኩረት ለመሳብ ከሆነ መጻሕፍተ መነኮሳት ላይ እንደተማማርነው አቦ አቦ ለመባል ቀልብ ለማግኘት ምንም እንዳናደርግ ታዘናል። ውጫዊ የታይታ (Show) ሥራዎች ላይ ባናተኩር መልካም ነው። እግዚአብሔር የሚወደውን ውሳጣዊ ሥራ እንሥራ።

© በትረ ማርያም አበባው

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ልብሰ ተክህኖን ክህነት የሌለው ሰው መንካትና ማጠብ አይችልም። ሥርዓት አይደለም። በቅንነት አንዳንድ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት አድርጋችሁት ከነበረ ከእንግዲህ እንዳታደርጉ ትምህርት ይሁናችሁ። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፰ ላይ ከዲያቆናት፣ ከቀሳውስትና፣ ከዚያ በላይ ከሆኑት በስተቀር ንዋየ ቅድሳትን እንዲነኩ አልተፈቀደም። ስለዚህ ካህናት ሆይ ክህነት የሌላቸው ሰዎች ንዋየ ቅድሳትን እንዲነኩና እንዲያጥቡ አታድርጉ።

© በትረ ማርያም አበባው

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም #መድኀኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ #ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከሚነግሡት ዓመታዊ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ ነሐሴ ፳፬ ቀን የሚከብሩት የጻድቁ አባታችን አቡነ #ተክለ_ሃይማኖት
የቅድስት እናታችን #ክርስቶስሠምራ እና የቅዱስ #ቶማስ ዘመርዓስ በዓለ ንግሥ ነው(ታሪኩን ከታች ይመልከቱ) ፡፡
በደብራችን ታቦታተ ሕጉን በማውጣት መከበር የተጀመረው #በ፲፱፻፹፪(1982) ዓ.ም እንደሆነ አባቶቻችን ይናገራሉ፡፡አሁንም የአባቶቻችንን ፈለግ የተከተልን እኛ ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ለማግኘት በየዓመቱ በድምቀት እናከብረዋለን፡፡

✤✤✤
ነሐሴ ፳፬(24) ቀን የሦስቱም ቅዱሳን በዓለ እረፍታቸው ነው
ታሪከ አቡነ #ተክለሃይማኖት ወቅድስት #ክርስቶስ ሠምራ እንዲሁም አርዮስን መልስ ለመስጠት በቅርጫርት ውስጥ ተጉዞ ለሄደው እና ከ 318 ሊቃውንት አንዱ የሆንው የቅዱስ #ቶማስ ዘመርዓስ ታሪክ::

✤✤✤

✤✤✤ #አቡነ_ተክለሃይማኖት ✤✤✤
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ #ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት #እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ ዓ.ም ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው«አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለውሥላሴ ን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡
በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በአሥራ አምስት ዓመታቸው ከ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ /ጌርሎስ/ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ በዚህም ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጓደኞቻቸው ጋር ወደ ዱር አደን ሄደው ሳለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ ለኢትዮጵያ ውያን ክርስቲያኖች ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ መረጣቸው። ስማቸውንም «ተክለ ኃሃይማኖት» አለው፡፡ ትርጓሜውም የኃይማኖት ፍሬ ማለት ነው፡፡
አባታችንም ሐዋርያዊ ጉዟቸውን ሲጀምሩ /ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ ፳፰ ቁ ፪ - ፫/ ትሕትና በተሞላበትና በተሰበረ ልብ ወደ ፈጣሪያቸው ከለመኑ በኋላ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሃይማኖት መልሰዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ፀሐይ ተብለዋል፡፡
አባታችን በዳዊት ፀሎት ከነቢያት ምስጋና ሌሊቱን ሙሉ ይተጉ ነበር በያንዳንዱ መዝሙርም 10፣ 10 ስግደትን ይሰግዱ ነበር፡፡ በሕዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው (አወጣቸው) ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበረን “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት አጥነዋል ፡፡ በሐይቅ 10 ዓመት በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡ ለ22 ዓመት ቆመው በመፀለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው #ለ7 ዓመት በፀሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በፀሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ አባታችን ባረፉ 54 ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም ለአባታችን ለአቡነ #ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ# ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል ፡፡
በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለእኚህ ዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው ለጻድቁ ተክለ ሃይማኖት በየዓመቱ በነሐሴ ፳፬ ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፡፡ እኛንም ከጻድቁ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
✤✤✤
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
✤✤✤ #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ ✤✤✤
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ ሀገሯ #ሸዋ_ቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌየ ሲሆን እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ደጋግ ወላጆቿ ከአባተቷ ቅዱስ ደረሳኒ ከእናቷ ከቅድስት ዕሌኒ በግንቦት 12 ቀን ተወለደች፡፡ እነርሱም ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ከወለዱ በኋላ በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በማስተማር ስላሳደጓት ከልጅነቷ ጀምራ በሥነ ምግባር፣ በሃይማኖት የታነጸች በመልኳም እጅግ ውብና ያማረች ሆነች፡፡ ባደገችም ጊዜ ለአቅመ ሔዋን ስትደርስ የንጉሥ ባለሟል ለሆነ ስሙ ሠምረ ጊዮርጊስ ለተባለ ደግ ሰው በሕግ አጋቧት፡፡ ከሕግ ባሏ ከሠምረ ጊዮርጊስም ዐሥራ ሁለት ልጆችን ወለደች፡፡ ከእነዚህም መካከል አስሩ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ፡፡
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዐፄ #ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት የነበረች ኢትዮጵያዊት ጻድቅ ስለነበረች ንጉሠ ነገሥቱ ዐፄ ገብረ መስቀል በትዳሯ፣ በሥነ ምግሯና በሃይማኖቷ በሁለመናዋ የተመሰገነች መሆኗን ዝናዋን ስለሰማ ‹‹#በጸሎትሽ አስቢኝ›› በማለት ከአገልጋዮቹ ውስጥ እርሷን እንዲያገለግሏት፣ 174 አገልጋዮቸን ላከላት፡፡ ብዙ ፈረስና በቅሎ እንዲሁም ለነገሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማም ላከላት፡፡ ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ‹‹ለዓላማዬ እንቅፋትና ውዳሴ ከንቱ ይሆንብኛል እንደዚሁም ወርቁ ጌጡ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ነገር ግን እነዚህን አገልጋዮች ምን አደርጋቸዋለው?›› እያለች ወደ እግዚአብሔር አመለከተች፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ #ሚካኤል ፊቱ እንደ ፀሐይ እያበራ ሦስት ኅብስት በእጁ ይዞ መጥቶ ‹‹የእግዚአብሔር ባለሟል ክርስቶስ ሠምራ ሆይ! እነሆ ይህን #ኅብስት ተመገቢ እግዚአብሔር በቸርነቱ ብዛት ሰጥቶሻል›› አላት፡፡ እርሷም ፈጣሪዋን አመስግና ኅብስቱን ከመልአኩ እጅ ተቀብላ ተመገበች፣ መዓዛ ጣዕሙም ሰውነቷን አለመለመው፡፡ በዚህም የተነሳ እስከ ሦስት ቀን እህል ሳትበላ ውኃ ሳትጠጣ ቆየች ኃይለ መንፈስ ቅዱስ በሰውነቷ አድሮባታልና፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፡- ከአገልጋዮቿ መካከል አንዷ ምግባሯ የከፋ ነበርና በጣም ስላበሳጨቻት በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት፡፡ ያም የእሳት ትንታግ እስከ ጉሮሮዋ ዘለቀና አገልጋይዋን ገደላት፡፡ በዚህ ጊዜ ብጽዕት ክርስቶስ ሠምራ ደንግጣ ወደ ሌላ ክፍል ገባችና ኃጢአቷን ለእግዚአብሔር እየተናዘዘች እጅግ በጣም አዝና ጥፋቷ እንደ ጸጸታትና እግዚአብሔር አምላክም በእጇ የሞተችውን አገልጋይዋን ከሥጋዋ አዋሕዶ ቢያሥነሳላት ያላትን ገንዘብና ሀብት ትታ ባላት ዘመኗ ሁሉ አገልጋዩ እንደምትሆን ብጽዓት (ስዕለት) አደረገች፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ አገልጋይዋን ከሞት አሥነሳለት፡፡ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ‹‹ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከእኔ ከባሪያው ያላራቀ አምላክ ይክበር ይመስገን›› ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔርን ካመሰገነች በኋላ አስቀድማ የገባችውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኩስናዋን አዘጋጀች፡፡ ሕፃን ልጅዋንም ይዛ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደች፡፡ ስትሄድም በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግሯ ከመንገዱ ብዛት ከእንቅፋቱም የተነሳ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሟ መሬት ለመሬት እየፈሰሰ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ደረሰችና አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብሰ ምንኩስናዋን ለብሳ ከሴቶች ገዳም ገባች፡፡ ይዛው የተሰደደችውን ሕፃን ግን ወንድ ስለሆነ ከደጅ ላይ አስቀምጣው ስለገባች ሕፃኑ አምርሮ ሲያለቅስ ከመነኮሳቱ አንዲቷ ሕፃኑ ሲያለቅስ ከሚያድር ብላ ወደ በአዓቷ ልታስገባው ስትል የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወስዶ በገነት አስቀመጠው፡፡ ታኅሣሥ 29 ቀን ተወልዶ በ 3 ዓመቱ ታኅሣሥ 12 ቀን ብሔረ ብፁዓን ገባ፡፡
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ቅዱስ ሚካኤል ካለችበት በዓት አውጥቶ በክንፉ ተሸክሞ ከጣና ደሴት አደረሳት፡፡ ከዚያም ሰውነቷ ተበሳስቶ የባሕር ዓሣ መመላለሻ እስከሚሆን ድረስ እንደ ተተከለ ዓምድ ሆና ሳትወጣ ባሕሩ ውስጥ ዐሥራ ሁለት ዓመት ቆማ ስትጸልይ ኖረች፡፡ ከዐሥራ ሁለት ዓመት በኋላም ጌታችን ተገልጦላት #ቃልኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ከዚህ በኋላ ሕይወቷን በሙሉ በታላቅ ተጋድሎ ስታሳልፍ ጌታችንም ከቅድስት እናቱ ጋር ሆኖ በየጊዜው ይጎበኛት ነበር፡፡ ቅዱስ ሚካኤልንም የሁልጊዜ ጠባቂዋ አድጎ ሰጥቷታል፡፡ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ብሔረ ብፁዓን እየሄደች ከዚያ ከሚኖሩ ቅዱሳን ጋር እስከ ሰባት ቀን ድረስ ስትነጋገር ትቆይ ነበር፡፡
#ሄኖክና #ኤልያስ ወዳሉበት ወደ ብሔረ ሕያዋንም እየሄደች ትመለስ ነበር፡፡
✤✣✤
ከዕለታት አንድ ቀን በጣና ማዶ መዕቀበ እግዚእ የሚባል አንድ ሰው ነበረና መልአከ ጽልመት ወደ እርሱ ዘንድ መጥቶ ‹‹ፈጣሪውን ክደህ ይህን ዕፅ በሰውነትህ ብትቀብር ሞትና እርጅና አያገኝህም›› አለው፡፡ እርሱም ለዚህ ክፉ ሀሳቡ ፈቃደኝነቱን ስለገለጠለት መልአከ ጽልመት በሰውነቱ ውስጥ ዕፁን ቀብሮለት ሄደ፡፡ መዕቀበ እግዚእም ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘንድ መጥቶ ‹‹ሰላም እልሻለው በጸሎትሽም ተማጽኛለሁ፣ የፈጠረኝን እግዚአብሔርን እስከ መካድ ደርሼ ብዙ ኃጢአት ሰርቻለውና›› አላት፡፡ ቅድስት እናታችንም በዚያን ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደችና ስለዚህ ሰው በፍጹም ኀዘን በመሆን ወደ ፈጣሪዋ አመለከተች፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታችን መጥቶ ‹‹ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ! ለዚህ ሰው ምሕረት አይገባውም፣ የምገድል የማድን የምቀስፍ ይቅር የምል አምላክ እኔ እያለሁ ፈጣሪውን ክዶ በሰይጣን ምክር ተማምኖአልና›› አላት፡፡ በዚህ ጊዜ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ጌታችንን እግሩ ሥር ተደፍታ ‹‹አንተ መዓትህ የራቀ ምህረትህ የበዛ ፈጣሪ ሆይ! ማርልኝ ሁሉ ይቻልሃልና…›› ስትል አጥብቃ ለመነችው፡፡ ሁሉን የፈጠረ ጌታችንም ‹‹ስለ አንቺ ፍቅር ምሬልሻለው›› አላት፡፡ ከዚህ በኋላ ማዕቀበ እግዚእን ጠርታ ‹‹ኃጢአትህን ይቅር ብሎሃል›› አለችው፡፡ ከዚህ በኋላ ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ የተቀበረውን ዕፅ ሰውነቱን ፍቃ ስታወጣለት ደሙ እንደ ቦይ ውኃ ወረደ፤ በዚያው ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ከማኅበረ ሰማዕታት ጋር አንድ ሆነች፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ #ስድስት ክንፎችን ሰጥቷታል፡፡ በበዓለ ጥምቀት ወቅት ሙሴ፣ ኤልያስና መጥመወቁ ዮሐንስ ጌታ የተጠመቀበትን የዮርዳኖስን ውኃ አምጥተው ሙሴ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ቀኝ እጇን፣ ኤልያስ ግራ እጇን ይዘዋት ዮሐንስ ውኃውን በራሷዋ ላይ አፍስሶ አጥምቀዋታል፡፡ ከጌታችን ጥምቀት በኋላ እንደዚህ ዓይነት መንገድ የተጠመቀ ማንም የለም፡፡ እነርሱም ጓንጉት በምትባል ገዳም ውስጥ የገዳም አስተዳዳሪ እንደምትሆንና እጅግ ብዙ ተከታዮች እንደሚኖሯት ትንቢት ነግረዋት ወደ ሰማይ ዐርገዋል፡፡
የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ምልጃና ጸሎት አይለየን
+++
✤✤✤ #ቅዱስ_ቶማስ_ዘመርዓስ ✤✤✤
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
የመርዓስ ኤጵስ ቆጶስ የነበረው አባት አባ ቶማስ ክርስቶስን በማመን በጾም፣ በጸሎት፣ በሰጊድ፣ ቀንና ሌሊት በመትጋት ለድኆችና ለምስኪኖችም በመራራት ተጠምዶ የሚኖር ነበር። በዚህ ፅናቱ የክብር ባለቤት ጌታችን መርዓስ ለሚባል አገር ኤጲስ ቆጶስ ይሆን ዘንድ መንጋውንም ይጠብቅ ዘንድ መረጠው አባታችን ቶማስም ሐዋርያዊ ተልዕኮውን እየፈፀመ፣ ሕዝቡን እየመራ ሳለ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሱ ላይ፣ በአጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ላይም ተነሳባቸው፣ ክርስቲያኖችንም ያሰቃያቸው ጀመር በአንድ ወቅት ከመኳንንቶች አንዱ የነበረው፣ ቅዱስ ቶማስን ወደ እርሱ ያቀርቡት ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ እነርሱም እየደበደቡ በምድር ላይ እየጎተቱ ወሰዱት ደሙም እንደ ውኃ ፈሰሰ ከዚህም በኋላ መኮንኑ ቅዱስ ቶማስን ለአማልክት ስገድ አለው ቅዱሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት «እኔ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለረከሱ ጣኦታት አልሰግድም ለረከሱ ጣዖታት የሚሰግድ ሁሉ የተረገመ ነውና» በዚህም ጊዜ መኮንንኑ በጣም ተቆጥቶ እጅግ የበዛ ስቃይን አሰቃየው የነዳጅ ድፍድፍን አፍልተው በላዩ በአፉና በአፍንጫው እስከመጨመርም ደረሱ ልባቸው እንደ ድንጋያ የፀና ስለ ነበር ቅዱስ ቶማስን ገድለው ቶሎ ማሣረፍ አልፈለጉም ይልቁንም የስቃዩን ዘመን አስረዘሙ እንጂ እርሱም ስለ ስህተታቸው ይዘልፋቸው ነበር፣ እንደ ማይመልስም ሲገባቸው በጨለማ ቦታ ጣሉት በየዓመቱም ወደ እርሱ እየሄዱ ከሕዋሳቱ አንድ፣ አንዱን ይቆርጡ ነበር፡፡
በዚህም ለሃያ ሁለት(፳፪) ዓመት ቆየ ሲቆይ ግን አፍንጫውን፣ ከንፈሮቹን፣ ጆሮዎቹን፣ እጆቹንና እግሮቹን ቆርጠው ነበር፤ በዚህም ምክንያት የአገሬው ሰው ሞቷል ብለው አስበው በየዓመቱ መታሰቢያ ያደርጉለት ነበር ይህ ለምን ሳይሞት ቢሉ ጊዜው ሲረዝም ቢሞት ነው እንጂ እስካሁንማ ይመጣ ነበር ብለው ስላሰቡ ነበር፤ ነገር ግን ከሕዋሳቶቹ አብዛኛው ክፍል ቆርጠው ቢጥሉትም አካሉ ግን ተቆራርጦ ሲጣል አንዲት ሴት አየችው፣ ይህችም ሴት በሌሊት ወደርሱ ተሠውራ በመሔድ ትመግበው ነበር፡፡
ጻድቅ ቈስጠንጢኖስም እስከነገሠና የቀናች የክርስቶስን ሃይማኖት ክብር እስከገለጥ ድረስ እንዲህ ሲሰቃይ ኖረ፡፡
#ቈስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ ስለክርስቶስ በመታመን የታሠሩ እስረኞች ሁሉ እንዲፈቱ በማዘዙ ሁሉም ተፈቱ፡፡ ቅዱስ ቶማስ ግን የተጣለበት ቦታ፤ በሕይወት ያለም ስላልመሠላቸው አላወጡትም ነበር፤ ነገር ግን ይህን አዋጅ ትመግበው የነበረችው ሴት ሰምታ ነበርና ወደ ካህናቱ ዘንድ ሄዳ ስለ ቅዱስ ቶማስ ሃያ ሁለት ዓመት በዚያ ስለመኖሩ ነገረቻቸው ቦታውንም አመለከተቻቸው እነርሱም ባገኙት ጊዜ አንስተው ተሸከሙት እየዘመሩና እያመሰገኑም ወደ ቤተ ክርስቲያን አደረሱት በቤተ መቅደስ ፊት ለፊት በወንበሩ ላይ አስቀመጡት ምእመናንም ሁሉ ወደርሱ እየመጡ ከርሱ ይባረኩና የተቆረጡ ሕዋሳቱንም ይሳለሙ ነበር፡፡ ከቦታ ቦታ ይዘዋወር የነበረውም በቅርጫት ኹኖ በዘህያ ላይ ተጭኖ ነው፡፡

ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ የከበሩ ፫፻፲፰ ኤጲስ ቆጶሳትን (ሠለስቱ ምዕት) የአንድነት ጕባኤን በኒቂያ አገር በሰበሰበ ጊዜ ይህ አባት (ቅዱስ ቶማስ) ከሠለስቱ ምዕት አንዱ ነበር፤ ወደ ኒቅያ ጕባኤ በቅርጫት ሁኖ በአህያ ተጭኖ እየሄደ መሆኑን አርዮሳውያን ሲሰሙ፤ ቶማስማ በጕባኤው ከተገኘ ተከራክሮ ይረታናል አንችለውም በማለት መንገድ ላይ ባደረበት ይዘውት ይጓዙት የነበሩትን አህዮች በጨለማ በሰይፍ መተዋቸዋል፤ ነገር ግን ሌሊት ሊነጋጋ ሲል ለመንገድ ሲነሱ ቶማስ በተዓምራት አግልጋይ ረድኡን የተቆረጡትን የአህያዎቹን አንገታቸውን ከሰውነታቸው አጋጥመው ይነሳሉ ብሎ ሲያዘው የአንዱን አህያ ከሌላኛው አህያ ቢያጋጥመውም ቅሉ አህዮቹ ሕይወት አግኝተው ጕባኤ ኒቅያ አድርሰውታል፤ በዚያም አርዮስን መልስ እስኪያጣ ድረስ በጽናት ሲከራከረውና መልስ ሲያሳጠው የጕባኤው ሊቀ መንበር ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እስኪደነቅ ድረስ በማየቱ ሃይመኖትስ የእነ ቶማስ ዘመርዓስ ነች ብሎ አጽንቶ ወስኗል፡፡ በጕባኤውም አርዮስን ተከራክረው ከረቱ በኋላ አውግዘው ለይተውታል፤ ከዚህ በኋላ መንፈስ ቅዱስ እንዳስተማራቸውና እንደመራቸው የሃይማኖትን ትምህርት በአንደበታቸው ተናገሩ፤ ሕግና ሥርዐትን ሥጋዊና፤ መንፈሳዊ ፍርድንም ሰሩ። ቅዱስ ቶማስ ወደ መንበረ ሢመቱ ከተመለሰ በኋላ ካህናቱና መንጋዎቹን ሁሉ ሰብስቦ አነበበላቸው እርሱንም እንዲያስተውሉት እንዲጠበቁትም በመጠበቅም እንዲጸኑ አዘዛቸው፡፡ ይህ አባት ለ፵ ዓመት ያህል በሢመቱ አገልግሎ በነሐሴ ፳፬ ቀን አርፋል፡
በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#ደብረ_ሊባኖስ

ደብረ ሊባኖስ ገዳም በሰሜን ሸዋ ደብረ ሊባኖስ ወረዳ የሚገኝ ገዳም ሲሆን የጥንት ሰሙ #ደብረ_አስቦ ነበር። ገዳሙ የተቋቋመው በአራተኛው ክፍለ ዘመን #በአቡነ_ሊባኖስ አማካኝነት ነው። አቡነ ሊባኖስ በቦታው በጸሎት ተወስነው ሲኖሩ ከእርሳቸው በኋላ #ሌላ_ታላቅ_ሐዋርያ እንደሚመጣና ቦታውም በርሱ እንደሚከብር ነገር ግን ለመታሰቢያ ቦታው በስማቸው እንደሚጠራ ከእግዚአብሔር ተነገራቸው። በዚህ ምክንያት ለ700 ዓመታት ያህል ጠፍ ሆኖ ኖሯል።

ሌሎች የታሪክ ምንጮች እንደሚሉት አባ ሊባኖስ ከሔዱ በኋላ አባ ዘመደ ሊቃኖስ የተባሉ አባት ወደ ቦታው እንደ መጡ፤ ከርሳቸውም በኋላ አባ ነገደ እስራኤል በኋላም አባ ዘድንግል በየዘመናቸው አያሌ የትሩፋት ሥራዎችን ሠርተውበታል።

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ ደብረ አስቦ ሲመጡ ሐረስ የተባለ ጠንቋይ ቦታውን ወስዶት እንደነበር ይነገራል። ወደ ዋሻው ሲገቡ "እንተ ሶበ ጸዋዕክዎ ለእግዚአብሔር እድኅን እምፀርየ፤ ወይባልሐኒ እምጸላዕትየ ምንስዋን" የሚለውን የዳዊት መዝሙር ይጸልዩ ነበር። ሐረስም ይህንን ሰምቶ አካባቢውን ጥሎ ጠፋ።  ጻድቁም ቦታውን ባርከው በአት አድርገውታል።

አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህ ገዳም በተጋድሎ መኖራቸው በየአካባቢው እየተሰማ ብዙ መነኮሳት ተሰባሰቡ። እርሳቸውም እመቤታችንን ይወዱ ስለነበር በዋሻዋ እኩሌታ በሰሌን ጋርደው ታቦተ ማርያምን አኑረው በእኩሌታዋ ደግሞ እርሳቸው ከዐሥራ አምስት ደቀ መዝሙሮቻቸው ጋር ይኖሩ ነበር።

በዐፄ ሰይፈ አረእድ ዘመነ መንግሥት /1336-1364/ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተቀበሩበት ዋሻ በመናዱ ለዕጨጌ ሕዝቅያስ አቡነ ተክለሃይማኖት በራእይ በገለጡላቸው መሠረት ዐፅማቸው ግንቦት 12 ቀን ፈልሶ ቤተ መቅደሱ ወደ ተሠራበት አካባቢ መጥቷል።

ደብረ ሊባኖስ እየተባለ ስሙ ገኖ መጠራት የጀመረው ከ15ኛው ምእት በተለይም ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ /1426 -1460 ዓ.ም/ ጀምሮ እንደሆነ ይነገራል።

የገዳሙ ዋና ሕንጻ ከኢትዮጵያ ነገሥታት ብዙዎቹ ያማረ በመሰላቸው ጊዜያቸው በፈቀደላቸው ጥበብ ሕንጻውን አሠርተዋል። ለምሳሌ የመጀመሪያውን ሕንጻ ያሳነፁት በ1280 የነገሡት አጼ ይኩኖ አምላክ ሲሆኑ፤ ሁለተኛው ደግሞ በ1405 ዓ.ም የነገሡት አጼ ይስሐቅ ነበሩ። እንዲሁም በ1804 ዓ.ም በወሰን ሰገድ ፤ በ1876 ዓ.ም አጼ ዮሐንስ፤ በ1900 ዓ.ም በዳግማዊ ምኒልክ እንደገና ታንጿል።

የሥፍራው ገደላማ አቀማመጥ እና የአፈሩ የመሸሽ ባሕሪ ለሕንጻው የማይስማማ በመሆኑ ግንባታው ለብዙ ጊዜ ሊያገለግል አልቻለም።

በመጨረሻም በቀዳማዊ  ኃይለ ሥላሴ ዘመን ከጥልቅ የግንባታ ጥናት በኋላ ተሠርቶ ኅዳር 9, 1955 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ ተመረቀ።

#በተስፋህ_ያመነውን#በቃል_ኪዳንህ_የተማጸነውን፤ ሥጋህን የቆረስክበትን ደምህን ያፈሰስክበትንም #ቦታ_እጅ_የነሳውን ሁሉ #ከሞተ_ነፍስ_አድንልሀለሁ፤ ከዚህ ቦታ #በተስፋ_ጸንተው_በኪዳንህ_ተማጽነው የሚኖሩ ልጆችህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሀለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል።

@Niigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
እንደዚህ ያሉትን እወቋቸው 
                                                  
Size:- 27.8MB
Length:-1:19:49
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
1ኛ. የፍሥሓ ያዜን የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ የልብ ወለድ መጽሐፍ እውነት አድርገው የያዙ ሰዎች ያሳዝኑኛል።

2ኛ. ኢትዮጵያን ከዓለም ሁሉ በንጽሕና የተለየች ቅድስት ሀገር እንደሆነች የሚናገሩ ሞኞችም ያሳዝኑኛል። ኢትዮጵያ ማለትኮ አሁን ላይ ከየትኛውም ሀገር በበለጠ ሰው በቋንቋ በብሔር እየተለየ የሚጨፈጨፍባት፣ የሰባት ዓመት ሕፃን የሚደፈርባት፣ የሁለት ዓመት ሕፃን የሚታፈንባት አሳዛኝ ሀገር ናት። እንኳን የዓለም ብርሃን ልትሆን ጨለማው በርትቶባት እየማቀቀች ያለች ሀገር ናት።

3ኛ. የካህናትን፣ የጳጳሳትን ችግሮች ጠቅሰው ምእመኑን አስኮብልለው ለራሳቸው ዓላማ የሚያታልሉ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚባሉ ነቀዞች አሉ።

4ኛ. ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ሥጋዊ ሞትን የሚፈራ ለትክክለኛ ነገር ሰማዕትነትን የማይወድ ሆዳም ማኅበር ነው። ሥጋዊ ምቾትን ፈልጎ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ተደብቆ የሚኖር የፈሪዎች ስብስብ ነው።

5ኛ. ለችግሮች መፍትሔ መስጠት የምንችለው እኛው ተመካክረን እንጂ ከእኛ ውጭ የሆነ ቴዎድሮስን በመጠበቅ እኛ ማድረግ የምንችለውን ነገር ሳናደርግ በማለፍ አይደለም።

6ኛ. ቴዎድሮስን የሚያነግሥ እግዚአብሔር ነው። ከእግዚአብሔር በላይ እኛ ካላነገሥነው ብላችሁ ልባችሁ ውልቅ ያለ ሰዎች አትልፉ። ግላዊ ፍላጎታችሁን በቴዎድሮስ አታሳቡ።

7ኛ. አለቃ አያሌው አቡነ ጳውሎስን አውግዘዋል የሚሉ አስቂኝ ሰዎችም አሉ። ቄስ ጳጳስን የማውገዝ ሥልጣን የለውም። ዐይነ ሥውርም ቄስ መሆን አይገባውም።

8ኛ. የኢትዮጵያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ታሪካዊ ስለሆነ እንወደዋለን። ሃይማኖታዊ ግን አይደለም። ስለዚህ በምንወደው ባንዲራ ሕዝብን ማጭበርበር ቢቆም።

ከዚህ የነቀዘ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ስብስብ ራሳችሁን አድኑ።

© በትረ ማርያም አበባው

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/09/21 05:53:21
Back to Top
HTML Embed Code: