Telegram Web Link
#እንኳን_አደረሳቹሁ ፡፡

በዓለ ፍልሰታ ወዕርገታ ለማርያም   ወፍልሰተ አጽሙ ለሊቀ  ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት

ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡
እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው።
የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤  ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለ መኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።

ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ  እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ  ከሀገረ ስብከቱ  (ሕንድ) ወደ   ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።
    ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው።
       ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።

በዚህችም ዕለት ከፋርስ ወደ ልዳ የሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍለሰተ አጽም ሆኗል፡፡

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
በአንዳንድ ጉዳዮች "በግብፅ ቤተክርስቲያን ስለሚደረግ በእኛም ይደረግ አታካብዱ" የሚሉ ሰዎች አሉ። ጉዳዮችን ከባለጉዳዮች ለይተን ብንመረምራቸው መልካም ነው። ግብርን ከገባሪው ለይተን ብንነቅፍ ጥሩ ነበረ። ይህ አልሆነም። በጊዜው ጊዜ እንዲሆን ምኞቴ ነው። አለማቀፋዊ ሲኖዶስ የወሰነውን ጉዳይ አምስቱም አኃት አብያተ ክርስቲያን ይተገብሩታል። በአካባቢያዊ ሲኖዶስ የተወሰነ ጉዳይ በተለይ ሥርዓት ተኮር የሆነው ግን በአካባቢ ይተገበራል። አለማቀፋዊ ሲኖዶስ የሚባሉት እንደ ጉባኤ ኒቅያ፣ እንደ ጉባኤ ኤፌሶን፣ እንደ ጉባኤ ቁስጥንጥንያ ያሉት ናቸው። አካባቢያዊ የሚባሉት እንደ ጉባኤ ዕንቆራ፣ እንደ ጉባኤ አንጾኪያ፣ እንደ ጉባኤ ግንግራ ያሉት ናቸው።

በዶግማዊ ጉዳዮች ሁለቱም ጉባኤያት በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት አላቸው። ሥርዓት ተኮር ጉዳዮች ላይ ግን የእኛን እንደ ግብፅ ካልሆነ የግብፅን እንደእኛ ካልሆነ ማለት አይገባንም። ከነጫማ ተገብቶ የሚቀደስበት ሀገር ሊኖር ይችላል። እኛጋም ከእነጫማችን እንግባ አይባልም። እኛጋ ታቦት አለን። ታቦት የሌላቸው ይኖራሉ። እኛም አይኑረን አይባልም። መንጦላዕቱን ገልጠው ለምእመናን ሁሉ እያሳዩ የሚቀድሱ አሉ። እኛጋ ይህ የለም። እንደነርሱ ካልሆነ አንልም። የእነርሱን ምክንያት አላውቅም። የእኛ ግን መጋረጃ መኖሩ ጌታ በአደባባይ ሲሰቀል ፀሐይ ለመጨለሟ ምሳሌ ነው።

አንዳንድ ጉዳዮችን ደግሞ ከግለሰቦች ብንለያቸው መልካም ነው። ግለሰቦች ሕግ ሆነው አያውቁም። እነርሱም የሚዳኙበትን ሕግ ነው ማየት ያለብን። አቡነ እገሌ የተባሉ ጳጳስ የፈቀዱት ነገር ሁሉ ትክክል ነው አይባልም። መጽሐፍ ላይ ያለውን ከተናገሩ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ብለን እንመርቃቸዋለን። ከተጻፈው ሥርዓት ያፈነገጠ ነገር ከተናገሩ ግን ተቀባይነት አይኖራቸውም። ጉባኤያዊት ቤተክርስቲያን በሥርዓት በቀኖና የደነገገችውን ጉዳይ ማንም ቢናገረው ደስ ይለናል። ከተቃወመው ደግሞ እርሱም በሥርዓቱ ይመዘናል እንጂ የሰውየው ግላዊ ንግግር እንደ ሥርዓት ተደርጎ መያዝ የለበትም።

አንዳንድ ነገርን ደግሞ ከድርጊቱ ጀርባ ያለውን ኅሊና ብናየው ጥሩ ነው። ያልተለመደ አዲስ ነገር ሰው ይዞ ሲወጣ ፍቅርን ለመግለጥ ነው ወይስ ትኩረት ለመሳብ??? ትኩረት ለመሳብ ከሆነ መጻሕፍተ መነኮሳት ላይ እንደተማማርነው አቦ አቦ ለመባል ቀልብ ለማግኘት ምንም እንዳናደርግ ታዘናል። ውጫዊ የታይታ (Show) ሥራዎች ላይ ባናተኩር መልካም ነው። እግዚአብሔር የሚወደውን ውሳጣዊ ሥራ እንሥራ።

© በትረ ማርያም አበባው

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ልብሰ ተክህኖን ክህነት የሌለው ሰው መንካትና ማጠብ አይችልም። ሥርዓት አይደለም። በቅንነት አንዳንድ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት አድርጋችሁት ከነበረ ከእንግዲህ እንዳታደርጉ ትምህርት ይሁናችሁ። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፰ ላይ ከዲያቆናት፣ ከቀሳውስትና፣ ከዚያ በላይ ከሆኑት በስተቀር ንዋየ ቅድሳትን እንዲነኩ አልተፈቀደም። ስለዚህ ካህናት ሆይ ክህነት የሌላቸው ሰዎች ንዋየ ቅድሳትን እንዲነኩና እንዲያጥቡ አታድርጉ።

© በትረ ማርያም አበባው

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#በደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም #መድኀኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ #ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከሚነግሡት ዓመታዊ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ ነሐሴ ፳፬ ቀን የሚከብሩት የጻድቁ አባታችን አቡነ #ተክለ_ሃይማኖት
የቅድስት እናታችን #ክርስቶስሠምራ እና የቅዱስ #ቶማስ ዘመርዓስ በዓለ ንግሥ ነው(ታሪኩን ከታች ይመልከቱ) ፡፡
በደብራችን ታቦታተ ሕጉን በማውጣት መከበር የተጀመረው #በ፲፱፻፹፪(1982) ዓ.ም እንደሆነ አባቶቻችን ይናገራሉ፡፡አሁንም የአባቶቻችንን ፈለግ የተከተልን እኛ ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ለማግኘት በየዓመቱ በድምቀት እናከብረዋለን፡፡

✤✤✤
ነሐሴ ፳፬(24) ቀን የሦስቱም ቅዱሳን በዓለ እረፍታቸው ነው
ታሪከ አቡነ #ተክለሃይማኖት ወቅድስት #ክርስቶስ ሠምራ እንዲሁም አርዮስን መልስ ለመስጠት በቅርጫርት ውስጥ ተጉዞ ለሄደው እና ከ 318 ሊቃውንት አንዱ የሆንው የቅዱስ #ቶማስ ዘመርዓስ ታሪክ::

✤✤✤

✤✤✤ #አቡነ_ተክለሃይማኖት ✤✤✤
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ #ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት #እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ ዓ.ም ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው«አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለውሥላሴ ን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡
በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በአሥራ አምስት ዓመታቸው ከ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ /ጌርሎስ/ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ በዚህም ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከጓደኞቻቸው ጋር ወደ ዱር አደን ሄደው ሳለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ ለኢትዮጵያ ውያን ክርስቲያኖች ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ መረጣቸው። ስማቸውንም «ተክለ ኃሃይማኖት» አለው፡፡ ትርጓሜውም የኃይማኖት ፍሬ ማለት ነው፡፡
አባታችንም ሐዋርያዊ ጉዟቸውን ሲጀምሩ /ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ ፳፰ ቁ ፪ - ፫/ ትሕትና በተሞላበትና በተሰበረ ልብ ወደ ፈጣሪያቸው ከለመኑ በኋላ በልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሃይማኖት መልሰዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ፀሐይ ተብለዋል፡፡
አባታችን በዳዊት ፀሎት ከነቢያት ምስጋና ሌሊቱን ሙሉ ይተጉ ነበር በያንዳንዱ መዝሙርም 10፣ 10 ስግደትን ይሰግዱ ነበር፡፡ በሕዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው (አወጣቸው) ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበረን “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት አጥነዋል ፡፡ በሐይቅ 10 ዓመት በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡ ለ22 ዓመት ቆመው በመፀለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው #ለ7 ዓመት በፀሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በፀሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ አባታችን ባረፉ 54 ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም ለአባታችን ለአቡነ #ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ# ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል ፡፡
በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለእኚህ ዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው ለጻድቁ ተክለ ሃይማኖት በየዓመቱ በነሐሴ ፳፬ ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፡፡ እኛንም ከጻድቁ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/
✤✤✤
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
✤✤✤ #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ ✤✤✤
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ ሀገሯ #ሸዋ_ቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌየ ሲሆን እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ደጋግ ወላጆቿ ከአባተቷ ቅዱስ ደረሳኒ ከእናቷ ከቅድስት ዕሌኒ በግንቦት 12 ቀን ተወለደች፡፡ እነርሱም ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ከወለዱ በኋላ በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በማስተማር ስላሳደጓት ከልጅነቷ ጀምራ በሥነ ምግባር፣ በሃይማኖት የታነጸች በመልኳም እጅግ ውብና ያማረች ሆነች፡፡ ባደገችም ጊዜ ለአቅመ ሔዋን ስትደርስ የንጉሥ ባለሟል ለሆነ ስሙ ሠምረ ጊዮርጊስ ለተባለ ደግ ሰው በሕግ አጋቧት፡፡ ከሕግ ባሏ ከሠምረ ጊዮርጊስም ዐሥራ ሁለት ልጆችን ወለደች፡፡ ከእነዚህም መካከል አስሩ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ፡፡
እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዐፄ #ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት የነበረች ኢትዮጵያዊት ጻድቅ ስለነበረች ንጉሠ ነገሥቱ ዐፄ ገብረ መስቀል በትዳሯ፣ በሥነ ምግሯና በሃይማኖቷ በሁለመናዋ የተመሰገነች መሆኗን ዝናዋን ስለሰማ ‹‹#በጸሎትሽ አስቢኝ›› በማለት ከአገልጋዮቹ ውስጥ እርሷን እንዲያገለግሏት፣ 174 አገልጋዮቸን ላከላት፡፡ ብዙ ፈረስና በቅሎ እንዲሁም ለነገሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማም ላከላት፡፡ ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ‹‹ለዓላማዬ እንቅፋትና ውዳሴ ከንቱ ይሆንብኛል እንደዚሁም ወርቁ ጌጡ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ነገር ግን እነዚህን አገልጋዮች ምን አደርጋቸዋለው?›› እያለች ወደ እግዚአብሔር አመለከተች፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ #ሚካኤል ፊቱ እንደ ፀሐይ እያበራ ሦስት ኅብስት በእጁ ይዞ መጥቶ ‹‹የእግዚአብሔር ባለሟል ክርስቶስ ሠምራ ሆይ! እነሆ ይህን #ኅብስት ተመገቢ እግዚአብሔር በቸርነቱ ብዛት ሰጥቶሻል›› አላት፡፡ እርሷም ፈጣሪዋን አመስግና ኅብስቱን ከመልአኩ እጅ ተቀብላ ተመገበች፣ መዓዛ ጣዕሙም ሰውነቷን አለመለመው፡፡ በዚህም የተነሳ እስከ ሦስት ቀን እህል ሳትበላ ውኃ ሳትጠጣ ቆየች ኃይለ መንፈስ ቅዱስ በሰውነቷ አድሮባታልና፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፡- ከአገልጋዮቿ መካከል አንዷ ምግባሯ የከፋ ነበርና በጣም ስላበሳጨቻት በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት፡፡ ያም የእሳት ትንታግ እስከ ጉሮሮዋ ዘለቀና አገልጋይዋን ገደላት፡፡ በዚህ ጊዜ ብጽዕት ክርስቶስ ሠምራ ደንግጣ ወደ ሌላ ክፍል ገባችና ኃጢአቷን ለእግዚአብሔር እየተናዘዘች እጅግ በጣም አዝና ጥፋቷ እንደ ጸጸታትና እግዚአብሔር አምላክም በእጇ የሞተችውን አገልጋይዋን ከሥጋዋ አዋሕዶ ቢያሥነሳላት ያላትን ገንዘብና ሀብት ትታ ባላት ዘመኗ ሁሉ አገልጋዩ እንደምትሆን ብጽዓት (ስዕለት) አደረገች፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ አገልጋይዋን ከሞት አሥነሳለት፡፡ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ‹‹ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከእኔ ከባሪያው ያላራቀ አምላክ ይክበር ይመስገን›› ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔርን ካመሰገነች በኋላ አስቀድማ የገባችውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኩስናዋን አዘጋጀች፡፡ ሕፃን ልጅዋንም ይዛ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደች፡፡ ስትሄድም በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግሯ ከመንገዱ ብዛት ከእንቅፋቱም የተነሳ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሟ መሬት ለመሬት እየፈሰሰ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ደረሰችና አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብሰ ምንኩስናዋን ለብሳ ከሴቶች ገዳም ገባች፡፡ ይዛው የተሰደደችውን ሕፃን ግን ወንድ ስለሆነ ከደጅ ላይ አስቀምጣው ስለገባች ሕፃኑ አምርሮ ሲያለቅስ ከመነኮሳቱ አንዲቷ ሕፃኑ ሲያለቅስ ከሚያድር ብላ ወደ በአዓቷ ልታስገባው ስትል የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነጥቆ ወስዶ በገነት አስቀመጠው፡፡ ታኅሣሥ 29 ቀን ተወልዶ በ 3 ዓመቱ ታኅሣሥ 12 ቀን ብሔረ ብፁዓን ገባ፡፡
ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ቅዱስ ሚካኤል ካለችበት በዓት አውጥቶ በክንፉ ተሸክሞ ከጣና ደሴት አደረሳት፡፡ ከዚያም ሰውነቷ ተበሳስቶ የባሕር ዓሣ መመላለሻ እስከሚሆን ድረስ እንደ ተተከለ ዓምድ ሆና ሳትወጣ ባሕሩ ውስጥ ዐሥራ ሁለት ዓመት ቆማ ስትጸልይ ኖረች፡፡ ከዐሥራ ሁለት ዓመት በኋላም ጌታችን ተገልጦላት #ቃልኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ከዚህ በኋላ ሕይወቷን በሙሉ በታላቅ ተጋድሎ ስታሳልፍ ጌታችንም ከቅድስት እናቱ ጋር ሆኖ በየጊዜው ይጎበኛት ነበር፡፡ ቅዱስ ሚካኤልንም የሁልጊዜ ጠባቂዋ አድጎ ሰጥቷታል፡፡ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ብሔረ ብፁዓን እየሄደች ከዚያ ከሚኖሩ ቅዱሳን ጋር እስከ ሰባት ቀን ድረስ ስትነጋገር ትቆይ ነበር፡፡
#ሄኖክና #ኤልያስ ወዳሉበት ወደ ብሔረ ሕያዋንም እየሄደች ትመለስ ነበር፡፡
✤✣✤
ከዕለታት አንድ ቀን በጣና ማዶ መዕቀበ እግዚእ የሚባል አንድ ሰው ነበረና መልአከ ጽልመት ወደ እርሱ ዘንድ መጥቶ ‹‹ፈጣሪውን ክደህ ይህን ዕፅ በሰውነትህ ብትቀብር ሞትና እርጅና አያገኝህም›› አለው፡፡ እርሱም ለዚህ ክፉ ሀሳቡ ፈቃደኝነቱን ስለገለጠለት መልአከ ጽልመት በሰውነቱ ውስጥ ዕፁን ቀብሮለት ሄደ፡፡ መዕቀበ እግዚእም ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘንድ መጥቶ ‹‹ሰላም እልሻለው በጸሎትሽም ተማጽኛለሁ፣ የፈጠረኝን እግዚአብሔርን እስከ መካድ ደርሼ ብዙ ኃጢአት ሰርቻለውና›› አላት፡፡ ቅድስት እናታችንም በዚያን ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደችና ስለዚህ ሰው በፍጹም ኀዘን በመሆን ወደ ፈጣሪዋ አመለከተች፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታችን መጥቶ ‹‹ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ! ለዚህ ሰው ምሕረት አይገባውም፣ የምገድል የማድን የምቀስፍ ይቅር የምል አምላክ እኔ እያለሁ ፈጣሪውን ክዶ በሰይጣን ምክር ተማምኖአልና›› አላት፡፡ በዚህ ጊዜ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ጌታችንን እግሩ ሥር ተደፍታ ‹‹አንተ መዓትህ የራቀ ምህረትህ የበዛ ፈጣሪ ሆይ! ማርልኝ ሁሉ ይቻልሃልና…›› ስትል አጥብቃ ለመነችው፡፡ ሁሉን የፈጠረ ጌታችንም ‹‹ስለ አንቺ ፍቅር ምሬልሻለው›› አላት፡፡ ከዚህ በኋላ ማዕቀበ እግዚእን ጠርታ ‹‹ኃጢአትህን ይቅር ብሎሃል›› አለችው፡፡ ከዚህ በኋላ ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ የተቀበረውን ዕፅ ሰውነቱን ፍቃ ስታወጣለት ደሙ እንደ ቦይ ውኃ ወረደ፤ በዚያው ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ከማኅበረ ሰማዕታት ጋር አንድ ሆነች፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ #ስድስት ክንፎችን ሰጥቷታል፡፡ በበዓለ ጥምቀት ወቅት ሙሴ፣ ኤልያስና መጥመወቁ ዮሐንስ ጌታ የተጠመቀበትን የዮርዳኖስን ውኃ አምጥተው ሙሴ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ቀኝ እጇን፣ ኤልያስ ግራ እጇን ይዘዋት ዮሐንስ ውኃውን በራሷዋ ላይ አፍስሶ አጥምቀዋታል፡፡ ከጌታችን ጥምቀት በኋላ እንደዚህ ዓይነት መንገድ የተጠመቀ ማንም የለም፡፡ እነርሱም ጓንጉት በምትባል ገዳም ውስጥ የገዳም አስተዳዳሪ እንደምትሆንና እጅግ ብዙ ተከታዮች እንደሚኖሯት ትንቢት ነግረዋት ወደ ሰማይ ዐርገዋል፡፡
የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ምልጃና ጸሎት አይለየን
+++
✤✤✤ #ቅዱስ_ቶማስ_ዘመርዓስ ✤✤✤
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/09/25 14:17:22
Back to Top
HTML Embed Code: