Telegram Web Link
አንባብያን ሆይ! በመፃጉዕ ቦታ እኛ ብንሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልትድኑ ትወዳላችሁን? ብሎ ቢጠይቀን መልሳችን ምን ይሆን? ለራሳችን፣ ለማኅበረሰባችንና ለሀገራችን መለኮታዊውን ፈውስ በእውነት እንመኛለን ይሆን? ይህ ጥያቄ ከአካላዊው ድኅነት በዘለለ ለአእምሯዊ፣ ለስሜታዊና ለመንፈሳዊ ማንነታች ፈውስን መሻታችንን በጥልቀት ይመለከታል። እውነት ፈውስን እንፈልጋለን? ፍትሐዊነት የሰፈነበት፣ አቀመ ደካሞች መጠጊያ የሚያገኙበት፣ የተበደሉ የሚካሱበት ማኅበረሰብንስ እንናፍቃለን?

++++

ድኅነት ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቦቻችን፣ ለጎረቤቶቻችን፣ ለኅብረተሰባችን ብሎም ለሀገራችን ጭምር መሆኑን "ብቻ" በሌለበት የኦርቶዶክሳዊነት ትርጉም ውስጥ የምንረዳው እውነታ ሲሆን ልክ እንደ መፃጉዕ በእምነት ሆነን አዎ ጌታ ሆይ መዳን እንፈልጋለን ብለን ፈቀዳችንን በቅንነት ብንገልጽና አሳልፈን ብንሰጥ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ይገለጣል። አዎ አባት ሆይ ሕመምተኞች ነንና ፈውስህን እንፈልጋለን!

ሊቁ አውግስጢኖስ “እምነት ያላየኸውን ማመን ነው፣ የእምነት ሽልማት ደግሞ ያመንከውን ማየት ነው”[2] ብሎ እንደጻፈ። እኛ በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት መልካም ነገርን ፈውስን ለተጠማችው ምድራችን ተስፋ እንድናደርግ ያደርገናል። ይህንም በፍጹም እምነት ተስፋ ያደረግነው መልካም ነገር ሊቁ እንዳለው የእምነታችን ሽልማት ሆኖ የምናገኝው ሲሆን ነገር ግን ቅዱስ ያዕቆብ በመልእክቱ እንዳስተማረን እምነት ያለ ሥራ የሞተ መሆኑን ቆም ብለን ማጤን ይገባናል።

++++

‘ልባቸው የቆሰሉትን ይፈውሳል ፡ ሕማማቸውንም ይጠግናል’ መዝ ፻፵፯፥፫

++++

3. የጌታችን የኢየሱ ክርስቶስ ፈውስ (ዮሐ ፭፥፰)

‘ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ’

በዚህ ቁጥር ላይ የምናገኘው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ከላይ ለጠይቅነው ፈውስን የመሻት ጥያቄ የተሰጠ ታላቅ ምላሽ ነው። የጌታችን ትዕዛዝ የሻትነውን መልካም ነገር ለማግኘት ከምናደርገው ጥያቄና ጥረት ጋር በእጅጉ የሚስማማ ነው።

ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በአልጋ ላይ የነበረው መፃጉዕ እንደተነሳ በዘመናት ስቃይ ውስጥ የምንገኝ እኛና ማኅበረሰባችንም በእርሱ መለኮታዊ ኃይል እንነሳለን። ይኸውም የመነሳት፣ አልጋን ተሸክሞ የመሄድና የመለወጥ ሂደት በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በእውነተኛው ሐዋርያዊ ሥልጣነ ክህነት በሚከናወኑ በቅዱሳን ምስጢራት አማካኝነት የሚፈጸም ነው፡፡ በምሥጢረ ጥምቅት ንጽሕናን ገንዘብ እናደረጋለን ይኸውም ከጥላቻ ከመለያየትና ከመገፋፋት አውጥቶ አንድ የክርስቶስ አካል ያደርገናል። ቅዱስ ቁርባንም ዘወትር በክርስቶስ አካልነት ውስጥ እንድንሆን በማድረግ በአንድነትና በአብሮነት ያስተሳስረናል። ምሥጢረ ቀንዲልም ቁስላችንን ይጠግናል ከተኛንበትም አልጋ ያነሳናል። ሌሎችም ቅዱሳት ምሥጢራት ከክብር ወደ ክብር እንድናድግ ይረዱናል። በመሆኑም አንዲት ጥምቀትን የተጠመቅን ከአንድ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የተቀበልን ኦርቶዶክሳውያን በኅብረት በመመላለስ ለህዝባችንና ለሀገራችን መፍትሄዎች መሆን ይገባናል።

++++

ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ስለ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ባስተማረው ትምህርቱ “እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ የሕይወት ውኃ ምንጭ ይሆንላታል ወደ ዘላለም ሕይወትም የሚመራ የሕይወት ውኃ ምንጭ ይሆናል” [3] በማለት የቅዱሳት ምሥጢራትን ጥልቅ ትርጉም ይነግረናል። ቅዱሳት ምሥጢራት መንፈሳዊ ዕድገትና ለውጥ በማምጣት ያለምንም ልዩነትና አድልዎ ስለ እግዚአብሔር ልጆች ክብር፣ እኩልነትና ለውጥ በአንድነት እንድንቆም ይመሩናል።

በቤተሳይዳ የመጠመቂያ ሥፍራ የተከናወነውን ተአምራዊ ፈውስ ስናስብ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የሰጠው መለኮታዊ ትእዛዝ አካላዊ ፈውስን ብቻ ሳይሆን ከመንፈሳዊውና ከሥነልቦናዊ እሥራትም ነፃ የመውጣትን ጥሪ ያካተተ መሆኑን እንገነዘባለን። ይህንንም ጥሪ ተከትለን ፍትሐዊነት እንደ ወንዝ የሚፈስባት ሁሉም በነጻነትና በክብር የሚራመደባትን ምድር ለመገንባት በጋራ መሥራት ይገባናል።

++++

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች በዚህ ሳምንት እያሰብነው ያለው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የፈውስ ተአምራት ከመፃጉዕ ግለሰባዊ ማንነት በዘለለ በዘመናችን እኛን፣ ማኅበረሰባችንና ሀገራችንን የሚያጠቃልል ሰፊና ጥልቅ ትርጓሜ እንዳለው እናስተውል። እንደ ሀገር፣ ማኅበረሰብና ግለሰብ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራትና ድንቅ ነገር እንደሚያስፈልገን እንመን። ለሚያጋጥሙን የተለያዩ ህመሞቻችን ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛና ዘላቂ ፈውስ በፍጹም ማግኘት አንችልም።

በሀገራችን ውስጥ ከተፈጠረው የመለያየት፣ የመቃቃርና የኢ-ፍትሐዊነት ህመም ድኅነትን እናገኝ ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፈውስ የሚያስፈልገን ሲሆን የሚከፋፍሉንን እንቅፋቶች አስወግደን አንድ መሆን የምንችለው በእሱ ጸጋ ብቻ ነው።

እኛም እንደ ግለሰብ ከብዙ መከራዎች፣ ፍርሃቶችና ጥርጣሬዎች ጋር ትግል ላይ እንደሆንን ይታወቃል። ይህም ትግላችን አብቅቶ ፍጽም ምሉዕነት ያለውን ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፈውስ ያስፈልገናል። በዚህም ውስጥ እርሱ በመንገዳችን ሁሉ ከእኛ ጋር አብሮ እንዲጓዝ ፈተናዎቻችንን በእምነትና በድፍረት የምንጋፈጠበትን ኃይል እንዲሰጠን በፍጹም ትህትና በጾምና በጸሎት እንትጋ።

++++

‘የጠፋውን እፈልጋለሁ የባዘነውንም እመልሳለሁ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አጸናለሁ` ሕዝ ፴፬፥፲፮

++++

የተወደድሽ የድኅነታችን ምክንያት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የመከራችንን ጥልቀትና የልባችንን የመፈወስና የመዳንን ምኞት አድምጠሽ የአንቺን የእምነት፣ የትህትና እና የእግዚአብሔርን ፈቃድ መታዘዘ እንድንከተል ጸጋውን ይሰጠን ዘንድ በልጅሽ ፊት አማልጅን።

++++

የሰማይ አባት ሆይ ጸሎታችንን ሰምተህ ለሀገራችን፣ ለአህጉራችንና ለዓለማችን የአንተ የፈውስና የጸጋ መሳሪያዎች እንሆን ዘንድ ጸጋህን ስጠን። በነገር ሁሉ ፈቃድህን እንድንፈልግ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም፣ የቅዱሳን እና የምእመናን ሁሉ ጸሎት የብርታትና የመጽናናት ምንጭ ይሁንልን። በአንድ ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሱም ጋር ትክክል በሆነ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን!

 
መ/ር ቃለአብ መዝገቡ
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የፈተናዎች ማስተባበሪያና ክትትል ክፍል ዋና ኃላፊ
መጋቢት ፳፩
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
የጌታ ጅራፍ
                         
Size 31.4MB
Length 1:30:08

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#ምስባክ #መጻጕዕ
ዘመጋቢት ፳፫ ፣ ፳፬ ፣ ፳፭
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#72ቱ_አርድዕት_ስም_እና_መታሰቢያ_ቀን
1 ማርቆስ ዮሐንስ ወንጌላዊው ሚያዝያ 30
2 እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ጥር 1 እና ጥቅምት 17
3 ጳውሎስ ሐዋርያ ሐምሌ 5
4 ጢሞቴዎስ ወልዱ ለጳውሎስ ህዳር 27 ና ጥቅምት 26
5 ሲላስ ወልዱ ለጳውሎስ ጥቅምት 15
6 በርናባስ ወልዱ ለጳውሎስ
7 ቲቶ ወልዱ ለጳውሎስ ታህሳስ 18ና ጳጉሜ 2
8 ፊልሞና ወልዱ ለጳውሎስ መጋቢት 7ና ሕዳር 7
9 ቀሌምንጦስ ወልዱ ለጳውሎስ መጋቢት 12
10 ዘኪዎስ ወልዱ ለማቴዎስ ጥር 28
11 ቆርነሌዎስ ወልዱ ለጳውሎስ መስከረም 11
12 ቴዎፍሎስ ወልዱ ለሉቃስ መስከረም 1
13 ኤውዴዎስ ሰኔ 21
14 አግናቴዎስ ነሐሴ 23
15 አናንያኖስ ዘይሰመይ ይሁዳ ነሐሴ 3
16 ማልኮስ (አግሊጦስ) መስከረም 24
17 ኤሌናስ (ኢተኮስ) ሚያዝያ 16
18 አርሳጢስ (አርጣቦሉ) ሚያዝያ 29
19 አስተራቲዎስ ሀናንያ መጋቢት 7 እና ሰኔ 26
20 አርሰጦበልስ ወልዱ ለጳውሎስ መጋቢት 19
21 ጋይዮስ ሚያዝያ 23
22 እድማጥስ መስከረም 16
23 ሉኪዮስ ታህሳስ 29
24 ድዮናስዮስ ጥር 21
25 መርአንዮስ (ዊይዳ) ነሐሴ 6
26 አርክቦንዮስ ህዳር 24
27 አናሲሞስ ጳጉሜ 3
28 ከርላዲስ ወልዱ ለፊልጶስ ሐምሌ 10
29 አኪላስ መጋቢት 15
30 ንኪትስ (ኢያሶን) ግንቦት 3
31 ቀርጾስ (ጢባርዮስ) መስከረም 21
32 ክርስቶፎሮስ ሚያዝያ 2
33 ፊልጶስ ካልዕ ጥቅምት 14
34 ጰርኮሮስ ሰኔ 8
35 ኒቃሮና (3 ጊዜ ሞቶ የተነሳ)
36 ጢሞና ኡቲቦስ ረድዑ ለዮሐንስ ወንጌላዊ ሚያዝያ 16 እና ሰኔ 8
37 ጰርሚና መስከረም 21
38 ኒቆላዎስ ወልዱ ለሉቃስ ሚያዝያ 15
39 ሉቃስ ወንጌላዊ ወልዱ ለዮሐንስ ጥቅምት 22
40 ዮሴፍ ነሐሴ 25
41 ኒቆዲሞስ ሚያዝያ 6
42 ያዕቆብ (የጌታ ወንድም የሚባለው) ጥቅ. 26 እና የካቲት 18
43 አብሮኮሮስ መጋቢት 1 እና ጥር 20
44 ሮፎስ ወይም አንሲፎሮስ መጋቢት 25
45 እስክንድሮስ መጋቢት 1
46 ስልዋኖስ የካቲት 11
47 ሳንቲኖስ (እንደበቅሎ ተጎትቶ የሞተ) መጋ. 5
48 ኢዩስጦስ ሚያዝያ 16
49 አክዩቁ (አጋቦስ) የካቲት 4 እና ሚያዝያ 15
50 አፍሮዲጡ (አፍሮዲጦስ) ግንቦት 23
51 አንሞስ (በጉድጋድ ጥለው ያሰቃዩት) ታህ. 9
52 ገማልኤል ሐምሌ 5
53 አንዲራኒቆስ ጥር 8 እና ግንቦት 22
54 አናንያ ጥቅምት 4 እና ሰኔ 27
55 ድርሶቅላ ሰኔ 7
56 አቄላ ሚያዝያ 5
57 ኤጴንጢስ ሕዳር 15
58 አንድራኒቆስ (ጴጥሮስ) ሕዳር3
59 ዮልያል (ዮልዮስ) ግንቦት 23
60 ጰልያጦስ ሐምሌ 19
61 መርማርያን (በመጋዝ ሰንጥቀው የገደሉት) መጋቢት 5
62 ኬፋ ወልዱ ለሉቃስ ሰኔ 25
63 ኡርባኖስ ወልዱ ለቶማስ ሰኔ 9
64 ስጠክን ወልዱ ለማትያስ ሕዳር 13
65 አጤሌን ወልዱ ለፊልጶስ ጥር 12
66 አክሌምንጦስ ወልዱ ለያዕቆብ ጥር 21
67 ሔሮድያኖስ ወልዱ ለቶማስ ሰኔ 21
68 ጥርፌና ወልዱ ለታዴዎስ ህዳር 3
69 ጠርፌስ ወልዱ ለበርተለሜዎስ መጋቢት 16
70 አስከሪጦስ ወልዱ ለጴጥሮስ ሰኔ 25
71 ሉቅዮስ ወልዱ ለያዕቆብ ወልደዘብዴዎስ ህዳር 3
72 ሱሲ ወልዱ ለማቴዎስ መጋቢት

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ደስ ይበልሽ
                         
Size 29.6MB
Length 1:24:56

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ቀድሞ የገባ ሰው ይፈወሳል
                         
Size 58.7MB
Length 2:48:30

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ
ማቴ 26÷39
Size 34.5MB
Length 2:30:38
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ለ "ዓለም" ማለፍ የግድ 6 ነገሮች መገጣጠም አለባቸው 👇
1. ዕለት (እሑድ)
2. ሰዓት (መንፈቀ ሌሊት)
3. ወንጌላዊ (ዮሐንስ)
4. የምልክቶች ሙሉ ለሙሉ መፈጸም (ማቴ 24 ላይ የተዘረዘሩት)
5. የፀሐይ ሙሉ ግርዶሸ 👉 Total Solar Eclipse (የ 12 ሰዓታት ሙሉ ግርዶሽ ይኸውሞ አቀድ ኮከብ የሚባል ኮከብ የሰሌዳው መጠን ከፀሐይ ጋር የሚተካከል ሲሆን ጽሉም ወይም ጥቁር የሆነ ሰሌዳውን ወደ ውጪ አድርጎ ፊቱን ወደ ፀሐይ አዙሮ ዘግቷት ለ 12 ሰዓት በእኩል ፍጥነት አብሯት ይጓዛል በዚህ ምክንያት ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ ይፈጠራል 👉ማቴ 24፥29)
6. የዘመን መፈጸም ፦ ለዓለም ኅልፈት የተሰጠው ዘመን 7980 ዓመተ ዓለም ከተፈጸመ በኋላ ነው ፤ 464 ዓመት ይቀረዋል ...ከዚያ በኋላ ግን ዓለምን ያሳልፈው እንደሆነ ያዘገየውም እንደሆነ ይተወውም እንደሆነ እርሱ ያውቃል ብሎ አቡሻኽር ይዘጋል። 👇
እነዚህ 6 ነገሮች ካልተገጣጠሙ ዓለም አያልፍም !!!
ስለሆነም አሁን በዓለማችን ያሚታዩት ምልክቶቹ "የምጥ ጣር መጀመሪያ" ተብለው የተገለጹ ናቸው (“እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።”
— ማቴዎስ 24፥8)
ይሁን እንጂ ዓለም ማለት ሰው ነውና የእያንዳንዱ ሰው ኅልፈት የዓለም ኅልፈት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል !

ዓለም እኛ በሞት ከማለፋችን በፊት በንስሐና በሥጋ ወደሙ በኩል እንድናልፍ እግዚአብሔር ይርዳን!!!!

( መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው )


@Nigatu 5
@Nigatu5
@Nigatu 5
Audio
መቼ ይመጣል?
                         
Size 10.1MB
Length 28:57

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@NIGATU5
@NIGATU5
@NIGATU5
Audio
እሴተ ሃይማኖት 
       ክፍል 4                          
Size:- 18.9MB
Length:-54:07
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/09/23 14:27:17
Back to Top
HTML Embed Code: