Telegram Web Link
*ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ*

ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ ለመንገዴ ፋና
እንዳልጠፋ አምናለው ያንቺ ልጅ ነኝና/2/
አዝ..........
የጻድቃን እናቶች እጅብ ብዙ ናቸው
ከብሉይ ከሃዲስ ብንዘረዝራቸው
አንቺ ግን አንዲት ነሽ የለሽም ጭማሬ
ትኖሪያለሽ እንጂ ትውልድ ስታስምሪ
አዝ..........
ያንቺን ስም ተማጽኖ ያንቺን ስም ቀድሶ
አንቺን አመስግኖ አንቺን አወድሶ
የተጠቀመ እንጂ በረከት አግኝቶ
አልታየም እስከ አሁን የተጎዳ ከቶ
አዝ..........
ጎርጎርዮስና ሊቁ ዮሐንስ
አትናቴዮስ እና ሊቁ ባስልዮስ
አባ ኤፍሬም እና አባ ጊዮርጊስ
ተጠቅመዋል ባንቺ በስጋም በነፍስ
አዝ..........
አባትህን ጠይቅ ስለሚለን ቃሉ
ብንጠይቃቸው ቅዱሳኑን ሁሉ
ስላንቺ ነገሩን ክብር ተዓምራትሽን
ለሰው ዘር በሙሉ አማላጅ መሆንሽን
አዝ..........
ገብርኤል ከሰማይ ኤልሳቤጥ ከምድር
በአንድ መሰከሩ ስለ ድንግል ክብር
ሰዓኒ ለነ ብሎ ተማጽኖ በአንቺ ስም
የተጠቀመ እንጂ የተጎዳ የለም

ለነፍሴ ነፍሷ ነሽ ለመንገዴ ፋና እንዳልጠፋ አምናለው ያንቺ ልጅ ነኝና/2/
አድርሽን!

ከልጅሽ ፍቅር አድርሽን።
ከአንቺ ፍቅር አድርሽን።
ከቅዱሳን ፍቅር አድርሽን።
ለንስሐ ሞት አብቂን።
2024/09/30 09:22:16
Back to Top
HTML Embed Code: