Telegram Web Link
Audio
"" የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ ""

(ማቴ. ፮:፳፮)

በመምህርዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ

(ኅዳር 14 - 2015)
Audio
ወፍም ቤትን አገኘች
                   
  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ከንስሐ በሃላ



አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት


ክህነት ምንድነው


የምሥጢር ክህነት አመሠራረ ኪዳን

የምስጢር ክህነት አመሠራረት በሐዲስ ኪዳን

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት


የክህነት ዓላማና ጥቅም ምንድነው

ሥልጣና ክህነት ለማን ይስጣል

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ስርዓት ተክሊል ምንድነው

ጋቢቻ መቼ እና ማን መሰረተው

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ጋቢቻ ቅድም

ጋቢቻ በሃላ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ፋቺ የሚፈቅድባቸው ምክንያቶችስ

ምሥጢረ ቀንዲል

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
ከወደቁ አይቀር .....#ለጽዮን
____

አንዳንድ ውድቀቶች ካለ አስፍላጊ አቋቋሞች በእጅጉ የተሻሉ ናቸው ። ለምሳሌ ከሐውልቱ እንደምናየው ለጽዮን መውደቅ በእውነቱ ዋጋ ያለውና የተሻለ አወዳደቅ ነው::

#ይህ በመጠኑና በውበቱ ከፍ ያለው ሃውልት አሁን ሳይወድቅ ቆሞ ካለውና በቅርቡ ከሮም ከመጣው ዕድሜ ይሁን በሰው ሀገር ያለ ቦታው መቆሙ የሞራል መላሸቅ ያስከተለበት የሚመስለሁ እንደ አዛውንት ጎብጦ በመደገፊያ በግድ ከቆመው ሐውልት በተለየ መልኩ በፊት ለፊቱ ወድቆ ይታያል::

ይህ የአክሱም ሐውልት ከመሐመድ ግራኝ ወራራ በኋላ የተነሳችው ሴቷ ግራኝ ዮዲት ጉዲት ካስከተለችው ጥፋቶች መካከል የጥፉቷን ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የሆነ ታሪካዊ የሀገር ቅርስ ነው :: ዮዲት በክርስቲያንኖችና በቤተክርስቲያን ላይ ባደረባት የተሳሳት ጥላቻ ኃያሌ የጭካኔ ተግባራትን በክርስቲያኖችና በቤተክርስቲያን ላይ ያስከተለች የታሪክ ጠባሳ ነች ::

#ከበዙ ጥፉቶች በኃላ ወደ እዚህ ወደ አክሱም ሐውልት መቆሚያ አካባቢ ስትደርስም ጭፍሮቿ እንደለመዱት የእክሱምን ሐውልቶች ይጥሏቸውና ይሰባብሯቸው ዘንድ ተራኮቱ ዮዲትም ሁሉንም ሐውልቶች አትጣሏቸው አንዱንና ትልቁን ለዐይንም የሚማርከውን ሐውልት ብቻ ጣሉት ሌሎቹን ግን እንዳትነኩ ስትል ትዕዛዝ አስተላለፈች ጭፍሮቿም ለምን? ሲሉ ጠየቁ


በሌሎች ቦታዎች እዳደረግን ሁሉንም ብንሰባብርና ብናወድማቸው መጪው ትውልድ ሲያቸው አንድ ጊዜ ተበሳጭቶ ብስጭቱን ይተወዋል የሚያምረውን ና ተለቅ የሚለውን ሃውልት ብቻ ብንጥለውና ሌላው ብንተውለት ግን ባየውና በሰማው ቁጥር ይህ ትልቁኮ ባይወድቅ ከነዚኞቹ በላይ ውብ የሀገር ቅርስ ሆኖ ይታይ ነበር እያለ ዘላለም ዓለሙን እየተቃጠለ ሲብሰለሰል ይኖራል ገባችሁ ስትልም አምቧረቀችባቸው::


#ሐውልቱ ግን ለትውልዱ ቁጭት ሳይሆን ትምህር ይሆን ዘንድ ወደ ጽዮን ወደቀ ተንበርከኮም ሰገደላት ። የጌታዬ እናት በፊትሽ እቆም ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እያለም ተሳለማት ሉቃ1÷43። ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ ልብ ያለውም ልብ ያድርግ "በፈሊጥ ካልገባው በፍልጥ " እንዲሉ ። ሰው ሁለት ጊዜ ይማራል ይላሉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን አንድ በሣር " ሀ " ብሎ ካልሆነም በአሳር " ዋ "ብሎ ። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ብራና ዳምጠው ቀለም በጥብጠው በሣር ስግደት እንደሚገባት ሲያስተምሩን ካልገባን በአሳር ጎንበስ ማለታችን አይቀርምና ከአሳሩ በፊት በሳሩ ተማሩ እንላለን።

#የአስጨናቂዎችሽም_ልጆች_አንገታቸውን_ደፍተው_ወደ_አንቺ_ይመጣሉ ፥ የናቁሽም ሁሉ #ወደ_እግርሽ_ጫማ ይሰግዳሉ፤ #የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል #ቅዱስ_የሆንሽ_ጽዮን ይሉሻል።”
#ኢሳ 60፥14


አ.አ ኢትዮጵያ
ተርቢኖስ ዘተክለ ኤል
እርሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲገለጥና እርሱ እንዳይታይ ተናግሮ ነበር ከዚሆ በተጨማሪም እንዲህ በማለት ተናግሯል ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው ቆሞ የማሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምፅ እጅግ ደስ ይለዋል እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያሰፈልጋል ዮሐንስ 3÷29-30

አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ እንደ ተረጎሞት
ተክለሐይማኖት ባህታዊ

ተክለ ሐይማኖት ባህታዊ
ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ
በአደባባዩ ተተክለሃል
ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል

ቃልኪዳን አለህ የገነነ
ምህረት የሚያሰጥ የታመነ
በስምህ ውሃ አጠጥተን
ዋጋችን በዝቷል አባታችን
      #አዝ
እኛም ሆነናል ልጆችህ
ማርኮ አስቀርቶን ምግባርህ
በምልጃህ ጸሎት ትሩፋት
ቤታችን መላ በረከት
       #አዝ
ምህረት ይዘንማል ከሰማይ
በአንድ እግርህ ቆመህ ስትጸልይ
ብዙ ተጋድለህ አትርፈሀል
ያገለገልከው አክብሮሃል
        #አዝ
ተሰባበሩ ጣዖታቱ
አምነው ሰገዱ መኳንንቱ
የበረታው ቃል ከአፍህ ወጥቶ
የአምላክ አድርጓል ሁሉን ገዝቶ

         ዘማሪት
     ጸዳለ ጎበዜ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
#24ቱ_ካህናተ_ሰማይ_25 ሆኑ !
___

አስቀድመው ቅዱሳን ሐዋርያት 12 ብቻ ነበሩ ከመካከላቸውም ይሁዳ ገንዘብ ወዶ ዘመድ ለምዶ አገልግሎቱን ትቶ ሄደ ሐዋርያትም ወንጌል በዓለም ሳይሰበክ ቢቀር አገልግሎታችን ተስተጎግሎ መቅረቱ  አይደለ ብለው እግዚአብሔር ባወቀ ይሁዳ በተዋት አገልግሎት ፈንታ ሌላ ሰው እንዲሿምላቸው በርናባስንና ማትያስን አቀረቡ መንፈስ ቅዱስም ማቲያስን መርጦ ሰጣቸው:: የሚገርመው ነገር የእግዚአብሔር ድንቅ ስጦታ ነው በአንዱ ይሁዳ ፈንታ ሁለት ምትኮችን ሰጣቸው አንዱ ማቲያስ ሲሆን ሌላው እራሱ በቃሉ ሐዲስ ሐዋርያ ብሎ የሾመው ተክለ ሃይማኖት ነው ቅዱስ ጳውሎስን ከአሳዳጅነት ቅዱስ ጴጥሮስን ከዓሳ አጥማጅነት እደጠራቸው  ሐዋርያትን በጠራበት አጠራሩ አባታችን ተክለ ሃይማኖትን እንሰሳ ከሚያድኑበት ("ድ")ጠብቆ ይነበብ) ጫካ ጠርቶ በወንጌል መረብነት ሰው የሚድኑ ("ድ")ላልቶ ይነበብ አዳኝ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጉ  ሾማቸው የሐዋርያት ቁጥረም 12 ቢሆንም  በሐዲሱ ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ አማካኝነት  ያለ ወትሮ 13 ሆነ ምነው መጻሕፍት 12ቱ ሐዋርያት አይደል የሚለው ቢሉ መጻሕፍት በቀረበው የመጥራትም ፀባይ አላቸው 12ቱን ሐዋርያት አስሩም አያለ እንደጠራቸው ማለት ነው ስለዚህ 12ሐዋርያት ስላለ 13ተኛ አይጨመርም አያሰኝም

#አባታችን ተክለ ሃይማኖት ቁጥራቸው ከሐዋርያት ወገን ብቻ ሳይሁን ከስማዕታትም ጋር ጭምር ነው ምነው ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ሲሉ ሥጋቸውን የቆረሱ ደማቸውን ለምስክርነት ያፈሰሱ እንደነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያሉ ሰዎች አይደሉም  እንዴ ቢሉ አባታችን ተክለ ሃይማኖት መከራን አብዝቶ በመቀሎል ከሰማዕቱ በምን ተለዮ?በዳሞቱ ንጉስ እጃቸው በሰይፍ ተቆረጠች እግዚአብሔር እንደ ቀድሞ ጤነኛ አደረገላቸውጉልያድን በሚያካክሉ በሞተሎሚ  በወታደሮች በሽምግልና አቅማቸው ደም በአፍና በአፍንጫቸው እስኪተፉ ተደብድበዋል በንብ ቀፎ ተደርገው ወደ ገደል ተጥለዋል ከዚህ ሁሉ ስቃይና ደም መፍሰስ በኃላ እራሱ አልበቃ ብሏቸው ወደ አደባባይ ወጥቼ ስለ ስምህ መስክሬ እንደሰማዕታት ደሜን አፍስሼ ልሞት እፈልጋለው አሉ:: እግዚአብሔር ግን ከዚህ በላይ ሰማዕትነት አንደሌለ ሲነግረን እኔ ከአንተ ሰውነት በእመምህ ምክንያት የሚወጣውን ፈሳሽ እኔ እንደ ሰማዕታት ደም አቆጥርልሃለው ብሎ ዕረፍታቸውን በሰማዕታት ዕረፍት ቆጠረው ::
    #አንዳንድ ሞኝ ሰዎች ይህን በማንበብ እንዴት የተክለ ሃይማኖት በእመም ከሰውነታቸው የወጣ ፈሳሽ(ተቅማጥ)እንዴት ከሰማዕታት ደም ጋር እኩል ይሆናል? ሲሉ ይሰማሉ ጌታችን መዳኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ" ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል"ሲል ተደምጧል #ማቴ 25 ÷40 ታዲያ ለሰው ማድረግ ለእርሱ እንደማድረግ ተደርጎ ከተቆጠረ ወይም የአባታችን የሰውነት ( ፈሳሽ ተቅማጥ) እንዴት አንደ ሰማዕታት ደም መቆጠሩ ስህተት አይደለም እንደውም ይህ ነገር ስህተት ነው ከማለት ይልቅ የጌታችን ምሳሌ ስህተት ይመስላል ሰው ሲራብ ማብላት ሰው ሲጠማ ማጠጣት ሰው ሲታሰር ሄዶ መጠነቅ የማይራበው እግዚአብሔር ተርቦ እንደ ማብላት የማይጠማውን እግዚአብሔርን ተጠምቶ እንደ ማጠጣት የመይታሰረው እግዚአብሔርን ታስሮ እንደተጠየቀ አድርጉ መቁጠር  አንዴት ይቻላል? ሌላውና ወሳኙ ነጥብ በህመም ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽ(ተቅማጥ) እና ደም  ከሚያስከትሉት ችግር አንጻር ምንም ልዮነት የላቸውም በሳይንሱም ዓለም አገልግሎቱን ያልጨረሰ ፈሳሽ ከሰውነት ከወጣ በቶላ በሌላ ፈሳሽ ምግቦች እንዲተካ ይደረጋል ለምሳሌ" ሀተት "የተሰኘውን የጠቅማጥ በሽታ ብንወስድ ለሁለት ሳምንት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ቀኞች  ተተኪ ፈሳሽ ምግብ ሳንወስድ ዝም ብንለው  ወደ ሞት ያደርሰናል ይህ ማለት ደም ሥር ተቆርጦ ብዙ ደም ከፈሰሰ በኃላ ምንም ተተኪ ፈሳሽ ሳይወስዱ እንደመቀመጥ እና እነደሚያስከትለው ችግር ሊቆጠር ይችላል:: ስለዚህ ሰማዕታት ደማቸውን አፈሰሱ ሲባል ለመኖር የሚያስችላቸውን ወሳኝ ነገር(ደም)ከሰውነታቸው ወጣ ማለት ነው አባታችን ተክለ ሃይማኖትም ልክ እንደ ደም ጥቅምነቱን ሳይሰጥ ከሰውነታቸው በመውጣቱ ደሙ ሳይፈስ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ ሰማዕታት የክብርን አክሊል ወደ ሚቀዳጅባት ሞት እንደማይቀርቡ ሁሉ አባታችንም ለሞት ባልቀረቡ ነበር::

አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቁጥራቸው ከሐዋርያት ወይም ከሰማዕታት ወገን ናቸው ተብሎ ብቻ አይታለፍም ከካህናተ ሰማይ ከሡራፌል ጋርም ይመደባሉ ለወትሮ ካህናተ ሰማይ ሡራፌል ቁጥራቸው 24ብቻ ነበሩ ኢትዮጵያዊው አባት ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የኢትዮጵያ ሲሳይ ሐዲስ ሐዋርያ ሰማእት ወነብይ ወካህን በተወለዱ እና ባደጉ ጊዜ ግን 25ለመሆን ተገደዋል ::ኃዳር 24ቀን 24ቱ ካህናተ ሰማይ ሡራፌል እንደለመዱት ሥሉስ ቅዱስ ብለው መንበሩን አያጠኑ ሳለ ድንገት ቅዱስ ሚካኤል ከሰዎች ወገን የሆነ ሰው ሲሆን እንደ መላእክት  ስድስት የፀጋ ክንፎች የተሰጡት ብርሃን ዘኢትዮጵያ የሆነውን አባታችን ተክለ ሃይማኖትን ይዞ አመጣው  የወርቅ ማዕጥንትም ተሰጠው ከዙፋኑም ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ቁጥርህ ከንግዲህ ወዲህ ከ24ቱ ሰማያተ ካህናት ጋር ይሁን  አለው:: 25ተኛ ካህንም ሆኖ የሥላሴን መንበር ሥሉስ ቅዱስ እያለ በወርቅ ማዕጥንት አጠነ: : ራዕ ዮሐ 4÷4 ገድለተክለ ሃይማኖት
*ይቆየን*
#የባታችን እረድኤትና ምልጃው አይየን ለዘላለሙ አሜን!!!

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ምሥጢረ ቀንዲል

የመጨረሽ ክፍል

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
ኑ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ

ኑ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ ኑ በጸሎት ወደአምላክ ቅረቡ፤ በጸሎት ማለት እንዴት ነው? ይህስ የልባችሁን ምስጢር ሁሉ ሳትደብቁ እርሱ እግዚአብሔር እንደሚያስፈልጋችሁ መናገር ማለት ነው። እንዲህም በሉ፦

“ጌታ ሆይ ወደ አንተ መምጣት እፈልጋለሁ፤ ጌታ ሆይ ካንተ ተለይቼ እኔ ምንም ነኝ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ ዕለት ህይወቴን አጣሁ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ ዕለት ደስታዬን ሁሉ አጣሁ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ ዕለት ህይወቴ ትርጉም አልባ ሆነ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ ዕለት ህይወቴ ጣእም አልባ ሆነ” በሉት።

ዳግሞም ከእግዚአብሔር እግር ስር ተደፍታችሁ እንዲህ በሉት፦ “አምላኬ ሆይ ወደ አንተ መመለስ እፈልጋለሁ፤ ነገር ግን ጠላቶቼ ከእኔ በእጅጉ የሚበልጡ ናቸው፤ ነፍሴንም አምላክሽ አያድኑሽም የሚሏት ብዙ ናቸውና።” በሉት።

ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ “ጌታ ሆይ ታደገኝ ወደ አንተ የምመለስበትን መንገድ ምራኝ” በሉት፤ ለአምላካችሁ ንገሩት “ካንተ ከተለየሁ ወዲህ አቅሜ ሁሉ ተዳክሟልና ጌታ ሆይ ልዩ ሃይልህን ላክልኝ፤ ወደ አንተ የምመለስበትን ልዩ ርዳታህን ስጠኝ” በማለት ሁል ግዜ ጸልዩ።

ብዙ ሰዎች በመደጋገም “ወደ እግዚአብሔር የምመለሰው እንዴት ነው?” ይላሉ። ከእግዚአብሔር እግር በታች ራሳችሁን ጣሉ። እንዲህም በሉት “ጌታ ሆይ ሳትባርከኝ አልለቅህም፣ ወደ አንተ አቅርበኝ፣ ከልጆችህ እንደ አንዱ አድርገኝ፣ ሐጥያቴን ብቻ ይቅር እንድትልልኝ አልሻም፣ ይልቁንም ከሐጥያት ፍቅር ትለየኝ ዘንድ ጭምር እንጂ” በሉት።

ዳግምም “ጌታ ሆይ የሐጥያት ፍቅር ልቤን ተቆጣጥሮታልና ይህን ካላስወገድኩ ወደ አንተ መቅረብ አይቻለኝም፤ ጌታ ሆይ የሐጥያትን ፍቅር ከልቤ ላይ ንቀለው” በሉት።

ዳግምም እንዲህ በሉት “ጌታ ሆይ ከሐጥያቴ ነጽቼ ወደ አንተ መምጣት እንደምን ይቻለኛል? ይልቁንስ መጀመሪያ አንተ ናልኝ ሃጢአቴንም ደምስስ እንጂ” በሉት። እንዲህም በሉት “በራሴማ ሐጥያትን ማስወገድ ብችል ወደ አንተ መቼ መመለስ ያቅተኝ ነበር? እኔ ግን አንተ ከሐጥያቴ እንድታርቀኝ እወዳለሁ፤ ጌታ ሆይ ሃይልህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” በሉት።
ኅዳር 25 በዓለ እረፍቱ ለቅዱስ መርቆሬዎስ

የዚህ ቅዱስ ሰማዕት ወላጆቹ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ስሙን ፒሉፓዴር ብለውታል ትርጓሜውም “የአብ ወዳጅ” ማለት ነው፡፡ በመንፈሳዊ ትምህርት አጠንክረው አሳድገውታል፡፡ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጥቶት ዜናው በሁሉ ቦታ ሲሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎች ይልቅ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በዚህ ምክንያት በጊዜው በነበረው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘንድ ባለሟልነት አግኝቷል፡፡

ከዚያም በሮም ላይ የበርበር ሰዎች ተነሥተው የዳኬዎስን መንግሥት ሊወጉት መጡ፤ እጅግ ብዙዎችም ነበሩና ንጉሡ እጅግ ፈራ፤ ቅዱስ መርቆሬዎስ ግን “እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ” አለው፡፡ ወደ እግዚአብሔር በፀለየ ጊዜ መልአክ የተሳለ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገልጦለት ሰይፉን በመስጠት “ጠላቶችኽን ድል ባደረግህ ጊዜ ፈጣሪህ እግዚአብሔርን አስበው” ብሎ ሰጥቶታል፡፡ ያን ጊዜም በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት፡፡ ጸሎት አድርሶም የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ፡፡ ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም፡፡

ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ደስታን አደረጉ፡፡ ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ ነው" በማለት ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጣዖት እንዲሠዋ ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ፡፡ ቅዱሱ ግን ወደ ንጉሱ አደባባይ በመሄድ የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው "ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው፡፡  ንጉሡም እጅግ ተቈጥቶ ርጥብ በኾኑ የሽመል በትሮችና እንዲደበደብና ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገረፍ አዘዘ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስ ካለው ተወዳጅነት የተነሣ ሰዎች እንዳይነሡበት በመፍራት የቀጶዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሳርያ በብረት ማሠሪያ ታሥሮ እንዲላክ አድርጎ ብዙዎች ሥቃይ አደረሱበት፤ ከዚያም ኅዳር 25 ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ የምሕረትን ቃል ኪዳን ከገባለት በኋላ ራሱን በተሳለ ሰይፍ ቈርጠውት የሰማዕትነትን አክሊልን ተቀዳጀ፡፡

የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን፡፡
2024/10/01 09:42:34
Back to Top
HTML Embed Code: