Telegram Web Link
*የብርሃን እናት*

እርእስ ፦ከፀሐይ አጠገብ የነበረው ኮከብ

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
*የብርሃን እናት*

እርእስ ፦ከፀሐይ አጠገብ የነበረው ኮከብ

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
*የብርሃን እናት*

እርእስ ፦ከፀሐይ አጠገብ የነበረው ኮከብ

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው።

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ
የኤፍራጥስ ወንዝ ገጽ 87
*የብርሃን እናት*

እርእስ ፦የጻድቃን ቀጠሮ(ፈጥና ወጣች)

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
*የብርሃን እናት*

እርእስ ፦የጻድቃን ቀጠሮ(ፈጥና ወጣች)

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
Audio
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠    /ማቴ ፫:፫/

🌻እንኳን አደረሳችሁ!❀🌻

"" ቅዱሳንን ለማገልገል፥ ወደ ኢየሩሳሌም እሔዳለሁ! "" (ሮሜ. ፲፭:፳፭)

(መስከረም 20 - 2015)

በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ(ገበረ መድኅን)

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Audio
"" መስቀሌን በመስቀል ላይ አኑር ""

በመምህር ፍሬ ሕይወት አረጌ (የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ መምህር)

(መስከረም 21 - 2015)
Audio
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠    /ማቴ ፫:፫/

🌻እንኳን አደረሳችሁ!❀🌻

"" እኔ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ! "" (ኢያ. ፮:፲)

በመምህር ፍሬ ሕይወት አረጌ

(የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ መምህር)

(መስከረም 22 - 2015)

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Audio
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/


"" ምልክትን ሰጠሃቸው! "" (መዝ. ፶፱:፬)

"" ዝክረ ቅዱስ ዳዊት ዘወርኃ መስከረም ""

(🌻መስከረም 23 - 2014🌻)

በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
@m2vbot
Convert To Voice
"" ምልክትን ሰጠሃቸው! "" (መዝ. ፶፱:፬)

(🌻መስከረም 23 - 2014🌻)
የግእዝ ፊደላት ከሌሎች ቋንቋዎች ፊደል የሚለየው ፊደላቱ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ትርጉም ስላላቸው ነው።
ለምሳሌ፦


ሀ - ማለት የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው፡፡
    - ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እም ቅድመ ዓለም።

ለ - ማለት የእኛን ሥጋ ለበሰ።
    - ብሂል ለብሰ ሥጋ ዚአነ

ሐ - ማለት ስለእኛ ታሞ ሞተ።
     - ብሂል ሐመ ወሞተ በእንቲአነ

መ - ማለት የእግዚአብሔር  ስራው ድንቅ ነው፡፡
      - ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር

ሠ - ማለት ከድንግል በሥጋ ተወለደ(ተገለጠ)
     - ብሂል ሠረቀ በሥጋ እምድንግል

ረ - ማለት በጥበቡ ፤ ሰማይና ምድር ረጋ።
    - ብሂል ረግዓ ሰማይ ወምድር

ሰ - ማለት እንደእኛ ሰው ሆነ።
    - ብሂል ሰብአ ኮነ ከማነ

ቀ - ማለት በመጀመሪያ ቃል ነበረ።
    - ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ

በ - ማለት ለዓለም ሁሉ ቤዛነት በትሕትናው ወረደ፡፡
    - ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኩሉ ዓለም

ተ - ማለት ፍፁም ሰው ሆነ።
    - ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ

ኀ - ማለት ራሱን (ባህሪውን )ሰወረ (ሸሸገ)
    - ብሂል ኀብአ ርእሶ

ነ - ማለት ደዌያችንን ያዘል ሕማማችንንም ተሸከመልን።
   - ብሂል ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ
 
አ - ማለት እግዚአብሔርን ፈፅሞ አመሰግነዋለሁ።
    - ብሂል አአኲቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር

ከ - ማለት እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው፡፡
- ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር
   
ወ - ማለት ከሰማያት ወረደ።
     - ብሂል ወረደ እምሰማያት

ዐ - ማለት እግዚአብሔር ታላቅ ነው።
    - ብሂል ዐቢይ እግዚአብሔር

ዘ - ማለት እግዚአብሔር ሁሉን የሚይዝ (የሚገዛ ነው)።
    - ብሂል ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር

የ - ማለት የእግዚአብሔር ቀኝ ኀይልን አደረገች።
   - ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ

ደ - ማለት መለኮቱን ከሥጋችን ጋር አንድ አደረገ።
    - ብሂል ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ

ገ - ማለት ምድርና ሰማያትን የፈጠረ ነው፡፡
    - ብሂል ገባሬ ሰማያት ወምድር

ጠ - ማለት እግዚአብሔር ጠቢብ ነው፡፡
      - ብሂል ጠቢብ  እግዚአብሔር

ጰ - ማለት ጰራቅሊጦስ የእውነት መንፈስ ነው፡፡
    - ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ

ጸ - ማለት እግዚአብሔር  ጸጋና እውነት ነው።
    - ብሂል ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር

ፀ - ማለት እግዚአብሔር የእውነት ፀሐይ ነው።
    - ብሂል ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር

ፈ - ማለት በጥበቡ ዓለምን ፈጠረ።
    - ብሂል ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ

ፐ - ማለት የእግዚአብሔር ስሙ ፓፓኤል ነው፡፡
    - ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለእግዚአብሔር
እናቴ ቅድስት አርሴማ

ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ
ካለሽበት ገስግሼ መጣውኝ
እናቴ ክብርሽን አንግሼ
ሆንኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ
እናቴ ቅድስት አርሴማ
ዝናሽ ለዓለም ተሰማ


ስመጣ በአልጋ ነበረ
ተስፊዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት

አዝ----------

ደምግባት ከንቱ ብለሽ
ለሰማይ ክብር የታጨሽ
የእምነቴ አሰረ ፍኖት
በምልጃሽ አለውኝ በሂወት
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ሂወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል

አዝ----------

እርዳታሽ የደረሰለት
ያመጣል የልቡን ስለት
ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው
በአንቺ አፍሮ የሄደ ማነው
የልቡን ለነገረሽ
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ
ዘንባባሽ ሂወት ይዘራል
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል

አዝ----------

ስመጣ በአልጋ ነበረ
ተስፊዬም የተሰበረ
በእምነትሽ በፀበልሽ
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ
ልናገር ዝናሽን ላውራ
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት
2024/11/20 09:15:01
Back to Top
HTML Embed Code: