Telegram Web Link
​​🌼 አበባዮሽ 🌼

እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(2)
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ጌቶች አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ዘመን መጣ ብለን

አበባዮሽ                    ለምለም(2)
ባልንጀሮቼ                  ለምለም
ግቡ በተራ                  ለምለም
በእግዚአብሔር መቅደስ     ለምለም
በዚያች ተራራ              ለምለም
እንድታደንቁ                ለምለም
የአምላክን ሥራ           ለምለም
ህይወት ያገኛል         ለምለም
እርሱን የጠራ             ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ                   ለምለም (2)
ክረምት አለፈ            ለምለም
ጨለማው ጠፋ         ለምለም
የመስቀሉ ቃል          ለምለም
ሆነልን ደስታ            ለምለም
እናገልግለው           ለምለም
ቤቱ ገብተን            ለምለም
ትንሽ ትልቁ             ለምለም
ተሰልፈን                ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ               ለምለም(2)
ያንን ኩነኔ              ለምለም
ዘመነ ፍዳ              ለምለም
የሞቱ በራፍ           ለምለም
ያ ምድረበዳ           ለምለም
ልክ አንደ ክረምት    ለምለም
ሄደ ተገፎ              ለምለም
ፀሐይ ወጣልን        ለምለም
ጨለማው አልፎ      ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ                ለምለም(2)
ይኸው መስከረም   ለምለም
ይኸው ፀሐይ         ለምለም
ንጉሡ ወርዶ           ለምለም
ከላይ ሰማይ           ለምለም
አውደ ዓመት ሆነ     ለምለም
ደስታ ሰላም            ለምለም
ፍቅር ሲገለጥ         ለምለም
በአርያም                ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ                ለምለም(2)
ይኸው አበባ           ለምለም
ለምለም ቄጤማ      ለምለም
አዲሱ ዘመን           ለምለም
አምጥቷልና             ለምለም
በሩን ክፈቱ              ለምለም
መኳንንቶቹ              ለምለም
የክብር ንጉሥ          ለምለም
ይግባ ቤታችሁ        ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ                ለምለም(2)
ቤታችሁ ይሙላ      ለምለም
ሰላም ደስታ            ለምለም
ሰጥቷችሁ እርሱ     ለምለም
የሁሉ ጌታ              ለምለም
ከዘመን ዘመን         ለምለም
ያሸጋግራችሁ          ለምለም
የሽበትን ዘር            ለምለም
ይሸልማችሁ            ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ

ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ

ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
አርብ ሀገር ኬዊት ተክለሃይማኖት እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን  እንዲህ አከብረዋልን

የስንበት ተማሪ ህጻናት

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
አርብ ሀገር ኬዊት ደብር ምህረት ተክለሃይማኖት እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን  በበዓሉ የተሰጠው ትምህርት ወንጌል ነው

2015 ዓ.ም አጿሟት የሚውሉበት እለት ቅመር ተጠቅሱ አል በጥሞና ያዳምጡ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገረን አሽጋገራቸለ የሰላም የፍቅር የአንድነት የንስሐ ዘመን ያደረግልን ዘመገ ሉቃስ 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


ለመምህራችን በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን 💐💐💐💐💐💐💐

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
አዲስ ዓመት
ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመት ሲመጣ መደሰት፣ ብዙ መብልና መጠጥ ማዘጋጀት፣ አዲስ ልብስም መልበስ ጥቅም የለውም፡፡ ነፍሳችን በኀጢአት እየተጨነቀች፣ ነፍሳችን ተርባና ተጠምታ ሳለ፣ የተዳደፈ የኀጢአት ልብስም ተጆቡና ሳለ አዲስ ዓመት ማክበር ለእኛ ምን ጥቅም ይሰጠናል? እንዲህ ከገቢረ ኀጢአት ሳይወጡ አዲስ ዓመትን ማክበር ማለት ለእኔ እንደ ልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ ነው፡፡

ክርስቶስ ከዚሁ ሥራ አውጥቶናል፡፡ ከሕፃንነት አዕምሮ ወደ ማወቅ አሸጋግሮናል፡፡ ከምድራውያን ለይቶ ከሰማያውያን ጋር ደባልቆናል፡፡ ስለዚህ “መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ” እንደ ተባለ አፍአዊ ሳይኾን መንፈሳዊውን ብርሃን ልናበራ ይገባናል (ማቴ.5፡16)፤ በአዲሱ ዓመት፡፡ ይህም ብርሃን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን የሚያስገኝ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ! ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ? ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ? አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን? አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት” ያለንም ስለዚሁ ነውና በአዲሱ ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)፤ አዲስ ዓመት ማክበር ማለት ይኼ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ - #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ)
መስከረም 1 - ርዕሰ አውደ ዓመት

በግዕዝ አውደ ዓመት ይባላል - ርዕሰ አውደ ዓመት - የበዓላት ሁሉ የበላይ፣ ራስ ማለት ነው፡፡ በዓመቱ ውስጥ የሚውሉት በዓላትና አጽዋማት የሚወጡት መስከረም አንድን መነሻ አድርጎ ስለሆነ ርዕሰ አውደ ዓመት ተባለ። በአማርኛ ደግሞ እንቁጣጣሽ፣ የዘመን መለወጫ ወይም ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል፡፡ የዘመን መለወጫ የሚለው ግልፅ ስለሆነ ሁለቱን ስያሜዎች ለየብቻ እንመልከታቸው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ የተሰየመው በነቢዩ ዘካሪያስ ልጅ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንጂ በሐዋርያው/ ወንጌላዊው ዮሐንስ አለመሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ በብሉይና አዲስ ኪዳን መካከል የነበረ እና "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ የኖረ፣ በመጨረሻም በሔሮድስ ትዕዛዝ ራሱን የተቆረጠ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡

በዚህም ምክንያት የቤተክርስቲያን አባቶች የበዓላትን ስርአት ሲሰሩ፣ ይህ በዓል ለመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ መታሰቢያ እንዲሆንና በእሱ ስምም እንዲጠራ በመወሰናቸው ነው፡፡

ዕንቁጣጣሽ ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች ይሰነዘራሉና ተራ በተራ እንያቸው፡፡

አንደኛው በኖህ እና በልጆቹ ዙሪያ የሚያጠነጥን፡፡ ሴም፣ ካምና ያፌት ሶስቱ የኖህ ልጆች ናቸው፡፡ ኖህ አህጉራትን ለሶስቱ ልጆች አከፋፍሎ ሲሰጥ ለካም አፍሪካ ደረሰው፡፡ ካም ወደ አፍሪካ የገባው እና መጀመሪያ የረገጠው ኢትዮጵያን ሲሆን ወሩም ምድሪቱ በአደይ አበባ ያሸበረቀችበት የመስከረም ወር ነበር፡፡ በምድሪቱ ውበት በመደመሙና ይህ ዕጣም ለእሱ ስለደረሰው ተደስቶ “ዕንቁ ዕጣ ወጣልኝ” አለ፡፡ እንግዲህ እንቁጣጣሽ ለሚለው ቃል አንዱ የየት መጣ ሀሳብ /Etymology/ እንዲህ የሚል ነው፡፡

ሁለተኛው ምድሪቱ በአደይ ፈክታ ሲመለከት “ዕንቁ ዕፅ አወጣሽ” ከሚል ነው እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ የመጣ የሚል ነው፡፡

በዚህኛው አካሄድ “ዕንቁ” ከኦይስተር ቅርፊት /pearl/ ውስጥ የሚገኝ ትንሽ ድቡልቡል፤ ጠንካራ አንጸባራቂ፤ ነጭ ውድ ጌጥ/ ለጌጥነት የሚያገለግል ነገር/ ሲሆን “ዕፅ” ደግሞ በግዕዝ የአማርኛው “ተክል” አቻ ነው፡፡ ስለዚህ የተክሉን መልክ ከዕንቁ ጋር በማነጻጸር የምድሪቱን ውበት ለመግለጽ የተጠቀሙበት ነው፡፡

ሶስተኛው ደግሞ የቀዳማዊ ምኒሊክ እናት ንግስት ሳባ ሰሎሞንን ለመጎብኘት በሄደችበት ጊዜ ንጉሱ “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንልሽ” ብሎ መስጠቱን መሰረት አድርጎ የሚነሳ ሃሳብ ሲሆን ወሩም ወርሃ መስከረም ነበር።

#ቀሲስ_ንዋይ_ካሳሁን
Forwarded from ElroyPromotionBot
🙏🌼🌼በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።🌼🌼🙏
መዝሙር 65 ÷ 11
🌼🌻እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ አደረሰን🌻🌼2015
🔵እንደሃጥያታችን እንደበደላችን ሳይሆን እንደቸርነቱ ለአዲሱ አመት ያደረሰን ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

👉ይህ አዲስ አመት ከሁል ጊዜውም በበለጠ
🔹 ከአምላካችን ከመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የምንቀርብበት
🔹 መልካም ስራዎችን የምንሰራበት 🔹በጾም በጸሎት በምስጋናና በስግደት የተሞላ
🔹ጻድቃን ሰማእታትን የምናስብበት የምንዘክርበት እነሱንም አብነት አድርገን የምንለወጥበት መልካም ዘመን ይሁንልን።

አዲሱን አመት☀️በአዲስ መንፈስ☀️ ህይወታችንን የምንገመግምበት ችግሮቻችንን የምንፈታበት
አዲስ ምእራፍን በእውነተኛው ክርስትያናዊ ማንነት የምንገነባበት
የለውጥ ዘመን ይሆንልን ዘንድ እግዚአብሔር ይባርክልን እያልን በዚህ ዙርያ በስፋት ወደሚሰራ
ኦርቶዶክሳዊ ህይወት የተሰኘው የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲   █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


▶️ናታኒም ዩትዩብ◀️
[ቻናላችንን እንጠቁሞት
ቻናላችንን በመመልከት❤️ከወደዱት❤️ ደግሞ🔸ሰብስክራይብ🔸በማድረግ እርስዎም የመልካምነት ጉዞው ተካፋይ ይሁኑ።
👇👇👇
https://youtu.be/tx7239g4beI
https://youtu.be/tx7239g4beI
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲናያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ጽሁፎች ቻናል⛪️
Video
*አድርሶናል*
አድርሶናል ለአዲስ አመት እኛም
አዲስ እንሁንበት ያለፈውን
በይቅርታ አሻግሮናል የኛ ጌታ //

*አዝ=========*
አስረጅቶ ዘመንን
ቢያመጣልን አዲሱን
አይለወጥ እርሱ ከቶ
ዘመን ብሄድ ዘመን መቶ

*/አዝ =====*
ሁሌም ፍቅር ሁሌም መልካም
የሆነልን አይለካም
እየበደልን እየራራ
ዘመን ሰጠን ልናፈራ

*/አዝ =====*
በአዲስ ዘመን አዲሱ ሰው
እየሱስን እንልበሰው
የጥላቻን ቁስል ይድረቅ
ፍቅር ለብሰን እንታዎቅ

*/አዝ =====*
የምህረቱ ምንጭ አይነጥፍም
ለምፅ ያነፃል በጉጠት ፍም
ያሳለፍነው ይብቃንና
አዲስ እንሁን እንደገና

*አዝ =====*
የድንጋዮ ልብ ይወገድ
በሰዎች ላይ ይቅር መፍረድ
እንድንሆን እንደ ቃሉ
ፍቅር እናብብ ከመስቀሉ

_*ዘማሪት ህፃን አሜን ቴድሮስ*_
_*የሊ/መ/ዲ/ን ቴድሮስ ዮሴፍ ልጅ*_
ሶ*የብርሃን እናት*

እርእስ: የምህረት አዋጅ (ፍርድ ወይስ ፍቅር)

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2024/10/02 08:28:22
Back to Top
HTML Embed Code: