Telegram Web Link
*የብርሃን እናት*

እርእስ:- የእግዚአብሔር እንግዳ

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
ሊቀ መላክ

ሊቀ መላክ ኡራኤል አባት
ፀበልህም ያድናል በእውነት
በምልጃህም ያመኑ በሙሉ
ባንተ ይድናሉ/2/
አዝ............
ኡራኤል መላክ ያንተ ድንቅ ስራ
ኡራኤል መላክ አይመረመርም
ኡራኤል መላክ ድንቅ ነው ምህረት
ኡራኤል መላክ ማዳንህ ዘላላም
ኡራኤል መላክ ቸርነትህ ብዙ
ኡራኤል መላክ ምልጃህም ፈጣን ነው
ኡራኤል መላክ ፀጋህን አድለን ለኛለምናምነው
አዝ...........
ኡራኤል መላክ ማዳንክን ሰምቼ
ኡራኤል መላክ ስምክን ጠርቻለው
ኡራኤል መላክ አላሳፈርከኝም
ኡራኤል መላክ ባንተስ ኮርቻለው
ኡራኤል መላክ መንገዴ ባንተ ነው
ኡራኤል መላክ የኔ መታመኛ
ኡራኤል መላክ እኔንም ጠብቀኝ ከሀጢያት ቁራኛ
አዝ..........
ኡራኤል መላክ ለእዝራ ሱቱኤል
ኡራኤል መላክ ጥበብ እንዳጠጣህ
ኡራኤል መላክ በፅዋው ብርሀን
ኡራኤል መላክ ደሙን እንደረጨህ
ኡራኤል መላክ ሠላምን ልታስገኝ
ኡራኤል መላክ ዓለምን መዞርህ
ኡራኤል መላክ ማዳንህ ተገልፆል በቅዱስ ፀበልህ
Audio
"" ለምን ትሞታላችሁ? ""
       (ሕዝ. ፴፫:፲፩)

(ነሐሴ 25 - 2014)

በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር።
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
እንኳን አደረሳቹ ነሐሴ 26  <+>

+*" አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ "*+

=>እግዚአብሔር በ13ኛው መቶ ክ/ዘ እነ አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ባያስነሳ ኑሮ ምናልባትም ዛሬ የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያንን በምናያት መንገድ ላናገኛት እንችል ነበር:: እውነተኛ አባቶቻችን ፈጽሞ ከሚቆረቁራቸው ነገር አንዱ የጻድቅና ሐዋርያዊ አባት አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መዘንጋት ነው::

+እርሳቸው ፍሬ ሃይማኖት ሆነው ከጽድቅ ፍሬአቸው አዕላፍ ቅዱሳንን ወልደው ሃገራችን በወንጌል ትምሕርትና በገዳማዊ ሕይወት እንድታሸበርቅ አድርገዋል:: እስኪ በዕለተ ዕረፍታቸው ስለ ጻድቁ ጥቂት ነገሮችን እናንሳ::

+አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጐንደር : የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: የተወለዱት በ1210 ዓ/ም ነው:: ነገር ግን አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ/ም ያደርጉታል::
Audio
*💠ለምን ሰላም አጣን 💠*

ለምን ሰላም አጣን ፍቅራችን ወደት ነው
አንድ የምንሆንበት ዘመኑ መቼ ነው
በቃበልን ጌታ ቸሩ አምላካችን
ሰላም ይስፈንባት ኢትዮጵያ ምድራችን(፪)



እየተከፈለ በጎሳና በዘር የሰው
ልጅ ጨከነ ለማይኖርበት ምድር
ወንድም በወንድሙ ፍፁም እየቀና
ደም መራጭት ሆነ ሰው መሆን ቀረና



*አዝ።።።።።።*

የሰው ልጅ በሀሰብ በፍቃዱ አበደ
ሰላም ፍቅር አቶ በዱር ተሰደደ
ልጅ ያለ አባት አይቅር አባት ያለጧሪ
የመንጋውን እንባ ተመልከት ፈጣሪ


*አዝ።።።።።።*


ወንድም ለወንድሙ መቃብር ቆፈረ
አፈር አለበሰ ቀና እንዳይል እያለ
አሁን ለየትኛው ለቀሪው እድሜ ነው
የሰው ልጅ በክፍት የሚጨካከነው


*አዝ።።።።።*

እግዚኦ ኤልሻዳይ የሰማይ አዶናይ
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታይ
እንደ በደላችን ሳይሆን በምህረትህ
ሰላም ፍቅር ያለው ይዘጋልን እጅህ


*አዝ።።።።።።*


ወንድሞች በህብረት እንኖር ተስማምተን
ሰላምን እንስበክ ጸብን አስወግደን
በሰላም ተስማንተን እንኑር በጋራ
በተሰጠን እድሜ በልካሙን እንስራ

💦💦💦💦💦💦💦💦💦
ዘማሪ ዳ/ ን ኃይለ መስቀል በቃሻው
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃
2024/10/02 12:28:50
Back to Top
HTML Embed Code: