Telegram Web Link
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
✥የዓብይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት✥

            ✥ቅድስት✥

በመባል የታወቃል ።

በዚህ ቀን እግዚያአብሔር አምላክ ቅዱስ ነውና እኛም ቅዱስ እንድንሆን ይፈልጋል ሁሉም የተቀደሰ ህይወት እንዲኖረው ይሻል። እኛም እርሱን መስለን በሮሜ 8÷28 የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቅድሞ ወሰነ ይላልና። እግዚያአብሔር አምላክ በቅድስና እንዲመራን የርሱ መልካም ፍቃድ ይህውንልን።

ሌላው ግን በዚህ ጊዜ ቅድስት ተብሎ በሚታወቀው ሳምንት ውስጥ የምናስበው ምንድነው? ስንል ሰንበትን ነው። እግዚያአብሔር አምላክ ሰንበትን እንደቀደሳት ሰንበትን ቀድሶ ለኛ ቅድስት አድርጎ እንደሰጠን የሚያሳይ ነው።

ሰንበት ስናከብር ሁለት ሰንበት እናከብራለን።
በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን።
1ኛ ቀዳሚ ሰንበት
2ኛ ሰንበተ ክርስቲያን
የክርስቲያን ሰንበት ቀዳሚ ሰንበት የተባለቺው #ቅዳሜ ነው። ለምሳሌ ውዳሴ ማርያም በንደግምበት ሰዓት ውዳሴሃ ለእግዝተነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ። ይላል።

የቀደመች ሰንበት የአይውድ ሰንበት ወይም በብሉይ ዘመን የምትከበር ሰንበት ሁሉም ሰው ሊያከብራት የምትገባ ሰንበት። ዘፍጥረት 2÷3 እግዚያአብሔር አምላክ ሁሉን በስድስት ቀን ከፈጠረ በዋላ በሰባተኛው ቀን አረፈ የሰባተኛው ቀንም ቀደሰው።
አከበረው ሰንበት አለው። ዘጸአት 20 ላይ ስንመለከት ከአስርቱ ትዛዛት አንዱ ሰንበቴን አክብር ነው። ወይም ሰንበትን አክብር ነው።

እዚህ ሰንበት ቅዳሜ ላይ ጌታ ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ አረፈ ። ለምን አረፈ?
ደክሞት በፍፁም አይስማማውም።
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባው።
ከምንሰራው ስራ አርፈን እግዚያአብሔርን እናመሰግነው ዘንድ ነው።
ስለዚህ ቅዳሜ የስጋ እረፍት ነው።

2ኛ ሰንበት እውድ ነው።
እውድን ሰንበት እንደውም የቀኖች ሁሉ ንግስት ነው የሚላት አትናቲዮስ ሲጠራት ። የእለታት ሁሉ ንግስት አባይ ታላቅ እለት ይላታል።

ለምን ?
በዚህ ቀን ደሞ ነብሳችን አርፋለች።
እንዴት ? አለምን በስድስተኛው  ቀን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ያረፈው የሁሉ ፈጣሪ እግዚያአብሔር አለምን ለማዳን በጀመሪያውስንመለከት ትምህርት ዘወረደ እንደተመለከትነው ወርዶ ወደዚህ መቶ ነብሳችን በህለተ ሰንበት እውድ አሳረፋት። ማቴ 28÷1 ዮሐ 20÷1  በመቃብሩ ስፍራ በህለተ ሰንበት ወይም ደግሞ የሰንበቱ መጨረሻ በመጀመሪያው የሰንበት ቀንእነሆ ወደ መቃብሩ ስፍራ ኤዶ መቃብሩ ግን ባዶ ነበር። ነብሳችን ያረፈችበት ሰንበት እለተ ሰንበት እውድ ነበር ። እውድ ደግሞ ሰንበት ተብሎ ይጠራል።

1 ቀዳሚት ሰንበት ።
2 እውድ ሰንበት ።
ይኤንን እነሆ ሰንበታቴን አክብሩ ብሎ እንደተናገረ እነዚህን እናከብራለን ።

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በፍጥሞ ደሴት ሳለው ይላል ። ራይ 1÷10 ላይ በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርኹ አለ። የጌታ ቀን የሚላት እውድነው። ሐዋሪያት የጌታ ቀን ብለው ይጠርዋታል ።
ቅዳሜ ሥጋችን ያረፈበት የሚያርፍበት
እውድ ደግሞ ነፍሳችን የሚያርፍበት ልዩ ቀን ነው።  ቅድስት ሲል እግዚያአብሔር ቅዳሜን እግዚያአብሔር እውድን ለውላችን ቅድሶ ሰጠን ።

በዚህ ቀን አርፈን የታመመን እንድንጠይቅ ድውያን እድንጠይቅ እግዚያአብሔር ይፈልጋል።

ለስጋ ብቻ መሮጥ አይደለም ወገኖቼ ለዓለማዊ ነገር ብቻ መክነፍ አይደለም።
እግዚያአብሔር ዛሬ ይጠይቀናል ።
በዚህ ቀን ችግረኞችን እንድንጠይቅ እግዚያአብሔር ይሻል።

                   ✥

የህለተ ሰንበ በረከት እረድኤት ከኛጋር ይኑር።

ሼር በማድረግ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ።

👇👇👇👇👇👇👇
╔═✟✞════🇨🇬    ════✟✞═╗
         @dmse_tewado                       @orthodoxswi_eywet
╚═✟✞════🇨🇬    ════✟✞═╝
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ይህ ዘመን የተመቸው ለአቡነ ሩፋኤል ብቻ ነው የተመቸው አይሰግዱ አይፆሙ እንዲ ደልበው ።

እኛማ መነኮሳት የአብነት ተማሪዎች  ምዕመናን እየታረድን እየተሰደድን  ነው ።
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 4

ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ወሰደው ለመምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን

ዐቢይ ፆም ሁለተኛ ሳምንት  ቅድስት ትባላለች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፆም የጀመረበት ሳምንት እና ከዲያብሎስ የተፈተነበት ነው  ይህ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 4ኛ ላይ ይገኛል
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
መታዘዝ

"አቤቱ ጌታ ሆይ:- አንተ ወደዚህ ዓለም መጥተሃል::ለእናትህ ለቅድስት ድንግል ማርያምና ለቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ ራስህ ፈጣሪ ሆነህ ሳለህ ለፈጠርሃቸው ሰዎች በፍቅር ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ እኮ ሰማይና ምድር የሚታዘዙልህ አምላክ ነህ! መታዘዝህ ሥልጣንህን አያጠፋውም:: መታዘዝን በእኔ ውስጥ ቀድስ  ከመታዘዝ ሩጬ እንዳላመልጥ ከአንተ ጋር እሰረኝ:: እኔ በአንተ መታዘዝ ውስጥ ተካፋይ መሆኔ ይታወቀኝ ዘንድ ትእዛዝህን እቀበላለሁ:: በእኔ ዐይኖች ፊት እንደመገረፍ ስለሚቆጠር መታዘዝ ለእኔ መራራ ነው:: ከአንተ ጋር ከሆንኩኝ ግን እጅግ ጣፋጭ ነው:: የአንተን የመታዘዝ ልምድ ለእኔ አስተምረኝ፣አለማምደኝ አድለኝም:: ይህን ካደረግህልኝ እውነተኛ ትዛዥ የሆንኸው አንተን በእኔ ውስጥ ስትሰራ እመለከታለሁ::ጽድቅን ለመፈፀም ታዛዥ የሆንኸው አንተ ለእኛ ምሳሌ ነህ::" /ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ

@dmse_tewado
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ቅዱሳን አንተን ባወቁበት መጠን አውቅህ ዘንድ እሻለሁ የቅዱሳኑ ንፅህና ግን በእኔ ዘንድ የለም። እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች።አቤቱ ጌታዬ ሆይ አደከመቺኝ አንተን በፍፁም ንፅህና አፈልግህ ዘንድ ከለከለቺኝ።ደክሞኝም ፈፅሜ እንዳልተውህ ያቀመስከኝ የፍቅርህ ጣዕም ትዝ ይለኛል። አቤቱ ተጨነኩ አንተስ እስከመቼ ዝም ትላለህ? እስከመቼስ ለፈቃዴ ትተወኛለህ?...

አቤቱ አንተን እንደወደዱህ እንደ ቅዱሳንህ ከፈቃዴ እንድሰዋልህ ቅድስት የምትሆን በጎ ጭካኔንን አስጨክነኝ።

“ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ”
  — መዝሙር 54፥6


https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#ለሰይጣን_ጊዜ_የለኝም

መምህሩ ተማሪዎችን ሊፈትን በአንድ ሰዓት ውስጥ የሚመለሱ ሁለት ጥያቄዎችን አዘጋጀ። ተማሪዎች ራሳቸውን አዘጋጅተው ወደ ፈተና ክፍል ገበተው ወንበር ወንበራቸውን ይዘው ይጠብቃሉ። መምህሩ የፈተና ወረቀቱን ይዞ ገባ። የፈተናውን መመሪያ ተናግሮ የፈተና ወረቀቱን አደለና ሰዓት ይዞ "መጀመር ትችላላችሁ" አላቸው።

የመጀመሪያው ጥያቄ ስለ እግዚአብሔር የምታውቀውን ጻፍ የሚል ነው። ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ ስለ ሰይጣን የምታውቀውን ጻፍ ይላል፡፡ "ለአንዱ ጥያቄ 30 ደቂቃ ነው የተሰጠው ማለት ነው" ብለው ሰዓት ሳያልቅባቸው ሁለቱንም ጥያቄዎች ለመጨረስ ተሎ ተሎ ይጽፋሉ። ፈተና ከተጀመረ 30 ደቂቃ መሙላቱ ሰዓት ያዩ ተማሪዎች ከአንደኛው ጥያቄ ወደ ሁለተኛው አልፈው መስራት ጀምረዋል፡፡ በአእምሮአቸው የመጣላቸውን ሐሳብ በቻሉት ፍጥነት ይጽፋሉ፡፡ መምህሩም ሁሉም ተማሪ የየራሱ መስራቱን እየዞረ ይከታተላል።

"ለማጠናቀቅ አስር ደቂቃ ይቀራችኋል" አለ መምህሩ። መልሰን ጨርሰናል ብለው ያሰቡ ተማሪዎች ግማሾቹ ፈተና ወረቀቱን ለመምህሩ ሰጥተው ሲወጡ፥ ሌሎቹም የመለሱትን ደግመው ያነባሉ፡፡ ያልጨረሱም የቀረችውን ደቂቃ ለመጠቀም ይጣደፋሉ። ከአስር ደቂቃ በኋላ "ሰዓት አልቋል ሁላችሁም መስራት አቁሙ" አለ መምህሩ፡፡ እየዞረም ፈተና ወረቀቱን መሰብሰብ ጀመረ፡፡ አንድ ተማሪ ጋር ሲደርስ ግን አሁንም መልስ እየጻፈ ያገኘውና "ሰዓት አልቋል ሲባል አትሰማም እንዴ?" ብሎ ወረቁትን ተቀበለው፡፡

ሁሉም ተማሪዎች ለሁለቱም ጥያቄ የሚያውቁትን የመለሱ ሲሆን አንዱ ተማሪ ግን ለጥያቄ ቍጥር አንድ (ስለ እግዚአብሔር የምታውቁትን ጻፉ ለሚለው) ብቻ ነው መልስ የሰጠው። መምህሩ በዚህ ተማሪ መልስ ተገርሞ "ለምንድ ነው ለሁለቱንም ጥያቄዎች መልስ ያልጻፍከው?" ብሎ ጠየቀው። እርሱም "#ለሰይጣን_ጊዜ_የለኝም" ስለ እግዚአብሔር ራሱ የማያልቅ ቢሆን እኮ ነው የተሰጠን ሰዓት አልቆ ገና እየጻፍኩ ያስቆምከኝ" አለው ይባላል፡፡

እውነት ነው ነገረ እግዚአብሔር ቢጽፉት፣ ቢናገሩት፣ ቢሰሙትና ቢያዜሙት የማያልቅና የማይሰለች ጥልቅ ምሥጢር ነው። የፈለግነው ያህል ጊዜ ብንሰጠው እንኳን በጅምር እያለን ጊዜው ያልቃል። በቃሉ ፍቅር፥ በምሥጢሩ ተመስጦ ውስጥ ሆነን ወደማያልፈው ዓለም እንሻገራለን፡፡

ይህንን ገንዘብ ለማድረግ ግን ለሰይጣንና ለጉዳዮቹ የሚሆን ጊዜ የለኝም ማለት ይገባል፡፡ ከጊዜ ውጭ የሚሰራ ነገር የለምና ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን ከኃጢአት ሁሉ መራቃችን አይደል? ለሰይጣን ጊዜ ላለመስጠት ደግሞ ከእርሱ ጋር መጣላት ነው። መቼም ሰው ለጠላው ነገር የሚሆን ጊዜ አይኖረውም። ምንም ስራ ባይኖረውም እንኳ ከጠላው ጋር ላለመገናኘት ምክንያት ፈጥሮ ይርቅ የለ? ስለዚህ ለሰይጣን ጊዜ እንዳይኖርህ ከእርሱ ጋር ተጣላ። የሚገርመው ከሰይጣን ጋር ስትጣላ ደግሞ ከሰው እና ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር መኖር ትችላለህ፡፡ ከ24ቱ ሰዓት ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን መቼም ቢሆን ኃጢአት ሊያሰራን የሚችልበት ዕድል ወይም አጋጣሚ አይኖርም። የተሰጠን ጊዜ ለሰጪው አምላክ መልሰን እንሰጠው ዘንድ ማስተዋሉን ያድለን።
2024/11/04 21:36:16
Back to Top
HTML Embed Code: