Telegram Web Link
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ፆመ ነነዌ  ከሰኞ - ዕሮብ (ከየካቲት 18 -20 )

የነነዌን ህዝብ ጸሎት የሰማ አምላክ የኢትዮጵያንም ህዝብ ልመና ለቅሶ ችግር ይሰማ ዘንድ ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን አሜን፡፡

           ፆመ ነነዌ

ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው::በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ግን 7 ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል::እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች::
    ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ፰፻ ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ::

  ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ ገራገር የለምና እንቢ አለ ሰምቶ ዝም አለ:: እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ ተርሴስ ኮበለለ።
     ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሽ እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ:- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው::

   ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን ሌሊት ኖሮ: ሙስና ጥፋት ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ ምሳሌ ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው:: "ወበከመ ነበረ ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: ማቴ. 12:39

   ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት እጣ ወድቆበታልና የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው::
     እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ3 ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ3ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው::ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ::

የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል::
    የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቁዋ ነነዌ ከ፫፻ ዓመታት በኃላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም 170 ዓመት ነው::

አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን::
በጾመ ነነዌ ስለ ሃገርና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት መጸለይ ይገባል::
  ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ(ጌታችንን) በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ::
                    ማቴ. 12:39
ለሀገራችን ሰላም ለምድራችንም በረከትን ያድልልን!!
       ወስብሐት ለእግዚአብሔር
        ወለ ወላዲቱ ድንግል
         ወለመስቀሉ ክብር

https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
​​"4 ተገድለው 1 ጠፍተዋል፤ ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ"
የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች
++++++++++++++++++++++++++++++

የገዳሙን መጋቤ እና ዋና ጸሐፊ ጨምሮ የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም 4 መነኮሳት በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

ከገዳሙ በስልክ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው የካቲት 12/2016 ዓ.ም የታጠቁ ሰዎች ወደ ገዳሙ በመግባት ሁለት መነኮሳት መውሰዳቸውን እነሱ ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቁ በማግስቱ የካቲት 13/2016 ዓ.ም ታጣቂዎቹ ድጋሚ መጥተው ለውይይት እንፈልጋችኋለን በማለት 3 መነኮሳትን ወደ "ጂዳ ተክለ ሃይማኖት" ወስደዋል ብለዋል።

መነኮሳቱ "ለውይይት" ሲባሉም "ችግር የለውም እናንተ አባቶች እዚህ ቆዩ እኛ አነጋግረናቸው እንመጣለን፤ ተረጋጉ" ብለው ታጣቂዎቹን ተከትለው ከገዳሙ ሂደዋል።

ቀኑን ሙሉ ስልካቸው ክፍት እንደነበረ አመሻሽ ማግኘት ባለመቻላቸው ተጨንቀው የአካባቢውን ምእመናን ሲያጠያይቁ 4ቱ መገደላቸውን እንደነገሯቸው አንደኛው አባት ግን ተለቀዋል ቢባልም እስካሁን ያሉበት እንዳልታወቀ አባቶቹ ለጣቢያችን በእንባ ተናግረዋል።

በታጣቂዎቹ የተገደሉት አባቶች

፩ አባ ተክለ ማርያም አሥራት (የገዳሙ መጋቤ)

፪ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን (የገዳሙ ዋና ጸሐፊ)

፫ አባ ገብረ ማርያም አበበ (ቀዳሽ ካህን፣የመጽሐፍ መምህርና የገዳሙ አስተዳደር አባል)

፬ ባህታዊ ኃ/ማርያም ስሜ (የገዳሙ የአስተዳደር አባል)
ሲሆኑ
እስካሁን ያሉበት ያልታወቀው ደግሞ አባ ኪዳነ ማርያም ገ/ሰንበት ናቸው።

ገዳሙ በተደጋጋሚ በታጠቁ ሰዎች ዐይነተ ብዙ ጥቃት እንደሚደርስበት ነገር ግን መፍትሔ እንዳላገኙ በመግለጽ የአሁኑ ጥቃት ግን በቃላት የማይገለጽ ነው ብለዋል።

"ገዳሙን እና እኛን ለማዳን እነሱ ተሰው፤ የእኛንም በደል እነሱ ከፈሉ፤ ጻድቁን አገልግዬ እዚሁ አርፋለሁ ሲሉ ደመ ከልብ ሆነው ዐፈራቸውንም ሳይቀምሱ ቀርተዋል" ሲሉም መረጃ የሰጡን አባቶች በከፍተኛ ሐዘን ገልጸዋል።
"መሠረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው" | Meseretua Gulelatua New | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
"መሠረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው"

ሙሽራዋም መስቀል ላይ የሞተው
ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘለዓለም
አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም /2x
+++
የእንግዳው ትምህርት የጠላት እንክርዳድ
በመከሩ ጊዜ ይለያል ሲታጨድ
ጌታ ጌታ ያለው እንዲሁ በብልጠት
አይወርስም ፈጽሞ የሰማዩን ርስት
+++ አዝ+++
ራስ ለሆነለት ሆናለች አካሉ
ትታዘዘዋለች ዘወትር ለቃሉ
የፊት መጨማደድ ሳያገኛት ድካም
ታምና ትኖራለች እስኪመጣ ዳግም
+++ አዝ+++
የሰማዕታት ደም የከፈሉት ዋጋ
የመላዕክቱ ዜማ የሰማዩን ፀጋ
የሐዋርያት ስብከት የነቢያት ትንቢት
ይገኛል በውስጧ በፀጋዋ ግምጃ ቤት
+++ አዝ+++
ጎዳናውን ጥሰን ብንጓዝ በሐሰት
ለአንደበታችን አውጀን አርነት
አይዘጋም ደጅዋ አይጠፋም መብራቷ
ኢየሱስ ነው ክብሯ ጌጥና ውቤቷ

+++አዝ+++

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
               
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#ኪዳነ ምህረት  #16

ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡

ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መጥተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡

እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡

ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ በራሴ በአባቴና በመንፈስ ቅዱስ ስም ቀል እገባልሻለው ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል።

በዚህም የተነሳ እመቤታችን እኛን በምልጃዋ የምታስምርበተ ፣ ጥያቄያችንን የምታስመልስበት ፣ እንቆቅልሻችንን የምታስፈታበት የምህረት ኪዳን የካቲት 16 ተቀብላለች እና ኪዳነ ምህረት እንላታለን ።

https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
# መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል

❖  ከ7ቱ ሊቀነ መላእክት አንዱ ነው።

❖ ገብርኤል ማለት የስሙ ትርጉም የእግዚአብሔር ልጅ የሚመስል የእግዚአብሔር ሰው ማለት ሲሆን
ት.ዳን 3+25ሕዝ 9፥2 በተጨማሪም መጋቤ ሐዲስ( የሐዲስ ኪዳን አስተማሪ) እግዚእ ወገብረ (እግዚአብሔር አደረገ ) ማለት ነው።

❖ ብስራታዊ (አብሳሪው) መልአክ ነው። እመቤታችንንና ዘመዷ ኤልሳቤትና አብስሮአልና።

❖ ቅዱስ ገብርኤል አርባብ የተበለው ነገደ መላእክት አለቃ ነው።

❖ በመጀመሪያው የመላእክት ጦርነት ጊዜ አምላካችንን እስክናውቅ ባለንበት ፀንተን እንቁም በማለት መላእክት ያፀናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው።
❖ ተራዳዩ መልአክ ነው።

ዳን ፫፥፲፱-፳፯፣ዳን ፰፥፲፭ ዳን፱፥፳፩-፳፯
❖ ቅዱስ ገብርኤል ከ፯ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው።

❖ በጎ በጎውን የምንሰማበት መልካም መልካሙን የምናደርግበት መልካም ቀን ይሁንልን።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#መልካም እለተ ይሁንልን

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል
https://www.tg-me.com/dmse_tewado
2024/06/30 22:09:50
Back to Top
HTML Embed Code: