Telegram Web Link
አንዳንድ ነጥቦች በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ መከልከል ዙሪያ፦
1. ለዚህ አሳዛኝ ድርጊት የተቀነባበረ ሽፋን በቅርብ ሲሰጥ እንደምንሰማ የታወቀ ነው። በመንግሥት አካላት ተደርሶ የሚቀርበው ድራማና ዶክመንተሪ አያልቅምና ያልሠሩትን ወንጀል ሲያሸክሟቸውና ሲያጥላሉዋቸው እንሰማ ይሆናል። ስለዚህም ከሚዲያ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልሳን የሆኑ ሚዲያዎችን ብቻ እንከታተል።
2. መንግሥት ይህን መሰል አንገት ሰባሪና ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ሲፈፅምም ብፁዕነታቸው ያሉበትን ኃላፊነት ከግምት አላስገባም። ክብራቸውን የሚወክሉትን ቤተ ክርስቲያንና ሕዝባቸውን አላከበረም። በዚህ ጸያፍ ድርጊቱ እርሳቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝን እንዳሳዘነ መታወቅ አለበት።
3. ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሸክም ጎንበስ ብለው የሚሸከሙ አባት ናቸው። የዛሬው የመንግስት ድርጊት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ከሜዳው በማግለል የቅዱስ ሲኖዶስን ማዕከላዊነት የመናድ ሙከራ ነው።
4. ብፁዕነታቸው በእምነታቸው የማይደራደሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ እርሳቸውን ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የማድረግ ርምጃ የቤተ ክርስቲያንን በር የበግ ለምድ ለለበሱ ተኩላዎችና ለእንደ ልቡዎች ክፍት የማድረግ ዕቅድ አካል ነው። ከዚያም ውጪ ሌሎች ውጪ የሚኖሩ አበው ብፁዓን አባቶችንም አፍ የማስያዣ አካሄድ ነው።
5. በሌላ በኩል በውጪ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቁጣቸውን ማሳደር አለባቸው። ምክንያቱም መንግሥትም ሆነ ሕገ ወጥ አካላት በተለያዩ ሚዲያዎች በኩል ይህን ነገር እያራገቡ ጫና ፈጥረው ሌላ ሲኖዶስ እናቋቁም የሚል ሀሳብ እንዲፈጠር መሥራታቸው አይቀርምና በዚህ በኩል ረጋ ብሎ  መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ተተኪ ጸሐፊ ይመረጥ የሚል ሤራ እንዳይሸርብም ነቅቶ መጠበቅና መሥመር ማስያዝ እንደሚገባው ሳይረሳ!!
6. ይህ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የታሰበ እቅድ ነው። ስለዚህም እንደ ምእመን በበለጠ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ማተኮርና ቤተ ክርስቲያናችንን በንቃት መጠበቅ አለብን።
7. ይሄ ጉዳይ መሥመር እንዲይዝ የሚያደርጉ አባቶችን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ማገዝና ትዕዛዛቸውንም እንደ ልጅ መፈጸምም ይገባናል።
ልዑል እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

#ኢንፈርህሞተ
#ሞትንአንፈራውም
ብርሃኑ ተ/ያሬድ
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
" " " " ኢየሱስ ማን ነው?" " " "
     ❖ ❖ ❖
"እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ?"
(የማቴዎስ ወንጌል 16:15)

ይሄ ጥያቄ ከክርስቶስ ለሐዋርያቱ የቀረበ ቢሆንም ህያው ሆኖ ይሰራልና ለእኛም የተጠየቀ ነው!
ስለዚህ እናንተ ክርስቶስን ማን እንደሆነ ትላላችሁ? የሚለውን ጥያቄያችንን ለልባችሁ በመተው በዚህ ተከታታይ ፅሁፍ የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ አንጻር እንማማራለን።
ኢየሱስ ክርስቶስ የክርሰትናችን መስራች የሃይማኖታችንም ራስ በመሆኑ እርሱን በሚገባ ማወቅ ከእኛ ከክርስቲያኖች ይጠበቃል። እርሱን ማወቃችንም ለሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይረዳናል።

1. እርሱን አውቀን በህወታችን ያለውን ድርሻ ተረድተን ለእርሱ እንድንታዘዝና በአግባቡ እንደናገለግለውና እንድናመልከው

2. የምናውቀውን ለማያውቁትና ላልተረዱት በሚገባ ለማስረዳትና ወደ እውነተኛው የክርስቶስ ማንነት እንዲመጡ ለማድረግ

3. በዘመናች ኢየሱስ ክርስቶስን በተመለከተ ሰዎች ያላቸው አስተሳሰብ አራምባና ቆቦ ስለሆነ ጥያቄዎችንም ስለሚጠይቁን ለእነርሱ መልስ ለመስጠት ነው።

4- ዋናው ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ የዘለዓለም ህይወት ነው!! የሐ17-2፤4

ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በተመላለሰበት ጊዜ ሰዎች አውቀውት ተረድተውት እንደሆነ ይጠይቅ ነበር። ለምሳሌ በፊሊጶስ ቂሳርያ ሐዋርያቱን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል ብሎ ጠይቋቸው ነበር። ሐዋርያቱም ክብር ይግባውና ሰዎች የሚሉትን ተርከውለታል ።ማቴ 16፡18፤ማር 8 ። በዚያ ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ክርስቶስን ኤልያስ ነው፤ሙሴ ነው፤ ዩሐንስ ነው፡ ኤርሚያስ ነው ከነዚህም ካልሆነ ከነቢያት አንዱ ነው ይሉ ነበር። ሌሎቹም
ጋኔል አለበት ብለውታል የሐ 10፤20 ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የነቢያት አምላክ ነበር ሰዎች ባይረዱትም ቅሉ።
ሌሎቹም ካስተማራቸው ትምህርት የተነሳ ይህ ማን ነው የጸራቢው የየሴፍ ልጅ የማርያምስ ልጀ አይደለምን? ወንድሞቹ .. እህቶቹም በእኛ ዘንድ አይደሉምን? እያሉ ተሰነካከሉበት።ሉቃ 4፤16-22
ሆኖም ሁሉም ባያውቁትም ሐዋርያቱ ግን በሚገባ ተረድተውት ነበር ለዚህ ነው ሐዋርያው ቅዱሰ ጴጥሮስ አንተ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ የመለሰው። ቅዱሰ ጴጥሮስም አንተ የህያው እግዚአብሔር ልጀ ነህ በማለቱ ብጹዕ ተባለ፤የቤተ ክርስቲያን አለት እንዲባል ሆነ።

ወገኖቸ በዛሬው ጊዜ ኢየሱስን አንዱ ፍጡር/ነብይ/ ሌላው መልአክ ሌላም ሌላም እያሉ ይሳለቁበታል በእርግጥ እኛ አውቀነው ይሆንን?

ለመሆኑ ይህ ኢየሱስ ማን ነው?
ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢት ሳያናግር ሱባኤ ሳያስቆጥር እንዲሁ ከሰማያት የወረደ አይደለም። ይልቁንም ትንቢት አናግሮ ሱባኤ አስቆጥሮ ከሰማየ ሰማያት ወረደ እንጂ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሱባኤ አስቆጥሮ ቢመጣም እንኳን ሱባኤውን እንቆጥራለን የሚሉ
አይሁድ ማወቅ አልቻሉም እርሱ የመጣው በደካማ ስጋ ነበርና።

ዛሬም ሰዎች ክርስቶስ በደካማ ስጋ መምጣቱን ተመልክተው ብዙዎች እርሱን በሚገባ ለማመንና ለማዎቅ አቃታቸው። ክብር ለእርሱ ይሁንና እርሱ ኢየሱስ ማን ነው። እርሱ የማሰናከያው ድንጋይ እርሱ የማዕዘኑ ድነጋይ፤ ያ ከአለት የፈሰሰው እና በጥም
የነበሩትን በበረሃ የተቃጠሉትን ያረካው ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?

ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን፦

           ይቀጥላል............
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ህይወትህን በሙሉ ለምድራዊ ነገር አሳልፈህ ከሰጠህ ምድር መቃብርን ትሰጥሃለች፤ ነገር ግን ህይወትህን ለመንግስተ ሰማያት አሳልፈህ ብትሰጥ ግን መንግስተ ሰማያት ዙፋንን ትሰጥሃለች።
ምክረ አበው
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ህይወትህን በሙሉ ለምድራዊ ነገር አሳልፈህ ከሰጠህ ምድር መቃብርን ትሰጥሃለች፤ ነገር ግን ህይወትህን ለመንግስተ ሰማያት አሳልፈህ ብትሰጥ ግን መንግስተ ሰማያት ዙፋንን ትሰጥሃለች።
ምክረ አበው
#ጌታችን ስምኦን ቤት ተቀምጦ ሳለ፣ መላ #ህይወቷን_ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቶዋ ማርያም)፤‹‹ከእንግዲህ ወዲህ #በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን #ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል #አምላክ_መጣ›› ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦሰት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ(በራሱ)ላይ በማርከፍከፍ ጌታችንን ቀብታዋለች በረከቷ ይደርብን

        
#መልካም__ቀን🙏
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ኢየሱስ ማን ነው?
           ክፍል -፪
<< ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን መፅሐፍት >>

የክርስቶስ ኢየሱስ መምጣት ድንገተኛ ዱብዳ ወይም በአጋጣሚና አይደለም ! መምጣቱን በብሉይ ኪዳን በብዙ ቦታዎች በትንቢት ተናግሮ ነው የመጣው። ይህም ማን እንደሆነ በሚገባ እንድናውቀው ከሀሰተኛው መሲህ እንዲለይ ያደረገው ነው። በዚህ ምክንያት ይልቅ የትውልድ ናፍቆት ነበረ እንጂ። ከ -እስከ ተብሎ ዘመን የማይቆጠርለት አልፋና ኦሜጋው ዘመን ተቆጠረለት እርሱ ራሱ መጥቶ ያድናችሗል እንደተባለ ሊያድነን የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ በትንበቱ እና በቃሉ መሰረት ነው። ከዚህ ቀጥለን በአጭሩ በብሉይ ኪዳን ስለ ኢየሱስ በትንቢት የተነገሩና በክርስቶስ የተፈጸሙ ጥቅሶችን እንመለከታለን፦

፩. ክርስቶስ ከይሁዳ ነገድ እንደሚወጣ፦
በትረ መንግስት ከይሁዳ አይጠፋም የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአህዛብም መታዘዝ በእርሱ ይሆናል። ዘፍ 49፤10 ፍጻሜው የጌታችን የትውልድ ሐረግ ከይሁዳ ነገድ መሆኑ ሉቃ 3፤23-28

፪. ጌታ በድንግልና ተጸንሶ በድንግልና እንደሚወለድ፦
እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ኢሳ 7፤14 ፍጻሜው ማቴ 1፤23 በነብይ በጌታ ዘንድ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆነ!!

፫. ጌታ በቤተ ልሄም እንደሚወለድ:-
ሚኪ 5፤2 አንች ቤተልሄም ኤፍራታ ሆይ አንች ከይሁዳ አእላፍ መካከል ትንሽ ነሽ … ከአንች ከአወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ የሆነ በእስራኤል ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል ፍጻሜው ሜቴ 2፤4-6 ሔሮድስ ካህናቱን በጠየቃቸው ጊዜ … ህዝቤን እስራኤል የሚጠብቅ ከአንች ይወጣል

፬. ወደ ግብጸ እንደሚሰደድ:- ሆሴ 11፤1 ፍጻሜው ማቴ 2፡13-15

፭. በዩርዳኖስ እንደሚጠመቅ መዝ 68 ፤ፈጻሜው ማቴ 3

፮. ስበከቱን በገሊላ እንደሚጀምር:- ኢሳ 9፤1-2 ፍጻሜው ማቴ 4፤1-2

፯. በሆሳዕና እለት በአህያ ተጭኖ እንደሚመጣ:- ዘካ 9፡9 ፍጻሜው የሐ 12፤13-14

፰. በሰላሳ ብር እንደሚሸጥ:- ዘካ 11፤12-13 ማቴ 26፤15

፱. ሲከሱት ዝም ስለማለቱ:- ኢሳ 53፤7 ማቴ 26፤62-63

፲. እንደሚመታ እንደተተፋበት:- ኢሳ 50፤6 ፍጻሜው ማር 14፤65

፲፩. ከሐጢያተኞች ጋር እንደተሰቀለ:- ኢሳ 53፤ ፍጻሜው ማቴ 27፤38

፲፪. እጅ እና እግሩ ስለመቸንከሩ መዝ 22 ፤16 ፍጻሜው የሐ 20፤25-27

፲፫. እንደ ተሰደበ እና እንደተላገጠበት መዝ 22፤6-8 ፍጻሜው ማቴ 27፤36-40

፲፬. ሆምጣጤ እንደሰጡት መዝ 69፤21 ፍጻሜው የሐ 19፤29

፲፭. አጥንቶቹ እንደማይሰበሩ መዝ 34፤20 ፍጻሜው የሐ 19፤33

፲፮. ጎኖቹ እንደተወጉ ዘካ 12፤10 ፍጻሜው ዮሐ 19፤34

፲፯. ልብሱን እንደሚካፈሉ መዝ 22፤18 ፍጻሜው ማር 15፤24

፲፰. ከሙታን እንደሚነሳ መዝ 16፤10 ፍጻሜው ማቲ 16፤21፣ ማቴ 28፤5-6

፲፱. እንደሚያርግ መዝ 68፤18 ፍጻሜው ሉቃ24፤50-51 ይህ ሁሉ ጥቅሶች የሚያሳዩን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያት የተናገሩለት ያድናቸው ዘንድ ይጠባበቁት የነበረው አዳኝ እርሱ መሆኑን ነው።

ወገኖች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱም የዓለም መድሃኒት ሆኖ እንደሚገለጥ በነበያቱ ያስተማረ ቢሆንም ለማገናዘቢያ ይሆነን ዘንድ ይህ በቂያችን ነው!!

በሚቀጥለው ደግሞ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ፈቅዶ ቢያገኛኘን ቀጥሎ ባለው ርዕስ እንማማራለን።

"ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ሰው መሆን አስፈለገው?"

                    ይቀጥላል.
ወዳጄ ሆይ

"ክፉ ሐሳብ ሲዋጋህ ያንን ለመርሳት አትታገል ፤ ሐሳብ የሚሸነፈው በሐሳብ ነውና ስለ እግዚአብሔር ማሰብ ጀምር ፤ መጻሐፍትንም አንብብ ። ያዘዝከውን ሰዎች ባይፈጽሙ አቅም አንሷቸው ሊሆን ይችላልና ራስህ ፈጽመው ወይም ለሚሠራ ለሌላ ሰው ስጠው ። መንደሮች የሚያስቡት በመንደራቸው መጠን ነውና ከመንደር ይልቅ ልብህን አስፋው ። አቅምህ እንጂ እምነትህ አናሳ አይሁን ። ኑሮህ እንጂ ፍቅርህ ድሀ አይሁን ። በእጅህ የወደቀ ምርኮኛህ ነውና አቅም አለኝ ብለህ ምንም አታድርግበት ። ተቀምጠህ የምታየውና ቆመህ የምታየው ልዩነት አለው ። ስትቀመጥ ትልቅ የመሰለህ ስትነሣ ትንሽ ነው ። አንድ እርምጃ መራመድም ወደ ግቡ መቃረብ ነው ። እውነተኛ አጥር የሰው ፍቅር ነውና ከአጥር ይልቅ ፍቅርን ገንባ ።"

"መካሪ ከተገኘም ሕይወት ቀላል ነው።"
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ  በዓል  እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል  በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የአብርሐምን ቤት የባረኩ ሥላሴ እኛንም በህይወታችን በኑሮዋጭን በአገልግሎታችን  በትዳርአችን በትምርታችን በሥራችን ይባርኩን ።

ሥሉስ ቅዱስ ለሚታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::

#መልካም እለተ  ይሁንልን

     #መልካም ቀን

 
🌺 ሶበሰ ይወረዱ 🌺


/ ሶበሰ ይውረዱ መላእክት
መላእክት ይወርዱ
አወ ሊቃነ መላእክት ይበል ኧኸ / 2 / /

/ አልቦሙ ድምጽ ኧኸ ኧኸ ኧኸ
ወአልቦ አሰረ ለምክያዳት
ይቀልል ሩፀቶሞ እም ነፋሳት
ውስተ አገሮ ለእግዚአብሄር
ኢትዮጵያ ይበል ኧኸ /3/ /

/ ሶበሰ ይውረዱ መላእክት
መላእክት ይወርዱ
አወ ሊቃነ መላእክት ይበል ኧኸ / 2 / /
Forwarded from 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#ደጉ እና ሩሩህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ በዓል እንኳን አደረሳቹ።

"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ"

እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ

የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"

#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል

" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።"

#መዝሙረ ዳዊት 34:7፤)

"በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል። "

#ትንቢተ ዳንኤል 12:1

" የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት። "

   #ትንቢተ ዳንኤል 10:13

" ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።
"
#ትንቢተ ዳንኤል 10:21፤)ዐ

"የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።"

#የይሁዳ መልእክት 1:9

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
2024/09/28 21:37:34
Back to Top
HTML Embed Code: