Telegram Web Link
የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል

ታምረኛው ፡ እጅግ ጥንታዊ ፡ ታሪካዊና እድሜ ጠገብ ቅርሶች ባለቤት የሆነውን በ12ኛው መቶ ክፈለ-ዘመን የተመሰረተው የትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል " የደቡብ ቁልቢ " ከብዙው በጥቂቱ እናስተዋውቆ !!

እዣ ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮአዊ እና ባህላዊ ለቱሪስት ቀልብ የሚስቡ መስህቦች መገኛ ከሆኑት አካባቢዎች ውስጥ በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ስትሆን እጅግ ማራኪና የአየር ንብረ ለውጥ ለመከላከል የሚያስችሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ደኖች ፡ ውብና ማራኪ ፏፏቴዎች ፡ ትክል ድንጋዮች ፡ ጥንታዊና በውስጣቸው እድሜ ጠገብ ቅርሶችን የያዙ ገዳማት ፡ እና ካቴድሪያሎች ተጠቃሾች ናቸው ።

ከነዚህም መካከል እጅግ ታሪካዊ ፡ ጥንታዊና የሀገር ውስጥና የውጭ የጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ ያለው የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል "የደቡብ ቁልቢ " ከብዙው በጥቂቱ እናስተዋውቆ ።

የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ገደብ ቀበሌ የገረሙጀ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከዞናችን ዋና ከተማ ወልቂጤ በ52 ኪ ሜ እና የእዣ ወረዳ ዋና ከተማ ከሆነችው አገና በ10 ኪሜ ርቀት በስተ-ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ነው።

ካቴድሪያሉ በ12ኛው መቶ ክፈለ-ዘመን በስደት ከአክሱም ፂዮን "ወሰናይ " ተብለው ይጠሩ በነበሩት አባት ከብዙ በጉዞአቸው ላይ ከነበረው ከድቅና ብዙ ታዓምር በኋላ ይዘው በማምጣት እንደሰየሙት በጉራጌ ሀገረ-ስብከት የእዣ ወረዳ ቤተ-ክህነት ስራስኪያጅ እና የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ ብርሃን ብስራት አካለ ወልድ ይናገራሉ ።

በየ ዓመቱ ጥር 18 በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በመሳተፍ በድምቀት የሚከበረው ካቴድሪያሉ በአባታችን በአቡነ መልከ-ፄዲቅ ከተለያየ ቦታ በመምጣት እጅግ ቁጥር ያላቸው እንግዶች በክብረ -በዓሉ መገኘትና የተሳሉትን ስለት ቶሎ የሚሰማ መሆኑን ብዙዎቹ በመመስከራቸው ምክንያት " የደቡብ ቁልቢ " የሚል ስያሜ እንደሰጡትም የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ብርሀን ብስራት አካለወልድ ያስረዳሉ ።

በካቴድሪያሉ ከነሀስና ብር የተሰሩ ጥንታዊ መስቀሎች ፡ ፅዋዎች ፡ የተለያዩና እድሜ ጠገብ የብራና መፅሀፎች ፡ የጥበቃ መሳሪያዎችና በርካታ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በቀድሞ ሀገርመሪ በነበሩ እንደ አፄ ሚኒሊክ ፡ ደጅ አዝማች ፡ ደጅ አዝማች ባልቻ ፡ ደጅ አዝማች ሀብተ -ጊዮርጊስ የተበረከቱ ቅርሶች በካቴድሪያሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተሰራው ዘመናዊ ሙዚየም ውስጥ መመልከት ወይም መጎብኘት ይቻላል ።

ካቴድሪያሉ ከሀይማኖት ስርዓት በተጨማሪ ከእምነቱ ተከታዮች ውጪ ያሉትም ጨምሮ በተለያየ ማህበራዊ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በደንና አካባቢ ጥበቃ ስራ አሻራ እያኖረ ያለና ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ 22 ወገኖች በቋሚነትም ይረዳል ።

በየዓመቱ ጥር 18 እጅግ በአስደናቂ ሁኔታ የሚከበረው የአትፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል በወረዳው የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር በማድረግና የገቢ አቅም በማሳደግ ረገድ የራሱ ድርሻ እንዳለውም የሚታመን ነው ።

ይህን ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮዓዊ እና የበርካታ ቅርስ ባለቤት የሆነውን ካቴድሪያል እንድትጎበኙ እንጋብዛለን ።
#ወዳጆቼ___?

#ኃጢአት መሥራት በራሱ  አስቀያሚ ነው፤ ኃጢአት ከሠሩ በኋላ በዚያ ኃጢአት መታበይ ግን እጅግ #ጽኑ_ደዌ ነው፡፡ #ጽድቅን ሠርተው በዚያ በሠሩት ጽድቅ #ከተኩራሩበት ጽድቁን ያጡታል፡፡ ይህ በኃጢአት ሲኾን ደግሞ የባሰ ነው፤ ወደ ከፋ ጥፋት ይወስደናልና፡፡ ከሠራነው #ኃጢአት ይልቅ በሠራነው ኃጢአት መታበይ የሚያመጣው ፍዳ ኵነኔ እጅግ #ጽኑ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

       
#መልካም__ቀን🙏
#ተክለሃይማኖት_ሆይ፤ ከላይ ከሰማይ ለወረደው እግዚአብሔር አምላክ #ስግደትን #ለአዘወተሩ
አብራኮችህ ሰላም እላለሁ።
#ቅዱስ_አባት_ሆይ፤ በኔ ላይ የተጫነውን ከባድ ሸክም አቅልልኝ፤ ከትእዛዞችህ አንዱን ስንኳ ጠብቅ ባልገኝም አንተ ግን እንደ አባትነትህ ይቅርታ አድርገህ #ልጄ_ልጄ በለኝ።

#መልክአ_ተክለ_ሃይማኖት

      
#_መልካም_ቀን🙏
፨ቅዱስ መርቆሬዎስ ሊቀ ሰማዕታት
ለምስራች ወንጌል ታስሮ በሠንሠለት
በምግባር በጸሎት ጸንቶ በሃይማኖት
ጌታዬ እና አምላኬ ኢየሱስ ነው ብሎ
መከራውን ንቆ ጸና በተጋድሎ።

ዛሬም እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በገባለት ቃል ኪዳን በራዕይ በሕልም ሳይሆን በግልጽ ተገልጾ የሚራዳ በስዕሉ ፊት ያለቀሱትን ቤተክርስቲያን ታደጋት ብለው የተማጸኑትን የአባ ጎርጎርዮስን የአባ ባስልዮስን እንባ ያበሰ አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታገሰ ኃያል ሰማዕት ገባሬ ተአምር። ቅዱስ መርቆሬዎስ ሆይ በጸሎትህና በምልጃህ እርዳን!

ረድኤት በረከቱን ያሳድርብን ምልጃ ጸሎቱ ተራዳኢነቱ አይለየን አሜን።
Audio
#የብርሃን_እናት_ነሽና

የብርሃን እናት ነሽና የብርሃን እናት(፪)
ለምኚልን ድንግል ለምኚልን(፪)

ጸጋንና ክብርን የተመላሽ
ከሴቶች መካከል የተመረጥሽ
ለቃሉ ማደሪያ ዙፋን ሆነሽ
በደመና መንበር የተመሰልሽ
አዝ= = = = =
የሽቶ ማኖሪያ የተቀደስሽ
መዓዛሽ ያማረ ሽቶ ያለሽ
ውዳሴሽ ብዙ ነው እናታችን
ስምሽን እያሰብን ነው መጽናኛችን
አዝ= = = = =
በሀሳብ በግብር ፍጹም ሆነሽ
ምንኛ ብሩህ ነው ድንግል ልብሽ
አንቺን የሚመስል የለምና
ይሰማል ምልጃሽ ያንቺ ልመና
አዝ= = = = =
የብርሃን መውጫ ምሥራቁ ነሽ
ሰውን ለለወጠ ድልድይ ነሽ
ምሥጋናሽ አያልቅም ለዘላለም
ማህሌት ነሽና በአርያም
አዝ= = = = =
መላዕክት ፍጥረትሽን ያደንቃሉ
ጌታን በመውለድሽ ይመካሉ
ሰማይና ምድር ሳይወስኑት
ባንቺ ተወሰነ እፁብ በእውነት
#እሑድ_ማለት "አሐደ"  ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

#ዮሐንስም_በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት (ራዕይ 1፥10) ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ #ዕለተ_እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ #እሑድ ናት።

    
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት 🙏
Audio
"አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል "

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል
ፍቅርህ ይማርካል
በመስቀል ተሰቅለህ መድኃኒት ሆነሃል
አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል
…………
ሳታቆስል በፍቅርህ ማረከን
ከፊት ቀድመህ በድል አስከተልከን
በደለኞች እኛ ሆነን ሳለ
አንተ ከፍለህ ክሳችን ተጣለ

* ኪርያላይሶን* /4x/
አዝ…………

እንደሰማን እንዲሁ አይተናል
ማዳንህን ቀምሰን መስክረናል
የእግዚአብሔር በግ ቆስለህ የፈወስከን
ወደ ድንቁ ብርሃን አሻገርከን

* ኪርያላይሶን* /4x/
አዝ……………

አጽናንተኸን ሞትን አስተከዝከው
ወደ ጥልቁ እንዲወርድ አዘዝከው
ባንተ ፍቅር ምርኮ በዝቶልናል
ማማ ሆነህ ከፍ ከፍ ብለናል

* ኪርያላይሶን* /4x/
አዝ………………

ስንሸሽህ እየተከተልከን
ልጆች አድርገህ በክብር አስጌጥከን
ተቅበዝባዡን ሰብሰበሃልና
ከማደሪያህ ይፈልቃል ምስጋና

*ኪርያላይሶን* /4x/
አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል
ፍቅርህ ይማርካል
በመስቀል ተሰቅለህ መድኃኒት ሆነሃል
አማኑኤል ፍቅርህ ይማርካል
……………………………………
…………………………………

መልካም ቀን ይሁንላችሁ
አማኑኤል ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ
ምክረ አበው ዘአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

=> ኃጢአት ከበጎ ነገር በተቃራኒ መስራት ብቻ አይደለም። በጎውን አውቆ አለመስራትም ኃጢአት ነው።

=> ኃጢአት ምን እንደሆነና ፍፃሜውንም ብታውቅ ትሸሸዋለህ!

=> በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፦ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።

መልካም ቀን
አንዳንድ ነጥቦች በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ መከልከል ዙሪያ፦
1. ለዚህ አሳዛኝ ድርጊት የተቀነባበረ ሽፋን በቅርብ ሲሰጥ እንደምንሰማ የታወቀ ነው። በመንግሥት አካላት ተደርሶ የሚቀርበው ድራማና ዶክመንተሪ አያልቅምና ያልሠሩትን ወንጀል ሲያሸክሟቸውና ሲያጥላሉዋቸው እንሰማ ይሆናል። ስለዚህም ከሚዲያ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልሳን የሆኑ ሚዲያዎችን ብቻ እንከታተል።
2. መንግሥት ይህን መሰል አንገት ሰባሪና ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ሲፈፅምም ብፁዕነታቸው ያሉበትን ኃላፊነት ከግምት አላስገባም። ክብራቸውን የሚወክሉትን ቤተ ክርስቲያንና ሕዝባቸውን አላከበረም። በዚህ ጸያፍ ድርጊቱ እርሳቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝን እንዳሳዘነ መታወቅ አለበት።
3. ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሸክም ጎንበስ ብለው የሚሸከሙ አባት ናቸው። የዛሬው የመንግስት ድርጊት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ከሜዳው በማግለል የቅዱስ ሲኖዶስን ማዕከላዊነት የመናድ ሙከራ ነው።
4. ብፁዕነታቸው በእምነታቸው የማይደራደሩ ታላቅ አባት ሲሆኑ እርሳቸውን ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የማድረግ ርምጃ የቤተ ክርስቲያንን በር የበግ ለምድ ለለበሱ ተኩላዎችና ለእንደ ልቡዎች ክፍት የማድረግ ዕቅድ አካል ነው። ከዚያም ውጪ ሌሎች ውጪ የሚኖሩ አበው ብፁዓን አባቶችንም አፍ የማስያዣ አካሄድ ነው።
5. በሌላ በኩል በውጪ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቁጣቸውን ማሳደር አለባቸው። ምክንያቱም መንግሥትም ሆነ ሕገ ወጥ አካላት በተለያዩ ሚዲያዎች በኩል ይህን ነገር እያራገቡ ጫና ፈጥረው ሌላ ሲኖዶስ እናቋቁም የሚል ሀሳብ እንዲፈጠር መሥራታቸው አይቀርምና በዚህ በኩል ረጋ ብሎ  መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ተተኪ ጸሐፊ ይመረጥ የሚል ሤራ እንዳይሸርብም ነቅቶ መጠበቅና መሥመር ማስያዝ እንደሚገባው ሳይረሳ!!
6. ይህ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የታሰበ እቅድ ነው። ስለዚህም እንደ ምእመን በበለጠ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ማተኮርና ቤተ ክርስቲያናችንን በንቃት መጠበቅ አለብን።
7. ይሄ ጉዳይ መሥመር እንዲይዝ የሚያደርጉ አባቶችን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ማገዝና ትዕዛዛቸውንም እንደ ልጅ መፈጸምም ይገባናል።
ልዑል እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

#ኢንፈርህሞተ
#ሞትንአንፈራውም
ብርሃኑ ተ/ያሬድ
2024/11/15 18:36:30
Back to Top
HTML Embed Code: