Telegram Web Link
🔶እየተጠራሁ ነው❗️
                ♻️ እውነተኛ ታሪክ!
አቶ በጋሻው እና ወይዘሮ ሽቶ ትዳር መስርተው አንድ የ10 አመት ልጅ ወልደው በፍቅር እየኖሩ ሳለ በአንዲት ባልታደለች ቀን ወይዘሮ ሽቶ በመንገድ ላይ ለጉዳይዋ ስትሄድ ፍሬን የበጠሰ መኪና ገጭቶ አለፋት። በአቅራቢያው ወደ ሚገኘው ክሊኒክ ቢወስዷትም በቶሎ ይህችን አለም ተሰናበትች። አቶ በጋሻው እና ልጃቸው ብርሃኑ ብቻቸውን ለአራት ዓመት ኖሩ። ከዚህ በኋላ አቶ በጋሻው ብቸኝነቱ ከብዶት ሌላ ሚስት አገባ።ልጅም ወለዱ ብርሃኑ ግን ሁለተኛ እናቱ ከመጣች እና ቤተሰቡን ከተቀላቀለች ቀን ጀምሮ ሃሳብ ገባው። ይህች ሁለተኛ እናቱ ብርሃኑን ትጨቁነዋለች እና አይወዳትም።
ያለ ምንም ጥፋቱ ቀኑን ሙሉ ፆሙን እንዲውል ስታደርገው ወደ ጓደኞቹ አቅንቶ ያገኘውን በልቶ ይውላል።
ሁሉ ጊዜ ብርሃኑን ያለ በደሉ ለአባቱ በጋሻው ትከሰዋለች። አባቱም ሚስቱን ያምናታል እና ብርሃኑን በርበሬ ያጥነዋል ሲገረፍም ያድራል።
ብርሃኑ አሁን ሁሉም ነገር ፊቱን ስለ አዞረበት ከቤቱ እንደ ምንም ብሎ የገብስ ዱቄት ይሰርቅ እና ጎረቤት አስቀምጦ ቂጣ እየጋገረ በውሃ እያማገ ይበላል።
የዚህ አይነት ግፍ እየደረሰበት በእንጀራ እናቱ ተጨቁኖ ህይወቱን እያኖረ የሚገኘው ብርሃኑ ጎደኞቹ ከፍለውለት በቤተክርስቲያን የሚዘጋጀውን የጉዞ መርሐ ግብር ሊካፈል ተዘጋጀ።ጉዞው ወደ ሸንኮራ ዮሐንስ ሲሆን በእለቱ ጠዋት ከቤቱ ሲወጣ ምንም ምግብ እንዳልበላ ያወቁት ጎረቤቶቹ ቁርስ በልተህ ትሄዳለህ ቢሉት ''አይይ እኔ እየተጠራሁ ነው'' ቶሎ መሄድ አለብኝ ብሎ ምንም ሳይበላ የጉዞውን መኪና ተሳፈረ። እየዘመሩ ከተጓዙ ከሰአታት በኋላ የጉዞው መድረሻ ቦታም  ደረሱ። ከዚህ በኋላ ነበረ ከሁለት ጓደኞቹ ጋራ ፀበሉ ወደ ሚገኝበት ቦታ ሲያቀና የቀሩት ጓደኞቹ ፀበል ይዘህልን ተመለስ ብለው ሃይላንድ ቢሰጡት ''እኔ አልመለስም እና አልቀበላችሁም'' ብሎ መለሰላቸው። ከዚያም ወደ ፀበሉ አቀና። በቦታው ደርሰው መታጠብ ጀመሩ ድንገት ግን ያልታሰበው ነገር ደረሠ። ብርሃኑ እየታጠበ ሳለ የቆመበት ቦታ አዳለጠው እና ወደ ውንዙ ገባ።አብረውት የነበሩት ጓደኞቹም ጮኹ ሁሉም ተሰባሰቡ ብርሀኑን ግን ሊያድኑት አልቻሉም ላይመለስ ተጠርቷል እና በዚያው ዳግም ወደ ማይመለስበት ከተማ ተጓዘ።
አስክሬኑም ሲፈለግ ቆይቶ በሁለተኛው ቀን ተገኘ። እነዚያ ሲዘምሩ የሄዱት ዛሬ ግን ተክዘው እና በነፍስ የተጓዘው የብርሃኑን አስክሬን ይዘው ወደ ሃገራቸው ተመለሱ።
ሃዘኑ በረታ ትካዜው በሁሉም ልብ ውስጥ ገብቶ የሁሉንም ልብ ሰበረው። ያቺ የምትጠላው እና ልታየው የማትፈልገው እንጀራ እናቱ ዛሬ ላይ በብርሃኑ ስትፈፅም የነበረውን ግፍ እያሰበች ትፀፀታለች።
የአካባቢው ሰዎች እና ጎረቤቶች ደግሞ የብርሃኑን ጭንቀት ስለሚያውቁ በቁጭት ወይኔ ያኔ እኔጋ አስጠግቼው ባሳደኩት የሚሉ እና የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው።ብርሃኑ ግን ይህንን ሳያይ ሄዷል።

🌟ሰዎችን መርዳት ካለብን በጊዜው እንርዳቸው ጊዜው ካለፈ ትርፉ ዋይታ እና ቁጭት ብቻ ነው።

    
        🌟💫ከኪነ-ጥበብ🌟💫
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ናዛዚትነ እምኀዘን
ወኃይለ ውርዙትነ እምርእሳን
በማኅፀንኪ ተፀውረ ብልየ ሞዋእል ሕፃን
ኦ ማርያም ተስፋ ለቅቡጻን 
በግዜ ጸሎት ወዕጣን
ወበግዜ ቅዱስ ቁርባን
ለናዝዞትነ ንኢ ሐበ ዝ መካን

ልጆች የእግዚአብሔር ጸጋ ናቸው ልጆቻቹ እግዚአብሔር በጥበብ ያሳድግላቹ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቤቴል ሚካኤል እንኳን አደረሳቹ ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብር በዓል አደረሳቹ
MK TV || ጠበል ጸዲቅ || የአህያ ሥጋ ብበላ ምን ችግር አለው?
Mahibere Kidusan
*🫏የአህያ ሥጋ ብበላ ምን ችግር አለው?*

🎥መምህር ኃይለማርያም

*ወደ አፍ እሚገባ እንዴት ያረክሳልጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ?*


4 *ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።*


*ማኅበረ ቅዱሳን ጠበል ጸዲቅ መርሃ ግብር*👆🏼🦻🏼👆🏼
2024/09/29 09:31:45
Back to Top
HTML Embed Code: