Telegram Web Link
የማይሸረሸር አለቴ
የማይናጋ መሰረቴ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሞገሴ
አንተህ ነህ የጽድቅ ልብሴ

ቀራንዮ ላይ የቆመ
በፍቅር የተተለመ
ከፊቴ ተነሰነሰ
ደምህ ሕይወቴን ወረስ

እፎይ ልበል ልዘምር
ሁነኸኛል ጌታ ክብር

የሲና ምድር ኅብስቴ
የተከተልከኝ አለቴ
መርገሜን ሰብሮ አለፈ
ሰላምህ ውስጤ ጎረፈ

የማትደፈር ክልሌ
የድል አርማዬ አክሊሌ
ዓለምን ማሸነፊያዬ
አንተ ነህ ክንዴ ጌታዬ

ማዳፎችህን አይቼ
በዕንባ ረጠቡ ጉንጮቼ
ትዝታዬ ነው ዘወትር
መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር

ዘማሪ ገብረ ዮሐንስ

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
ኢትዮጵያ እጅሽን ዘርጊ

ኢትዮጵያ እጅሽን ዘርጊ
ወደ አምላክ ወደ አዶናይ
ህዝብሽን ከሞት የሚያድን
ይዉጣልሽ የምህረት ፀሐይ


ህጻናት ወላጆች አጥተው በሜዳ ሲበታተኑ
ንስሮችሽ ወጣቶች አልቀው የአፈር ሲሳይ ሲሆኑ
የሞት መልአክ ተልኮብሽ መሬትሽ አጥታ ጸጥታ
ቁጣዉን እንዲመልሰው ለምኚ ለሰማይ ጌታ

አዝ__

ታማሚው እያጣጣረ ጤነኛው ቆሞ ሲፈራ
አምላክሽ ይቅር ይበልሽ ይለፍሽ ይሄ መከራ
አበዉን ይዘሽ ተነሺ ጸሎትሽን ቆመሽ አድርሺ
ያብርደው እሳት ንዳዱን በምልጃሽ በልመናሽ

አዝ____

ጆችሽ ቅጣት ገብቷቸው እንዲያዩ ወደ አምላካቸው
መከራው ትምህርት ሆኗቸው ይመለስ ታካች ልባቸው
የበደልነውን ታግሶ ቁጣውን እርሱ መልሶ
ይማረን ይቅር ይበለን ጽኑ ምህረቱን አስታውሶ

አዝ_

ህዛብ ተነጋገሩ አምላክሽ እረሳሽ ብለው
ልጆችሽ ሞት ሲፈጃቸው እያዩ እጅግ ተገርመው
ጉልበትሽ እንዳይሰበር ምርኩዝሽ እርሱ ነውና
ደዌ ቸነፈሩን ያርቅ አቅርቢ ፅኑ ልመና

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
Audio
አቡነ አረጋዊ ጻድቁ መነኩሴ
በኃጢአት አንዳትሞት ሕያዊቷ ነፍሴ
ጻድቁ አማልደኝ በቅድመ ሥላሴ(፪)

ከእናት ከአባት ፍቅር - - አቡነ አረጋዊ
አምላክን መርጠሀል - - አቡነ አረጋዊ
መከራ መስቀልን በእውነት ታግሰሀል
የእግዚአብሔር ቸርነት ከሞት ሰውሮሃል
አዝ= = = = =
ምስጢረ መለኮት - - አቡነ አረጋዊ
በልብ ቢመላ - - አቡነ አረጋዊ
አረጋዊ ተባልክ ሣለህ ታናሽ ጨቅላ
ጸጋህ ትደርብን ትሁንልን ጥላ
አዝ= = = = =
ከዳሞት ተራራ - - አቡነ አረጋዊ
ከማህሌት ከተማ - - አቡነ አረጋዊ
በጽዮን ዝማሬ ነፍስህ ብትጠማ
በዘንዶ ተጉዘህ ሰማህ ያንን ዜማ
አዝ= = = = =
የህግ መምህር - - አቡነ አረጋዊ
በረከት አድለን - - አቡነ አረጋዊ
ከድካም ወደ ኃይል በእምነት አሻግረን
ወደ ጌታ ደስታ በምልጃህ አቅርበን

https://www.tg-me.com/Egizhaberanidinew
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲናያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ጽሁፎች ቻናል⛪️
Photo
++  አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ! ++ (መዝ 91:13)

☞ ሞተ ሥጋ ሳያገኛቸው እግዚአብሔር የሠወራቸው ብዙ ቅዱሳን አሉ። ከነዚህም መካከል ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ አንዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱሱ ሰው ሄኖክ ሞት ሳያገኘው የተሰወረበትን ምክንያት ሲገልጽ “ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።” ይላል  አካሄድን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ እስከምን እንደሚያደርስ ተመልከት። (ዘፍ 5፥24) አካሄዳቸውን ከእርሱ ጋር ባደረጉ ወዳጆቹ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ቸርነትና ከኃሊነት ተገልጦአልና ነቢዩ “እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ።” በማለት ተናገረ።  (መዝ 4፥3) በቅዱስ ሰው ሃይማኖት፣ በጎ ምግባርና መልካምነት ኢየሱስ ክርስቶስ ይገለጣል እንጂ አይሸፈንም።

☞ ከቅዱሱ ሰው ከሄኖክ ሌላ ቀናተኛው ነቢዩ ኤልያስም ሞት ሳያገኘው በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ተነጥቆዋል። ይህንም መጽሐፍ ሲነግረን “ሲሄዱም፦ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥  እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።” ከነቢዩ ጋር የነበረ ይህን የተመለከተና ለእግዚአብሔር የተገዛ ኤልሳዕም የነቢዩ ኤልያስ በረከት አድሮበት ተመሷል።  (2ኛ ነገ 2፥11) መጽሐፍ በቅድስናቸው ለዚህ የበቁ እንዳሉ ሲነግርህ ዕፁብ ድንቅ ብለህ ማመን ማሰብም አንተንም ለክብር ያበቃሃል። ክርስቶስን በእነርሱ ሕይወት ትመለከተዋለህ እንጂ አይሠወርብህም። እንዲያም ባይሆን “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።” ባላለህም ነበር። (ዕብ 13፥7)

           ☞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከደቀመዛሙርቱ መካከል ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የሥጋ ሞት እንደማያገኘው ደጋግሞ ፍንጭ ሰጥቶ ነበር። በዚህም ቃሉ መሠረት ወንጌላዊው እንደተሠወረ የቤተክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል። (ማቴ 16:28፣ ዮሐ 21:23) 

☞በዚህ መልኩ የተሠወሩ ቅዱሳን እነዚህ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም። እግዚአብሔር የዘመናት ባለቤት ነውና በየዘመኑ እንዲህ አይነቱን የቸርነቱን ሥራ የሚሠራላቸው የሠራላቸውም ብዙ ወዳጆቹ አሉ። ከእነዚህም ወዳጆቹ በመለካውያን ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ ምድር መጥተው የነበሩት ጻድቁ አቡነ አረጋዊ አንዱ ናቸው። እንደ ሄኖክ አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር አድርገዋልና እግዚአብሔር ከሞተ ሥጋ ሰውሮ ወስዷቸዋል። ጻድቁ አቡነ አረጋዊ አምላካችን እግዚአብሔር  "በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።" በማለት አስቀድሞ የተናገረው ቃል እንዲሁም በኋለኛው ዘመን ጌታችን “ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤....... እባቦችን ይይዛሉ፥”  ብሎ የተናገረው ቃል በተግባር የተፈጸመባቸውና የተፈጸመላቸው ጻድቅ ናቸው። (ማር16፥17፣ መዝ 90:13) ልዑል አምላክ ክርስቶስ ከወዳጆቹ የምንደመርበትን መልካም ሥራ ለመሥራት ያብቃን!!

ቢትወደድ ወርቁ
ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ ም     
2024/11/19 20:39:39
Back to Top
HTML Embed Code: