Telegram Web Link
ጉራጌ ክልል እዣ ወርዳ አገና ከተማ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የጷጉሜን 6 ቀናት ጸሎተ ምህላ እንዲኖር አወጀ።

ዛሬ ነሐሴ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በአቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በተሰጠው መግለጫ መሰረት የጷጉሜን ወር 6 ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምህላ እንዲያሳልፍ መታወጁን ነው የገለጹት።

በመግለጫውም ዘመኑ ከደስታ እና የምስራች ይልቅ ሀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾም እና በጸሎት እንዲያሳልፉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ 13ተኛ ወር በሆነችው ወርሐ ጷጉሜ እለተ ምጽዓትን የምናስብበት ፤ ሠማይ የሚከፈትበት ፤ ጸሎት የሚሰማበት ሚስጥራዊ የሆነች ወር ነችና የበደሉንን ይቅር ብለን በንጹሕ ልቦና የቻልን ጾመን ያልቻልን በጸሎት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት እና የምንለምንበት ወር ሊሆን ይገባል ሲሉ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው የቤተ ክርስቲያን በዓላት ሲደርሱ ከሥርዓቷ እና ከአስተምሮዋ ውጪ በ ሆነ መልኩ የተለያዩ አካላት የዳንኪራ ጥሪ በማዘጋጀት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አግባብነት የሌለው መሆኑን እና ምዕመናንም ከዚህ እንቅስቃሴ እራሳቸውን ሊያርቁ ይገባል ነው ያሉት።

የማትደፈረዋን እና የማትነካዋን ቤተክርስቲያን የሚነኩ ሰዎች በዝተዋል ፤ ቀጣዩ ዓመትም ኢትዮጵያውያን በሰላም በፍቅር የምንኖርበት የሚራቡ የሚፈናቀሉ የሚያዝኑ ሰዎች እንዳይኖሩ ሁሉም ምዕመን ጠዋት ኪዳን ከሰዓት በሠርክ ጸሎት በየአብያተ ክርስቲያን በመሄድ ያልቻለም በየቤቱ ሊጸልይ ይገባል ብለዋል።

© ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
#ወዳጆቼ?????

#እግዚአብሔር_የሚወዳችሁ_እናንተም_የምትወዱት_ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን #ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ #እግብሔርን አመስግኑት፡፡

ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና #እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን #በጐ_ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ #ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም #የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼               🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
"" ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን።""

🌻የገዳማውያን አበው ጸሎት🌻

የተፋሁትን እንዳያስልሰኝ
ወደጠላሁት እንዳይመልሰኝ የሰይጣን ክንፉን ስበርልኝ።

መስቀል ከባረከው ወንጌል ከሰበከው
አንተን ከሚያመልክ ሰው ጨምረኝ።


ስደት ቢገጥመኝ እንደ ዮሴፍ ከጎኔ ቁምልን።
ጸንቼ ብገኝ ለክብሩ(ለሰማዕትነቱ) ለመንግስቱ አብቃኝ።


አየሁኝ በቃሁኝ ከማለት ከከንቱ ውዳሴ አድነኝ።
አይኔ ተከድና አፌ ተገጥሞ ጉድጓድ እስከምገባ ነፍሴ ወደ አንተ እስከምትመጣ ድረስ በራሴ እንዳለቅስ እንድጸጸት አድርገኝ።

ደህና ደኽናዎቹን እንድመስላቸው
ደካሞቹን እንዳልከተላቸው አድርገኝ።
ደካማ ቢያነሱት ምንግዜም ደካማነውና
ደህናውን  ቢጠሩት ፈጥኖ ይደርሳልና።

አንደበቴን ከሐሜት
ጉልበቴን ከስንፈት
ልቤን ከትዕቢት
እግሬን ከዙረት ጠብቅልኝ።

ደጎቹ አባቶቻችን ወንድሞቻችን እናቶቻችን እህቶቻችን ከደረሱበት አድርሰኝ።
ደካማ ነኝና ሐይል ስጠን
ውዱቅ ነኝና አንሳኝ። አሜን።
   

  
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
2024/09/29 17:39:52
Back to Top
HTML Embed Code: