Telegram Web Link
*ጉባኤ ሐዲስ ኪዳን*

🎙️መምህር ነቅዓጥበብ


*♥️ማትዮስ ወንጌል ክፍል ፩፫*


47 *✝️ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለች ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች፤*

*ክፍል1️⃣8️⃣*

https://youtu.be/jdF2flhnpXI


*ማኅበረ አትናትዮስ መልስ ለአህዛብ እና ለመናፍቅ*👆🏽👆🏽👂🏽👂🏽
ወብዙኃን ይትፌስሑ በልደቱ(በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል) ሉቃ [1÷14]

ጌታችን በወንጌል ሴቶች ከወለዷቸው ልጆች ሁሉ የሚበልጠው እንደሌለለ የመሰከረለት ፣ የመንገድ ጠራጊው  የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የልደት በዓል እንኳን አደረሳችሁ!
Abrham Abere ዘተዋህዶ:
የሚያስጨንቅ ዘመን(መምህር ብርሃኑ አድማስ እንደጻፈው)

ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። /2ኛ ጢሞ 3፤1/
ትዳር ልጆች፣ ቤት መኪና እና ደኅና ሥራ የነበረው አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖር አንድ ክርስቲያን ድንገት በአንድ ምክንያት ትዳሩ ይፈርሳል፣ ልጆቹም ይበተናሉ። ቤትና መኪናውም በእዳ ተይዘው ይሸጡበታል። ብቻውን ቤት ተከራይቶ ኑሮውን መግፋት ቢታገልም የደረሰበትን ተደራራቢ ፈተና መቀበል አቅቶት በሽተኛ ይሆንና እቤት ይውላል። እቤት ሲውል ደግሞ ከሥራውም ተባረረና ምንም ገቢ የሌለው ደሀ ይሆናል። በዚህም የባሰ ጭንቅ ውስጥ ይገባል። አከራዮቹም ረዘም ላለ ጊዜ ቢታገሱትም እነርሱም ኑሯቸው በዚያች ገቢ ጭምር ላይ የተመሠረች ነበርና የማትከፍል ከሆነ ቤቱን ልቀቅልን አሉት። ሁኔታውን የሚያውቁ ሰዎች በሚጥሉለት ቁራሽ ረሀቡን እያስታገሰ በጭንቅ ውስጥ የሚኖረው ይህ ሰው ወደ ጎዳና ወጥቶ የሚወድቅበት ቀን መቃረቡን ሲያስብ ጭንቀቱ በረታበት። በአልጋው ላይ ሆኖ ያለቅሳል። እመቤታችንን በአልጋው ላይ ሆኖ አምርሮ አለቀሰባት ። መንገድ ላይ ሳልወድቅ ልጅሽ እንዲወስደኝ አድርጊ አላት። ባለዕዳ እንደሆንኩም አይጥራኝ። እንኳን የኃጢአት እዳዬን የቤት ኪራይ እዳዬን ሳልከፍል እንዳይጠራኝ ከልጅሽ አማልጅኝ እያለ ምርር ብሎ አለቀሰባት ። እመቤታችንም ወዳጇ የሆኑ አንድ አባትን ይህን ሰው በራእይ አሳየቸቸው እና ሔደህ እዳውን ክፈልለት አለቻቸው። እኒያ አባትም ከተፈቀደላቸው ሰዎች ተቀብለው ሔደው መጀመሪያ የስድስት ወሩን በኋላ ደግሞ ቀሪውን የስድስት ወር ኪራዩን ከፈሉለት እና ድሮ የሚያውቅህ ሰው ከፈለልህ ብልው ለዚያ ተጨናቂ ነገሩት ። በአልጋው ላይ እንዳለ የእዳውን መከፈል ሰምቶ የእፎይታ የሚመስል ድምፅ እንዳሰማ በዚያው ዝም አለ፤ በቃ ዝምምምም እንዳለ ቀረ።

ይህ በዚህ በ2015 ዓ.ም. እንደሆነ የማውቀው እውነተኛ ታሪክ ነው። በእንዲህ ያለ ሁኔታ ብዙ ሰዎች እንደሚጨነቁ ምን ያህል እናውቅ ይሆን? ከዚህ ውጭም አስጨናቂው ነገርም ተጨናቂውም ሰው እጅግ ብዙ ነው። ይህን ታሪክ ያስቀደምሁት እኔን የሚያስጨንቀኝ ነገር ለመናገር ሳስብ ይህን እና የማታውቃቸውን ተጨናቂዎች ረስተህ ራስህን ከባድ ጭንቀት እንደወደበቀት ታመጻድቃለህን የሚል ኅሊና ስለመጣብኝ እንጂ ይህን ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሣሣኝ ግን የራሴ ጭንቀት ነው።

እንደ ዘንድሮ ተጨንቄ አውቅ ይሆን? እንጃ እስካሁን እንዲህ የተቸነቅሁበትን አላስታውስም። እንዴት እንደሚያጥርም አላውቅም። ማሰብ፣ ማቀድ፣ መሥራት፣ ... ይቅርና ነገሮችን ሁሉ ሰምቶ መረዳት እና ማሰላሰል እጅግ አስቸጋሪ ሆኖብኛል። የብዙዎችን ሳስብ ደግሞ ምንአለ ለእኔ ብቻ በሆነም እላለሁ፤ ግን አይደለም የዘንድሮ ጭንቀት የብዙዎች ነው። 

ምናልባት የሚያስጨቀን ነገር ይለያይ እንደሆን እንጂ የማይጨነቅም ላይኖር ይችላል። ርግጥ ነው የሚያስጨንቀንማ ይለያያል። ቀደም  ብዬ እንደገለጽኩት በሀገራችን የዕለት ጉርስ አጥቶ፣ የሚጠጋበት የሚጠለልበት አጥቶ የሚጨነቀው እጅግ ብዙ ነው። በተኛበት ጎጆው ውስጥ ማን መጥቶ ምን ያደርገን ይሆን ብሎ በየዕለቱ በጭንቅ በሰቀቀን የሚያድረውም እጅግ ብዙ ነው። ትንንሽ ቤት ያለው ሳይቀር ይፈረስብኝ ይሆን እያለ ይጨነቃል። የጣራ እና የግድግዳ ለመክፈል አጥቶ ተጨንቆ የሚጣጣረው ብዙ ነው። በኪራይ ቤት እየኖረ የወር ኪራይ መክፈያ ሲደርስ ነፍሱ የምትጨነቀው ብዙ ነው። በሕመም በተለያዩ ማኅበራዊ ምስቅልቅሎች ገቢውን አጥቶ የአከራዩን ፊት እየሸሸ የሚጨነቀውን ቤት ይቁጥረው። ሌላው ቀርቶ በከተማ ያለው ነጋዴም ሳይቀር በግብሩ፣ በጥቆማው በእሥሩ፣ በክስሱ፣ በመሳሰለው ይጨነቃል።

ባለሥልጣናቱም ይጨነቃሉ። ሥልጣናቸውን ላለማጣት እንቅልፍ አጥተው ያድራሉ። የራሳቸውን ለማስጠበቅ ሲሉም ብዙ ንጹሐንንን ሁሉ ያስጨንቃሉ። ካድሬው፣ ነገረ ሰሪው ምን ሪፖርት ላድርግ፣ ምንስ ጥቅም እንዴት ላግኝ፣ ሰው ሳያውቅብኝ እንዴት ልጠቀም እያለ ይጨነቃል። ሆዳሙ ሰካራሙ የነገውን ቁርጥ እና መጠጥ እነማን ይክፈሉ፣ በምን ላስፈራራቸው ብሎ ይጨነቃል። ለጥጋብ የሚሆን ገንዘብ ፍለጋ ይጨነቃል። ቆይቶ ደግሞ ተሰማብኝ፣ ታውቀብኝ፣ ቢይዙኝ ቢያስሩኝ፣ ቢያባርሩኝ ቢቀሙኝ፣ ቢገድሉኝ ቢቀብሩኝ እያለም ይጨነቃል፣ ቢበላና ቢጠግብም፣ ቢጠጣና ቢሰክርም፣ ቢሰበሰብና ምሥጢር ቢነገረውም ይጨነቃል።  ማን የማይጨነቅ አለ?

እነእገሌ ከታርቁ ምን ይወጠኛል፣ ጅምሬ ፣ ትግሌ ይከሽፋል ብሎም የሚጨነቀው ብዙ ነው። ስለዚህም ይመክራል፣ ስትራቴጂ ያወጣል፣ ፕሮፖጋንዳ ይሠራል፣ ያጣላል፣ ያለያያል፣ ገንዘብ ያወጣል፣ ይሸነግላል፣ ሐሰተኛ ዜና ያሠራጫል፣ ሥጋቴ ናቸው ያላቸውን ይፈርጃል፣ ሠርጎ ገቦችን ያመቻቻል፣ ... ተጨንቆ ያስጨንቃል። እንዲህ እንዲህ ሆኖ ዘመኑ ባጠቃላይ አስጨናቂ ዘመን ሆነ።

እኔን ፣ መሰሎቼን እና ቤተ ክርስቲያናችንም እንዲህ ያሉት ተጨናቂዎች አስጨነቁን። በእውነት አስጨነቁን። ይህን ለመናገር እና ለመጻፍ እንኳ ምን ያህል ተጨነቅሁኝ። በእውነት  አስጨናቂ ዘመን።

ሰሞኑን እየሆነ ባለው ብዙ ተጨነቅን። ፈተኞቻችን ቤታችንን አጣብቂኝ ውስጥ አስገቡት። የዋሐን አማኞች ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚወድዱ ቅን አገልጋዮች ፈሩ ተጨነቁ። አንዳንዶች የሚመስላቸውን ተናገሩ። ግምቶቻቸንን እና መረጃዎች ናቸው የምንላቸውን ይዘን ተወዛገብን። እንድንወዛገብ የሚሠራ አለ፣ እንድነጠላላ የሚሠራ አለ፣ እንድንከፋፈል እንዳንደማመጥ እንዳንተማመን የሚሠራ አለ። ሌላው ቀርቶ ምንስማማ ሲመስለው እንኳ  እጅግ ይጨነቃል። የነቃን ስንመስለው ይጨነቃል። ስትራቴጂው ሲጓደልበት ይጨነቃል። ስለዚህም አዳዲስ ስልት ያወጣል። ገንዘቡን ይበጅታል። መረጃውን ይተነትናል። በአካባቢ ያቧድናል። ይገፋፋል፣ ያጠላላል። ለዘላቂ ጥቅሙ ብሎ ብዙ ጉልበት ያፈሣል።  ለችኩሎች የሚሆነውንም ሳይቀር ያዘጋጃል። የሚደብቀው እንዳለው ሁሉ ሥራዬ ብሎ ለራሱ በሚጠቅመው መንገድ መረጃ ያለውን አሾልኮ ያስነግራል። እንቅልፍ የለውም ይደክማል፣ ያደክማል፣ ይጨነቃል፣ ይጨነቃል፣ ያስጨንቃል። በእውነት አስጨናቂ ዘመን።

የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሒደት ብዙ አስጨነቀን። አንዳንዶቹ አጋጣሚውን ተጠቅመው ለመሾም ብዙ ተጨነቁ። ኦሮሞዎች ይሾሙ ሲባል አፌን በኦሮምኛ ነው የፈታሁና እና ኦሮሞ ነኝ ብለው ለማሳመን አንዳንዶቹ ብዙ ተጨነቁ። አንዳንዶቹ ኦሮሞ ያልሆነ እንዳይገባብን ብለው ተጨነቁ። አንዳንዶች በዚህ አመካኝተው ገንዘብ ለመሰብሰብ ተጨነቁ። አንዳንዶቹ ደግሞ በዚህ ሁሉ መካከል ደኅና ደኅና አባቶችን ለማቅረብ ተጨነቁ። አንዳንዶች መብት የሚሉትን ለማስጠብቅ ወይም በእርሱ ስም ለመነገድ እና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ብዙ ተጨነቁ። ሌሎችም ቀኖና ለማስጠብቅ ተጨነቁ። አንዳንዶች የተራራቁ ፍላጎቶችን ለማስማማት እና አንድነት ለማጽናት ብዙ ተጨነቁ። በቅንነት የሰሩበትን ለማስረዳትም ደከሙ። ነገር ግን ከስንዴ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ እንደተባለው አብረው ተወቀጡ። በቅርበት እናውቃለን የሚሉም ነገሩን ለማስረዳት ተጨነቁ። ሌሎች ደግሞ በየአጋጣሚው ልዩነትን አስፈቶ ወደሚፈልጉት ሰፊ የጥቅም ባሕር ለመግባት እንቅልፍ እስኪያጡ ተጨነቁ። ይህን ሁሉ የፈሩ በአጠቃላይ በሹመቱ ተጨነቁ። ሌሎችም ሹመቱ ቢቀር ይመጣል ብለው በፈሩት ተጨነቁ። አንዳንዶች ምእመናን ላለመስማት ብዙ ተጨነቁ። ሌሎችም ለመስማት ተጨነቁ። ሌሎች ደግሞ ሁለቱን አቧድነው ትልቅ ክፍፍል ለመፍጠር ተጨነቁ። ሊሎች ደግሞ ይህን ለማምለጥ እጅግ ተጨነቁ።
ከጋዜጠኞችም አንዳንዶቹ እውነቱን

ለማወቅ ተጨነቁ። አንዳንዶች ደግሞ እውነቱ እንዳይሰማባቸው ተጨነቁ። አንዳንድ  (እንዲል ጋዜጠኛ) የማኅበራዊ ሚዲያ ቀለብተኞችም በዙ ሰው የሚሰማው ጉዳይ ለማዘጋጀት ተጨነቁ። አንዳንዶች ደግሞ ዜና ከፍተው ለመስማት እንኳ ተጨነቁ። በርግጠም አስጨናቂ ዘመን።

አሳቢዎችም አሳባቸውን አንረዳቸው ብለን ተጨነቁ። ስሜት ነግሶ ሲመለክቱ  ተጨነቁ። ስላለፈው እንጂ ሰለወድፊቱ በአግባቡ የሚያስብ የለም እያሉ ተጨነቁ። ኦርቶዶክሱን ወደ አንድነት በስልት የሚመራው ባለመኖሩ ተጨንቁ። ቢናገሩ የሚሰማቸው እንደሌለ አስበው ተጨነቁ። ሌላው ቀርቶ ቤተ ክህነት ሔደው ለማማከር እንዳይፈረጁ ፈርተው ተጨነቁ። መከፋፈሉ ጥሩ ውጤት እያመጣላቸው እንደሆነ አስበው ሌት ተቀን የሚሠሩትም አዋቂዎች ወደዚያ እንዳይጠጉባቸው ተጨነቁ። እውነተኛ አባቶች ምእመኑ ተስፋ እንዳይቆርጥ ተጨነቁ። እውነተኛ ምእመነናም ምን ይመጣብን ይሆን እያሉ ተጨነቁ። ተንኮለኞቹም አባቶችን አንድ የሚያደርግ ምእመኑንና አባቶችን እንደባለፈው በአንድ የሚያስቆም ሁኔታ እንዳይፈጠር ተጨነቁ። የሁኔታውን አደገኛነት የሚታዘቡ ፖለቲከኞችም የሕዝቡ ብሶት ከሚገባው በላይ አልፎ ያልታሰበ ማዕበለ እንዳይመጣ ተጨነቁ። በሌላ አቅጣጭ አንዳንዶቹ ደግሞ ጠንካራ ቤተ ክህነት እንዳይፈጠርም ተጨነቁ። ለሁሉም አስጨናቂ ዘመን።

አሁንም ገና አስጨናቂ ነው። በተግራይ ያለው የአባቶች መለየት እንዳይፈታ ብዙ ሰዎች ብዙ ተጨነቁ። ብዙ ፖለቲከኞች እንቅልፍ አጥተው ተጨናነቁ። ቅዱስ ፓትርያርኩን ከአባቶች ለመለየትም ብዙ ተደከመ። ትግራይ እንዳይሔዱ በዙ ደከሙ። ትግራይ መሔዳቸው ቁርጥ ሲሆን ደግሞ እንዳይገናኙ ደከሙ። ብዙ የዋሕ የየአካባቢያቸው ተቆርቋሪዎችንም አሰልፈው እጅግ  ብዙ ደከሙ። አሁንም እየደከሙ ነው። ሁሉም ፖለቲከኛ ለፖለቲካዊ ጉዳዩ ይበጀኛል ያለውን ሁሉ ለማድረግ ይጨናነቃል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሽታውን ለቤተ ክህነቱ፣ ለቤተ መስጊዱ፣ ለቤተ ፓስተሩ ሳይቀር አጋብቶ ኢትዮጵያን ሰቅዞ አስጨነቃት ። ሁሉም አሁን እንደተወለደ ውሻ ቡችላ አይኑን ጨፍኖ ወደራሱ አፍ የምትገባውን ጡት ብቻ ጠብቆ ይጮሃል እንጂ አብሮት እንደራሱ የተራበውን ጩኸት እንኳ አይሰማም። እንዴት ያለ አስጨናቂ ዘመን።
እኔም ይህን ሁሉ ሳስብ ተጨንቅሁ። ዛሬ የሚሆነውን ለማወቅ ተጨነቅሁ። ነገ ምን ይሆን እያልኩ እጨነቃለሁ። ክፍፍሉ የት ይደርስ ይሆን እያለኩ እጨነቃለሁ። በየግላችን የምንጽፈው፣ የምንናገረው ይጠቅም ይሆን ይጎዳ እያልኩ እጨነቃለሁ። ምንነው ዝም አልክ ሲሉኝም ለማስረዳት እጨነቃለሁ። አንድ ነገር ለማለትም እጨነቃለሁ። ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ካፉ እንዳይሆንብኝ እጨነቃለሁ። ዝም በማለቴም ለለውጥ አስተዋጽዖ ከማድረግ እርቄ ይሆን እያልኩ እጨነቃለሁ። ሰዎችን ለማናገር አስብና ምን ብለው ይተረጉሙት ይሆን ብዬ እጨነቃለሁ። ዝም በማለቴም ምን ይሉ ይሆን ብዬ እጨነቃለሁ። ባለመወያየቴ እጨነቃለሁ። ለመወያየትም ደግሞ እጨነቃለሁ። መጨነቄን ለመደበቅ እጨነቃለሁ። ይህን ለመጽፍም ተጨንቄያለሁ። በመጻፌም ተጨንቄያለሁ።  የቅዱስ ጳውሎስን ጥቅስ ሳነብም የትንቢቱ መፈጸሚያነት ተስምቶን ተጨንቄያለሁ። የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ዕወቅ ያለው ለመጠበቅ ነው ወይስ እንዳንሸበር አስቀደሞ አሳውቆ መንገድን አመላክቶ ለማጽናናት? በርግጠም ለማጽናናት ነው። ሆኖም ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ መልእክቱ ላይ “ቲቶን ወንድሜን ስላላገኘሁት መንፈሴ ዕረፍት አልነበረውም”  /2ኛ ቆሮ 2 ፤12/ እንዳለ እኔም ብዙ ወንድሞቼን እንዳጣሁ ወይም እንደማጣ በማሰብ ለአዕምሮዬ ዕረፍት የለውም። እንዴት ማረፍ ይቻላል? ጌታ ሆይ እባክህን ይህን ወቅት አሳጥረው።

©️ በመምህር ብርሃኑ አድማስ
እስመ በእንቲአከ ይቀትሉነ ኩሎ ጊዜ[ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን] ሮሜ 8÷36

በዛሬዋ ቀን ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ስለአመኑት ጌታ ክርስቶስ በኔሮን ቄሳር ምክንያት በሮም ከተማ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። ሰማዕትነትን እስከ መቀበል ድረስ እግዚአብሔርን ታማኝ ሁነው አገልግለዋል። በሕይወታቸውም ጭምር በማስተማር የኔሮንን ቄሳር ዛቻና ማስፈራራት እንኳን ምንም ሳይፈሩ እውነተኛ ምስክር በመሆን ቅዱስ ጴጥሮስ ቁልቁል በመሰቀል ቅዱስ ጳውሎስ አንገቱን በመሰየፍ ሁለቱም በዚህ እለት አርፈዋል። እውነተኛ የክርስቶስ ምስክር ከሆኑት ከቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት የምንማረው እውነተኛ ምስክር መሆንና ስለ ቤተክርስቲያን ማሰብ እንደሚገባን ነው።

ሁሌም ስለሥጋ ኑሮ ብቻ እያሰብን ከሆነ እረኞች ሳንሆን ምንደኞች እውነተኛ ምስክሮች ሳንሆን የሀሰት ምስክሮች መሆናችን ነውና ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰን እውነተኛ ምስክሮች እንድንሆን አምላከ ጴጥሮስ ወጳውሎስ እግዚአብሔር ይርዳን!

የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ በረከታቸው ይደርብን!
!...
የእግዚአብሔርን እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር እንግዳ ሆነለት!

መምህር ሃይማኖት አስከብር

ሐምሌ ፯ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

ወድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? እንኳን ለቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! እንደሚታወቀው ሐምሌ ፯ የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል ነው፤ የበዓሉን ታሪክ በአጭሩ አቅርበንላችኋል፡፡

ከላይ በርእሱ እንደገለጸው የእግዚአብሔርን እንግዳን ሲጠብቅ እግዚአብሔር እንግዳ የሆነለት ታላቁ አባትን አብርሃምን እናነሣለን፡፡ በዚህ ዕለትም ታላቁ አባት አብርሃም ሥላሴን በቤቱ ያስተናገደበት ዕለት ነው፡፡ ውድ አንባብያን! እግዚአብሔርን በቤታችን እንዴት ማስተናገድ ይቻላል?እንዴትስ ወደ ቤታችን መቀበል እንችላለን? እግዚአብሔርን በቤታችን ማስተናገድ ከአባታችን አብርሃም እንማራለን፡፡

በቅዱሳን መጽሐፍት እንደተጻፈው አብርሃም በተመሳቀለ ጎዳና ድንኳኑን ተክሎ በአራቱም አቅጣጫ የሚመጣውን እንግዳ ይቀበል ነበር፡፡ የደከመውን እግሩን አጥቦ፣ የተራበውን አብልቶና አጠጥቶ የሚልክ እንግዳ የሚወድ ታላቅ አባት ነው፡፡ ሥራው መልካም ሥራ በመሆኑና ሰይጣን በአብርሃም ላይ ቀናበት፤ መልካም ሲሠራ ሰይጣን ደስ ስለማይሰኝ የሚደንቀውም በመልካም ሥራ ሰይጣን የሚደሰት ቢሆን ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን የደከማቸው ሰዎች ወደ እንግዳ ተቀባዩ አብርሃም ቤት ሲገሰግሱ ሰይጣን ጎዳና ላይ ተቀምጦ እንግዶችን ‹‹ወዴት ትሄዳላችሁ እያለ ይጠይቅ›› ጀመር፡፡ እነርሱም ‹‹ስንደክም የምናርፍበት፣ ሲርበን፣ ሲጠማን የምንበላበትና የምንጠጣበት ወደ ደጉ እንግዳ ተቀባዩ ወደ አብርሃም ቤት እንሄዳለን እንጂ›› አሉት፤ ሰይጣንም ‹‹የድሮው አብርሃም መሰላችሁ! እኔም እንደ እናንተ ደክሞኝና እርቦኝ ተቀብሎ ያስተናግደኛል ብዬ ብሄድ በድንጋይ እራሴን ፈንክቶ፣ ደሜን፣ አፍስሶ፣ ልብሴን ቀምቶና ገፎ ላከኝ እንጂ፡፡›› እንዲህ እያለ ለሦስት ቀን እንግዳ እንዳይሄድ ከለከለበት፤ አብርሃምም ‹‹ማዕደ እግዚአብሔርን ያለ እንግዳ ምስክርነት አልቆርስም›› ብሎ ለሦስት ቀን ይጠብቅ ነበር፡፡ ታዲያ የአብርሃምን ደግነት የተመለከተ እግዚአብሔር ሰይጣን ሊያስቀረው የማይችል እንግዳ ራሱ እግዚአብሔር እንግዳ ሆኖ በአብርሃም ቤት ተገኘ፤ አብርሃምም የእግዚአብሔርን እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር እንግዳ ሆነለት፡፡ (ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ አንድምታ 4$#2) እግዚአብሔርም በአብርሃም ቤት በአንድነት በሦስትነት ተገለጠለት፡፡

በኦሪት ዘፍጥረት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው እግዚአብሔር ለአብርሃም በአንድነቱና በሦስትነቱ እንደተገለጠለትና በቤቱ እንደተስተናገደ ሲገልጽ ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲህ ይለናል፡፡ ‹‹በቀትር ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ ዛፍ ሥር ተገለጠለት፤ ዐይኑንም ባነሳ ጊዜ ሦስቱ ሰዎች በፊቱ ቁመው አየ፤ ሊቀበላቸውም ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ወደ እነርሱ ሮጠ፤ ወደ እነርሱም ሰገደ፤ አቤቱ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ ባርያህን አትለፈው፡፡›› (ዘፍ. 08$1)

ሦስት ቀን ያለ እንግዳ እና ያለ ምግብ የቆየ ሰው በዚያ ላይ እግዚአብሔርን ሲያይ ከደስታው ብዛት የተነሣ ‹‹አብርሃም ወደ ሥላሴ ሮጦ ሰገደ፡፡›› አብርሃም እየጠበቀ የነበረው ሰውን ነበርና፡፡ ሰውን ሰይጣን ቢያስቀርበት ሰውን የፈጠረ እግዚአብሔር በአብርሃም ቤት ተገኘ፤ መባረክ እንዲህ ነው! በትንሹ ሲጠበቅ በብዙ መባረክ እንደዚህም ነው፤ በቅዱስ መጽሐፍ እንግዳ መቀበልን ማዘውተርና ብዙዎች እንግዳዎችን በመቀበል ፈንታ መላእክትን እንደተቀበሉ ተጽፏል፡፡ ሎጥም መላእክትን የተቀበላቸው በእንግዳ አምሳል ነበር፡፡ (ዘፍ.09$3)

ብዙ አባቶች በእንግዳ አምሳል ጻድቃንን፣ መላእክትን እግዚአብሔርን በቤታቸው ያስተናገዱት ለዚህም ነው፤ እንግዳ መቀበል እግዚአብሔርን መቀበል ነውና፡፡ አብርሃምም ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚህ ዛፍ በታች እረፉ፤ ቁራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፤ ልባችሁን ደግፉ፤ ወደ ባሪያችሁ መጥታችኋል›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹እንደወደድክ አድርግ›› አሉት። በዚያን ጊዜ ጽንዓ ፍቅሩን ለማጠየቅ ‹‹አዝለህ አስገባን›› አሉት፡፡ እርሱም ከሦስቱ አካል አንዱ ሲያስገባ ሁለቱም ቤት አገኛቸው፤ ይህም አንድነቱን ሦስትነቱን ይገልጻል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስም ‹‹አንሰ እቤ እግዚአብሔር በእንተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ እኔ እግዚአብሔር ስል ስለ አብ ስለ ወልድ ስለ መንፈስ ቅዱስ ነው›› በማለት ተናግሯል፡፡ ‹‹እግዚአብሔርም ተገለጠለት›› ካለ በኋላ ‹‹ሦስት ሰዎች አየ›› ማለቱ ነው ነው፡፡ እግዚአብሔር የባሕርይ አንድነቱ የሦስቱም ስም ነው፡፡ አንድነቱ በባሕርይ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በመለኮቱና በመንግሥቱ ነው፡፡

በሦስትነቱ በአካል በስም በግብር ነው፡፡ ለዚህም ለአብርሃም በአንድነቱም በሦስትነቱም እግዚአብሔር ተገለጠለት፡፡ አብርሃም ወደ ሣራ ዘንድ በመሄድ ‹‹ሦስት መስፈሪያ ዱቄት ለውሰሽ አንድ እንጎቻ አድርገሽ አዘጋጂ›› አላት፡፡ ሦሰት ማለቱ የሦስትነቱ፣ አንድ አድርጊው ማለቱ የአንድነቱ ምሳሌ ነው፡፡ ወደ ላሞቹ ሄዶ ከላሞቹ መካከል ያማረውን የተዋበውን ንጹሑን ወይፈን አቀረበ፤ እግዚአብሔር ንጹሐ ባሕርይ ነውና ንጹሐ ነገር ይወዳል፡፡ አብርሃም ያዘጋጀውን ተመገቡ፤ ሥላሴ ምግብ የሚበሉ ሆነው አይደለም፤ ‹ተመገቡ› ብሎ መናገሩ በሰው አምሳል ስለተገለጡለት ለአብርሃምም የበሉ መስሎት ስለታዩት እንጂ ለሥላሴስ መብልና መጠጥ አይስማማቸውም፡፡ ‹‹ሥላሴ ምግብ በሉ›› ማለት ‹‹እሳት ቅቤን በላው›› እንደማለት ነው፡፡ ቅቤውም ከእሳት ገብቶ አልቀለጠም ማለት ነው፤ መብልና መጠጥ የሥጋ ፈቃድ ነው፡፡ ይህም ይታወቅ ዘንድ የታረደው ወይፈንም ተነሥቶ ‹‹ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ›› ብሎ አመስግኗል፡፡ አንዳንዶች ይህንን ሲሰሙ ላያምኑ ሞኝነት ይችላሉ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ግን እግዚአብሔር የበለዓምን አህያ እና የቢታንያም ድንጋዮችን አናግሯል፤ ስለዚህ በሰው ዘንድ ነው እንጂ በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል የማይቻል የለም፡፡

እግዚአብሔርም አብርሃምን ጠርቶ ‹‹ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት›› አለው፡፡ እግዚአብሔር ስለ ሣራ አብርሃምን መጠየቁ ያለችበት ጠፍቶት አልነበረም፤ ልጅ እንደምትወልድ ሊነግረው ነው እንጂ፤ አብርሃምም ‹‹በድንኳን ውስጥ አለች›› አለ፡፡ ‹‹ወይቤሎ ሶበ ገባእኩ እመጽዕ ኀቤከ አመ ከመ ዮም ትረክብ ሣራ ወልደ፤ የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራ ልጅ ትወልዳለች›› ብሎ ለአብርሃም ነገረው፡፡ (ዘፍ 08$0) ሣራም በአብርሃም በኋላ ቁማ ነበርና ሰማች፤ አብርሃምና ሣራ ፺፱ ሣራ ፹፱ ዓመታቸው ስለነበር አርጅተዋልና መውለድ አይችሉም፡፡ ሣራ ብቻዋን ሳቀች፤ ይህም ሣራ አርጅቻለሁ የሴቶች ልማድም አቁማለች እንዴት ሰው ካረጀ በኋላ ልጅ ይወልዳል፡፡ ‹‹ሲያረጁ በአምባር ይዋጁ›› እንዲሉ እስከ ‹‹ዛሬ ድረስ ገና ቆንጆ ነኝ›› ብላ ተጠራጠረች፤ ‹‹ትወልጃለሽ›› መባሏ አሳቃት፤ ‹‹ወይቤሎ እግዚአብሔር ለአብርሃም ምንት አስሐቃ ለሣራ እግዚአብሔር፤ አብርሃምን ሣራን ምን አሳቃት›› አለው፤ ሣራም ‹‹አልሳቅሁም›› አለች፤ እግዚአብሔር መሳቋን እንዳወቀም ከነገራት በኋላ ‹‹በድጋሚ በዓመት እንደ ዛሬው እመጣለሁ›› አለው፤ ወንድ ልጅም እንደምትወልድም አበሠራት፤ ‹‹ጌታዬም አርጅቷል እኔስ ገና ነኝ?›› ብላም ሣራ ጠየቀች፤ ‹‹ቦኑ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር፤ በእውነት ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለ?›› እግዚአብሔርም አለ ‹‹እኔ የማደርገውን
ከአብርሃም እሰውራለሁ፤ አብርሃም በምድር ላይ ትልቅ ብርቱ ሕዝብ ይሆናል፡፡›› መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ለማብሠር በመጣ ጊዜ ‹‹ልጅ ትወልጃለሽ›› ባላት ጊዜ ‹‹ወንድ ሳላውቅ እንደምን ይሆናል›› በማለት ስትጠይቀው መልአኩ ያስረዳት ዘንድም ከእርሷ በፊት ስለ ፀነሱችውን ኤልሳቤትን ነገራት፤ ለእግዚአብሔር የሚሣነው ነገር እንደሌለም አስረዳት፡፡ (ሉቃ. 1$@6-#7) ይህም እግዚአብሔር በዘመን ብዛት የማይለወጥ መሆኑን ያስረዳል፡፡ በአብርሃም ድንኳን እግዚአብሔር ተገኝቶ ለአብርሃምና ለሣራ የምሥራች ነገሯቸው፡፡ በአማናዊት ድንኳን እመቤታችን ተገኝቶ የምሥራችን ነገራት፤ ከዚህ አያይዞ ለአብርሃም እንዲህ ብሎት ነበር፤ ‹‹በዘርህ አሕዛብ ይባረካሉ፡፡›› ከአብርሃም ዘር ከተገኘችው እመቤታችን የረከሰው ዓለም ሁሉ እንዲባረክ ሆነ፤ ምክንያቱም ከእመቤታችን የተገኘው መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ፡፡

በአብርሃም ድንኳን ሥላሴ ተስተናግደውበታል፤ ይህች ድንኳን በእመቤታችን ትመሰላለች፤ በአብርሃም ድንኳን ‹‹አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ›› እንደገቡ ሁሉ አምስት ሽህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም በእመቤታችን እግዚአብሔር አብ ለአጽንዖ እግዘአብሔር መንፈስ ቅዱስ፣ ለአንጽሖ አግዚአብሔር ወልድ፣ በተለየ አካሉ ሥጋን ለመልበስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም አድረዋልና እመቤታችን በአብርሃም ድንኳን መመሰልዋ እንዲህ ስለሆነ ‹‹አብና መንፈስ ቅዱስ ተዋሐዱ አይባልም ወልድ በተለየ አካሉ እንጂ፤

በአጠቃላይ በዚህ ዕለት በአብርሃም ቤት እግዚአብሔር የተስተናገደበት፣ አንድነቱና ሦስትነቱ የተገለጠበት፣ አብርሃም እና ሣራ ካረጁ በኋላ ልጅ እንደሚወልዱ የተበሠረበት፣ ይሰሐቅንም እንደሚወልድ የተነገረበት እንዲሁም አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ስለ ገሞራ ሰዎች የማለደበት ዕለት ነው፡፡

ለአብርሃም ምሥጢሩን የገለጠ እግዘአብሔር ለሁላችን ይግለጥልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
እንኳን አደረሳቹ ለአብሳሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብር በዓል

ሃዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
2024/09/29 23:20:21
Back to Top
HTML Embed Code: