Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲናያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ጽሁፎች ቻናል⛪️
Photo
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
ጥንቃቄ ለመላው ኦርቶዶክሳዊ❗️
#ሁሉም ኦርቶዶክስ_ሼር ሼር ሼር_ያድርግ!!!

🔔 የቀበሌ መታወቂያ ጉዳይ ❗️

💥 ታግዶ የቆየው የመታወቂያ እድሳት ከዚህ ከህዳር ወር ጀምሮ መሰጠት የተጀመረ መሆኑን ተከትሎ መታወቂያ ለማሳደስ የሚሄዱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከታች የምትመለከቱትን ፎርም አስቀድመው እንዲሞሉ በመደረግ ላይ ይገኛል።

💥 በሚሞላው ፎርም ላይ ከተካተቱት መጠይቆች አንደኛው " ሃይማኖት " የሚለው ነው። አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ ባለማስተዋልና ትኩረት ባለመስጠት በዚህ መጠይቅ ሥር "ክርስቲያን" የሚለውን መጠሪያ መጠቀም ልምድ አድርጎት ይታያል።

💥 ሆኖም በዚህ ወቅት እንደ ወል ስም እያገለገለ በሚገኘው ስም መጠቀም ከኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር ጋር ተያይዞ በቀጣይ ትልቅ ፈተና ይዞ የሚመጣ መሆኑን በማስተዋል ሃይማኖት በሚለው መጠይቅ ሥር " #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ " የሚለውን የሃይማኖታችንን መጠሪያ ለይቶ በአግባቡ መሙላት ይገባዋል።

💥 በክርስትና ስም የሚጠቀሙ ሌሎች የሃይማኖት ድርጅቶች በመኖራቸውና ይህም የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር የተዛባና የተሳሳተ እንዲሆን ያደርጋል።

💥 በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ እንዳለው ኦርቶዶክሳውያን ከሀገሪቱ ፖለቲካዊ ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እየተገፉና እየተገለሉ እንዲሄዱ በማድረግ ቁጥራቸውን በማዛባትና ዝቅ አድርጎ በማሳየት ፍላጎታቸውን ለማሳካት ለሚፈልጉ አካላት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አይገባም።

💥 በተለይም በዕድሜ የገፉና የቀለም ትምህርት ያልቆጠሩ ወገኖቻችንን በማሳወቅ " #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ" የሚለውን የሃይማኖታችንን መጠሪያ በአግባቡ እንዲሞሉ ማድረግ ከእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ የሚጠበቅ ተግባር ነው።
Audio
በደብር ሰላም ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን በአርብ ሃገር በኪዌት

ቆሞስ አባ በርናባስ በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ቅብዓ ሜሮን በሐዲስ ከዳን

ሜሮን አገልግሎት

ቅብዓ ሜሮን አፈፃፀም እንዴት ነው

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
Easy Voice Recorder
*ከክፍ ነገር ኹሉ የአዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚኽን ብላቴኖች ይባርክ*
*(ኦሪት ዘፍጥረት ፵፰÷፲፯)*
በመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ አበበ
ለመምህራችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
*ማኅበረ ተዋሕዶ ዘኦርቶዶክስ*
ደቂቃዉ *//46፥51//*
*Ke Kfu Neger Hulu Yeadanegne Melak Ersu Enezihn Blatanoch Yibark*
*(Orite Ze Ftret 48÷16)*
Be Megabe Hadis Kesis Abebe
Lemehrachn Kale Hiywet Yasemaln
*MAHBERE TEWAHDO ZE ORTHODOX*
👆👂👂👈
https://youtube.com/channel/UCSzRc-X36uAdN5vIJ6MPwlQ
*የዩቲዩብ ቻናል👆*
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
ዲያቆን ተስፋዬ ቻይ
ኅዳር 12 ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? እየበረታችሁ ነውን? የሩብ ዓመት የምዘና ፈተናስ እንዴት ነው? መቼም ትምህርቱን በትኩረት ከተከታተላችሁ የምዘና ጥያቄዎችን እንደምትሠሩት ጥርጥር የለውም! በተለይ ልጆች መምህራን የሚነግሯችሁን በትኩረት በማዳመጥ፣ መጻሕፍትን በማንበብና ያልገባችሁን በመጠየቅ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ አለባችሁ፡፡ መልካም! ውድ የእግአብሔር ልጆች ለዛሬ ምንማረው ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ ስለሆነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! አምላካችን እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ቅዱሳን መላእክትን ፈጥሯቸዋል፤ እነርሱም እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና እኛንም የሚጠብቁ ናቸው፤ ነቢዩ ንጉሥ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹የእግዚአብሔር መላእክት በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራሉ፤ ያድናቸውማል››  በማለት እንደ ገለጸልን  ቅዱሳን መላእክት እኛን ከክፉ ነገር ይጠብቁናል፡፡ (መዝ.፴፬፥፯)
ውድ እግዚአብሔር ልጆች! ታዲያ እኛ የእነርሱን ጥበቃና ርዳታ ስንፈልግ እግዚአብሔርን  እንድንፈጽመው ያዘዘንን ትእዛዝ ስንፈጽምና  ጥሩ ሥነ ምግባራት ሲኖረን ነው፡፡ ልጆች! መላእክት በተፈጥሮ ብዙ ቢሆኑም የመላእክት አለቃ የሚባሉ ግን ሰባት ናቸው፤ ከእነዚህም የመላእክት ሁሉ አለቃ አንዱ ቅዱስ ሚካኤል ነው፤ ሚካኤል ማለት ‹‹ማን እንደ እግዚአብሔር›› ማለት ሲሆን ከእግዚአብሔር ተልኮ ሰዎችን በችግራቸው የሚረዳና ፈጣሪውንም የሚያመሰግን መልአክ ነው፡፡
ውድ የእግአብሔር ልጆች ! ቅዱስ ሚካኤል በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲሁም በድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል እንደተጻፈልን ለችግራቸው ደርሶ የልባቸውን የፈጸመላቸው፣ ከመከራ ያዳናቸው፣ ከሰይጣን ተንኮል የታደጋቸው ብዙ ሰዎች ናቸው፡፡ ሁል ጊዜ በየወሩ በ፲፪ (ዐሥራ ሁለት) ቀን መታሰቢያ በዓሉን እንዘክራለን፤ በዓመት ውስጥ ኅዳርና ሰኔ ወር ላይ ደግሞ ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይዘከራል፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ታሪኩ ብዙ ቢሆንም በኅዳር ፲፪ ቀን የሚከበርበትን በመጠኑ እንነገራችኋለንና አጽንዖት (ትኩረት) ሰጥታችሁ ተከታተሉን፡፡ መልካም! ኅዳር ፲፪ ቀን ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት ሁሉ አለቃ አድርጎ እግዚአብሔር የሾመበት ቀን ነው፤ ሌላው ደግሞ ልጆች እስራኤላውያንን ከፈርኦን ሠራዊት የታደገበት በዓል ነው፤ እስራኤላውያን ከግብጽ አገር በስደት (በመከራ) ከነበሩበት እግዚአብሔር ሲያወጣቸው ሊቀ ነቢያት ሙሴን መርጦት ሕዝቡን እየመራ ከግብጽ ወደ ከነዓን ወደ ተባለች አገራቸው ይመራቸው ጀመር፡፡ ይገርማችኋል ልጆች! ፈርዖን የተባለው የግብጽ ንጉሥ ሕዝቡን ሊይዛቸው ብዙ ሠራዊት (ወታደር) አስከትሎ ከኋላቸው ሲከተላቸው እስራኤላውያን ለማምለጥ ወደ ፊት ሲሄዱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከፊታቸው እየመራ መልካሙን መንገድ ያሳያቸው ነበር፡፡ እንደገናም መንገዱ በረሃ ነበርና ፀሐይ እንዳይነካቸው በደመና እየጋረደ ማታ ደግሞ ሲሆን እንዲታያቸው ብርሃን (ፋና) እያበራላቸው ይጓዙ ነበር፡፡
አያችሁ ልጆች! ለዚህ እኮ ነው ነቢዩ ዳዊት ‹‹ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና››  ያለው መልካም ከሆንንና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ከጠበቅን ክፉ ነገር እንዳይነካንና መንገዳችን እንዲቀና እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክቱን ይልክልናል፡፡ (መዝ.፺፥፲፩) ታዲያ አንድ ጊዜ እስራኤላውያንን ያሳድድ የነበረው ፈርኦን ከኋላ ሲከተላቸው እነርሱም ወደ ፊት ሲሄዱ በጣም ትልቅ ባሕር አጋጠመቸው፡፡ ልጆች! ሕዝቡ ከኋላቸው ፈርኦን ነበር፤ ከፊታቸው ደግሞ ትልቅ ባሕር ነበር፡፡ የዚህን ጊዜ በጣም ተጨነቁ፤ ፈሩም፤ ወዴት እንደሚሄዱ አማራጭ አጡ፡፡
ከዚያም ይመራቸው የነበረው ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም እንዲረዳቸው ቅዱስ ሚካኤልን ላከላቸው፡፡ ከዚያም ነቢዩ ሙሴ በበትሩ ባሕሩን ሲነካው ያ ትልቁ ባሕር ሁለት ቦታ ክፍል አለ፡፡ ይገርማችኋል ልጆች! ውኃው እንደ ግድግዳ ቀጥ ብሎ ቆመ፤ ከዚያም ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ለሁለት በተከፈለው ባሕር መካከል ሕዝቡ ተሻገሩ፡፡
ልጆች! እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ የሚቻለው አምላካችንና ፈጣሪያችን ነው፡፡ ባሕሩን በቅዱስ ሚካኤል አማካኝነት ደረቅ አደረገላቸውና በውስጡ አልፈው ሄዱ፤ ይገርማችኋል! ያሳድዳቸው የነበረው ፈርኦን ተከትላቸው፤ ለሁለት ተከፍሎ እንደግድግዳ (ግንብ) በቆመው ባሕር ውስጥ ሠራዊቱን (ወታደሩን) አስከትሎ  ገባ፡፡ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ባሕሩን አቋርጠው እንደጨረሱ የፈርኦን ሠራዊቶች ከመካከል ሲገቡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ባሕሩን በበትሩ ነካው፤ በዚያን ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ያንን ባሕር ወደ ቦታው እንዲመለስ ሲያደርገው እንደ ግንብ የነበረው ውኃ ፈሰሰ፤ ከዚያም ፈርኦንና ሠራዊቱ በባሕር ውስጥ ሰጠሙ፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! በመጀመሪያ እግዚአብሔር ፈርኦንን ሊያስተምረው ብዙ ተአምራትን እያደረገ አሳይቶት ነበር፡፡ ፈርኦን ግን ሳያምን ስለቀረና በትእቢቱ የተነሣ እምቢ በማለቱ በመጨረሻም በኤርትራ ባሕር ሰጠመ፡፡ ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን ለቀጣላቸውና እነርሱንም ከመከራ ላዳናቸው አግዚአብሔር ‹‹እግዚአብሔርን እናመስግነው፤ምስጉን ነው የተመሰገነ…›› እያሉ ዘመሩ፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እግዚአብሔርን የታመነ መከራ ቢገጥመውም ቅዱሳን መላእክቱን ልኮ ያድነዋል፤ እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ታምነው ስለነበር በችግራቸው ጊዜ ቅዱስ ሚካኤልን ላከላቸው፡፡ መልአኩ በመንገዳቸው እየመራና የሚያስፈለጋቸውን እያደረገ ጠላቶቻቸውን በመቅጣት ጭንቀታቸውን አራቀላቸው፤ ከመከራ ታደጋቸው፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ከእስራኤላውያን ታሪክ ምን እንማራለን እግዚአብሔርን የሚያምን በመከራው ጊዜ ቅዱሳን መላእክት እንደሚላኩላት፣ ሕጉንና ትእዛዙን ማክበር እንዳለብን፣ ቅዱሳን መላእክትን በችግራችን ጊዜ ስንጠራቸው ፈጥነው እንደሚያድኑን ተምረናል፡፡ ሌላው ደግሞ ልጆች! የሚነገረውን የማይሰማና ከጥፋቱ የማይመለስ መጨረሻው መጥፋ እንደሆነ አይተናል፡፡  ፈርኦን የተባለው ጨካኝ ንጉሥ የእግዚአብሔርን ልጆች መከራ ሲያሳያቸው እግዚአብሔር ተአምራት አድርጎ ከጥፋቱ እንዲመለስ ነገረው፤ እርሱ ግን አልመለስም አለ፤ በመጨረሻም በባሕር ውስጥ ሰጠመ፡፡
ልጆች! አመጸኛና ተው የሚሉትን የማይሰማ መጨረሻው ጥፋት ነው፡፡ ታላላቆቻችንን የሚነግሩንን መስማትና ከጥፋት እንድንመለስ ሲመክሩን መመለስ አለብን፡፡ ፈርኦን ተው ሲባል እምቢ አለ፤ ግን በመጨረሻ ተቀጣ።
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ ስለ ሆነው ስለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ካደረጋቸው ብዙ ድንቅ ተአምራቶቹ በኅዳር ፲፪ ቀን የሚታሰበውን ብቻ በጥቂቱ ነግረናችኋል፡፡ በቀጣይ ደግሞ የሌሎቹን ሊቃነ መላእክት ታሪክ እንነግራችኋለን፤ ይቆየን! ደኅና ሁኑ ልጆች!
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ምስጢረ ሜሮን ለምን ከጥምቀት ቀጥሎ እንዲፈጸም ይደረጋል

ሜሮን አቀባብ እንዴት ነው

ኃጢአት ለንስሐ አባት መናዘዝ ለምን አሰፈለገ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ከንስሐ በፊት

በንስሐ ጊዜ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
"" የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ ""

(ማቴ. ፮:፳፮)

በመምህርዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ

(ኅዳር 14 - 2015)
Audio
ወፍም ቤትን አገኘች
                   
  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ከንስሐ በሃላ



አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት


ክህነት ምንድነው


የምሥጢር ክህነት አመሠራረ ኪዳን

የምስጢር ክህነት አመሠራረት በሐዲስ ኪዳን

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት


የክህነት ዓላማና ጥቅም ምንድነው

ሥልጣና ክህነት ለማን ይስጣል

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ስርዓት ተክሊል ምንድነው

ጋቢቻ መቼ እና ማን መሰረተው

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ጋቢቻ ቅድም

ጋቢቻ በሃላ

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
Audio
መሠረተ እምነት  በአንዲት ሀይማኖት

ፋቺ የሚፈቅድባቸው ምክንያቶችስ

ምሥጢረ ቀንዲል

አዘጋጅና አሳታሚ :-ኢንጂነር ወንዴ ጫኔ
2024/10/05 15:18:46
Back to Top
HTML Embed Code: