Telegram Web Link
💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️
 
እንካን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አምታዊ በ ዓል አደረሰን:: ስምሽ ጉልበት ሆኖኝ ወጣሁት ዳገቱን  ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ አለፍኩት ዳገቱን::

    #መልካም እለተ

     #ድምፀ_ተዋህዶ
መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከእስር ተፈቱ።

የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከእስር መለቀቃቸውን የማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ለእስር የተዳረጉት።

ከሁለት ወራት በኋላ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016  ዓ.ም  ከእስር  መለቀቃቸውን  ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
እንኳን ለቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኁ፤ አደረሰን።

"ሰላም ለከ ጴጥሮስ ተልሚድ፤ ዘኢያቅበጽከ ተስፋ ነገረ ኑፋቄ ወካህድ፤ እንዘ ትረውጽ ጥቡዐ ለመልእክተ ክርስቶስ ወልድ፤ አመ ለሊከ ወሬዛ ቀነትከ በእድ፤ ወአመ ልህቀ አቅነተከ ባዕድ።"

"ሰላም ለጳውሎስ ሃይማኖተ ክርስቶስ ዘአግሀደ፤ እስከ አቊሰልዎ በሰይፍ ወመተርዎ ክሣደ፤ ከመ ያግብእ ሕዝበ ህየንተ ቀዳሚ ሰደደ፤ በላዕለ አብዳን ተመሰለ አብደ፤ ወለአይሁድኒ ኮኖሙ አይሁደ።"

❖ ሐምሌ ፭ ❖

✞ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ [የምስክርነታቸው መታሰቢያ]፤ ቅዱሳት አንስት:- ዴውርስ፣ ቃርያ፣ አቅባማ፣ አቅረባንያ፣ አክስትያና (የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮች) [መታሰቢያቸው]፤ ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ (የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር) [መታሰቢያው] የሚከብርባት ዕለት ናት✞
#ቅዱስ_ቂርቆስና_እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ (#ሐምሌ_19)

ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው። 

ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው። 

ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ። 

መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። 

በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። 

ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው። 

ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። 

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። 

ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ ➛ ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ)

#ድምፀ_ተዋህዶ
2024/09/28 23:17:57
Back to Top
HTML Embed Code: