Telegram Web Link
እመቤታችን ባንቺ ምልጃ

እመቤታችን ባንቺ ምልጃ ባንቺ ምልጃ
ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ
መድኃኒዓለም ታምር ሰራ በማየ ቃና x2

ለጌታችን ተዓምር ........በማየ ቃና
ተመርጣ ታድላ ..........በማየ ቃና
መጀመሪያ ሆነች ........በማየ ቃና
ቃና ዘገሊላ ...............በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

ታውቋት ስላለችው ......በማየ ቃና
ወይንኬ አልቦሙ.........በማየ ቃና
ውሃ ወይን ሲሆን ........በማየ ቃና
ሁሉ አዩ ሰሙ ............በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አሳላፊዎቹ .....................በማየ ቃና
ግራ ቢገባቸው ...............በማየ ቃና
የድንግል ማርያም ልጅ .....በማየ ቃና
ከጭንቅ አወጣቸው ........በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

እኛም እናምናለን.........በማየ ቃና
በእርሷ ትንብልና .........በማየ ቃና
ስለ ቃልኪዳኗ............በማየ ቃና
ሁሉ እንደሚቀና .........በማየ ቃና
ቃናን ሊያደርጋት የታምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ
Forwarded from ዘ-ተዋሕዶ ቦት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሮንጋዴ ቢጫ ቀይ የኖህ ቃል ኪዳን ምሳሌ ነው

የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ 3ሺ አመት ታሪክ ያለው ሳይሁን የጥንት የኖህ ቃል ኪዳን ነው

እኛ ታቦት አናመልክም የምናመልከው እግዚአብሔር ነው

ቃለ ህይወት ያሰማልን አባታችን
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ካራቆሬ ባህር ጥምቀት 10 ደብር አንድ ላይ ሆነው ረጴ ኪዳነምህረት እና በረከቴ ገብርኤል እና ጀሞ ተክለሃይማኖት ሲወጢ
የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል

ታምረኛው ፡ እጅግ ጥንታዊ ፡ ታሪካዊና እድሜ ጠገብ ቅርሶች ባለቤት የሆነውን በ12ኛው መቶ ክፈለ-ዘመን የተመሰረተው የትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል " የደቡብ ቁልቢ " ከብዙው በጥቂቱ እናስተዋውቆ !!

እዣ ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮአዊ እና ባህላዊ ለቱሪስት ቀልብ የሚስቡ መስህቦች መገኛ ከሆኑት አካባቢዎች ውስጥ በግንባር ቀደም ተጠቃሽ ስትሆን እጅግ ማራኪና የአየር ንብረ ለውጥ ለመከላከል የሚያስችሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ደኖች ፡ ውብና ማራኪ ፏፏቴዎች ፡ ትክል ድንጋዮች ፡ ጥንታዊና በውስጣቸው እድሜ ጠገብ ቅርሶችን የያዙ ገዳማት ፡ እና ካቴድሪያሎች ተጠቃሾች ናቸው ።

ከነዚህም መካከል እጅግ ታሪካዊ ፡ ጥንታዊና የሀገር ውስጥና የውጭ የጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ ያለው የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል "የደቡብ ቁልቢ " ከብዙው በጥቂቱ እናስተዋውቆ ።

የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ገደብ ቀበሌ የገረሙጀ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከዞናችን ዋና ከተማ ወልቂጤ በ52 ኪ ሜ እና የእዣ ወረዳ ዋና ከተማ ከሆነችው አገና በ10 ኪሜ ርቀት በስተ-ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኝ ነው።

ካቴድሪያሉ በ12ኛው መቶ ክፈለ-ዘመን በስደት ከአክሱም ፂዮን "ወሰናይ " ተብለው ይጠሩ በነበሩት አባት ከብዙ በጉዞአቸው ላይ ከነበረው ከድቅና ብዙ ታዓምር በኋላ ይዘው በማምጣት እንደሰየሙት በጉራጌ ሀገረ-ስብከት የእዣ ወረዳ ቤተ-ክህነት ስራስኪያጅ እና የአትርፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል አስተዳዳሪ የሆኑት መላከ ብርሃን ብስራት አካለ ወልድ ይናገራሉ ።

በየ ዓመቱ ጥር 18 በርካታ የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በመሳተፍ በድምቀት የሚከበረው ካቴድሪያሉ በአባታችን በአቡነ መልከ-ፄዲቅ ከተለያየ ቦታ በመምጣት እጅግ ቁጥር ያላቸው እንግዶች በክብረ -በዓሉ መገኘትና የተሳሉትን ስለት ቶሎ የሚሰማ መሆኑን ብዙዎቹ በመመስከራቸው ምክንያት " የደቡብ ቁልቢ " የሚል ስያሜ እንደሰጡትም የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ብርሀን ብስራት አካለወልድ ያስረዳሉ ።

በካቴድሪያሉ ከነሀስና ብር የተሰሩ ጥንታዊ መስቀሎች ፡ ፅዋዎች ፡ የተለያዩና እድሜ ጠገብ የብራና መፅሀፎች ፡ የጥበቃ መሳሪያዎችና በርካታ ቅርሶች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በቀድሞ ሀገርመሪ በነበሩ እንደ አፄ ሚኒሊክ ፡ ደጅ አዝማች ፡ ደጅ አዝማች ባልቻ ፡ ደጅ አዝማች ሀብተ -ጊዮርጊስ የተበረከቱ ቅርሶች በካቴድሪያሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተሰራው ዘመናዊ ሙዚየም ውስጥ መመልከት ወይም መጎብኘት ይቻላል ።

ካቴድሪያሉ ከሀይማኖት ስርዓት በተጨማሪ ከእምነቱ ተከታዮች ውጪ ያሉትም ጨምሮ በተለያየ ማህበራዊ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን በደንና አካባቢ ጥበቃ ስራ አሻራ እያኖረ ያለና ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ 22 ወገኖች በቋሚነትም ይረዳል ።

በየዓመቱ ጥር 18 እጅግ በአስደናቂ ሁኔታ የሚከበረው የአትፎ ደብረ-ወርቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድሪያል በወረዳው የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር በማድረግና የገቢ አቅም በማሳደግ ረገድ የራሱ ድርሻ እንዳለውም የሚታመን ነው ።

ይህን ታሪካዊ ፡ ተፈጥሮዓዊ እና የበርካታ ቅርስ ባለቤት የሆነውን ካቴድሪያል እንድትጎበኙ እንጋብዛለን ።
#ወዳጆቼ___?

#ኃጢአት መሥራት በራሱ  አስቀያሚ ነው፤ ኃጢአት ከሠሩ በኋላ በዚያ ኃጢአት መታበይ ግን እጅግ #ጽኑ_ደዌ ነው፡፡ #ጽድቅን ሠርተው በዚያ በሠሩት ጽድቅ #ከተኩራሩበት ጽድቁን ያጡታል፡፡ ይህ በኃጢአት ሲኾን ደግሞ የባሰ ነው፤ ወደ ከፋ ጥፋት ይወስደናልና፡፡ ከሠራነው #ኃጢአት ይልቅ በሠራነው ኃጢአት መታበይ የሚያመጣው ፍዳ ኵነኔ እጅግ #ጽኑ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

       
#መልካም__ቀን🙏
2024/09/29 21:22:36
Back to Top
HTML Embed Code: