Telegram Web Link
ህግ አስከባሪዎቹ አሸንፈዋል🔨🔨

ጂሲ ካፕ

ዛሬ በተደረገው የህግ ተማሪዎች እና የኢንድስትሪያል ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች የማጣሪያ ጨዋታ በ 2-1 ውጤት በህግ ተማሪዎች አሸናፊነት ተጠናቋል።

የህግ ኮሌጅ በ3 ቢጫ ካርድ የተቀጣ ሲሆን የኢንድስትሪያል ኢንጅነሪንግ ምንም ካርድ ሳይታይበት ጨዋታውን ጨርሷል።

ጨዋታዎቹ ነገ ሲቀጥሉ

በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት(COTM) እና በሲቪል ኢንጅነሪንግ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ነገ አርብ 10:00 ጀምሮ ይካሄዳል። 

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
የሃዘን መግለጫ
=========
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ ዓመት የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል የዕረፍት ቀናት ተማሪ የነበረው ኃይሉ የሽጥላ ማርሸት በአደረበት ህመም ምክንያት በ13/9/2016 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፡፡

በመሆኑም የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በተማሪያችን ህይወት ማለፍ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቹ፣ለጓደኞቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

የደ/ብ/ዩ/ማህበረሰብ
@DBU11
ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የበጎ አድራጎት የተማሪዎች ቡድን በልዩ ፍላጎት ዘርፍ ለተማሪዎች እንኳን ደህና
መጣቹ (WELCOME) ፕሮግራም አዘጋጅቶ ኑ አብርን በጎ ስራዎችን እንስራ ይላል።

ይህ የእንኳን ደህና መጣቹ ፕሮግራም በዋናነት አይነ ስውራንን ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀ ፕሮግራም ሲሆን ይህ ታላቅ ፕሮግራም የሚዘጋጅው እሁድ ግንቦት 18 ከቀኑ 7:30 ጀምሮ በPR አዳራሽ ይካሄዳል።

በእለቱ በአይነስውራን ተማሪዎች የተዘጋጁ ተውኔትን ጨምሮ የተለያዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።

የደብረ ብርሃን ዩኒቭርሲቲ የበጎ አድራጎት የተማሪዎች ክበብ!

@DBU11
Civil Engineers እንኳን ደስ አላችሁ!

ትላንት አርብ 10 ሰዓት  Construction technology management ከ Civil Engineering ጋር ባደረገው ጨዋታ

በ4-1 ውጤት ገንቢው ሲቪል ወደ ፍፃሜ ጨዋታ ተሸጋግሯል።

ሲቪል ኢንጅነሪንግ በ 1 ቢጫ ካርድ የተቀጣ ሲሆን በአንፃሩ ኮተም ዲፓርትመንት የ2 ቢጫ ካርድ ባለቤት ሆነው ተሸንፈዋል።

ነገ እሁድ የፍፃሜ ጨዋታው በሲቪል እና በህግ ተማሪዎች መካከል ይካሄዳል።

መልካም እድል!

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
ለማስታወስ ያህል

ሆሄ ተስፋ በአዲስ አበባ ለ4ኛ ዙር ያዘጋጀውን ልዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅት ታደሙልኝ ይላል።

እሁድ 8:00
መገናኛ ዋች ህንፃ
1ኛ ፎቅ - ጣዕም ባህላዊ የምግብ አዳራሽ

መግቢያ በነፃ
Use map https://maps.app.goo.gl/1x9HsYgRDesDKALi9

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
#Advertisment

እማዬ ሾርባ እና ስቲም ቡና

በልዩ አቀራረብ እና መስተንግዶ በአዲስ መልክ ተመልሰናል።

ሾርባ
ድንች ቅቅል
ቺፕስ(በካቻፕ)
እርጥብ/በአቮካዶ/ካቻፕ/በእንቁላል)
ቡና እና ሻይ
የለውዝ ሻይ
ቀሽር
እንዲሁም እንደምርጫዎ ቢያዙን እናስተናግዶታለን።

አድራሻ አልሚ ምግብ ቤት አጠገብ
0934892799
0980000091
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
-----------------------------
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በDocter of Medicine/MD/ መምህር በቅጥር አወዳድሮ ለመመደብ በቁጥር 0635/02-01/6 በቀን 08/08/2016 ዓ.ም ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን አሟልታችሁ ለተመዘገባችሁ ብቻ በቀን 22/09/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግቢ ለፈተና የተጠራችሁ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡

ማሳሰቢያ
-------------
* ለፈተና የሚመጣ ተወዳዳሪ ራሱን የሚገልጽ መታወቂያ ካልያዘ ፈተና ላይ አይቀርብም፡፡
* ማንኛውም ተወዳዳሪ የሞባይል ስልክ ይዞ መግባት አይችልም፡፡
* በሰዓቱ ያልተገኘ ተወዳዳሪ ወደ ፈተና መግባት አይችልም፡፡


ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ
አስራት ወልደየስ ጤናሳይንስ ካምፓስ

@DBU11
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ለ5 የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች ከባድ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀት እና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገንዘብ ሚንስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በገመገመበት ወቅት

የ ወላይታሶዶ፣ጋምቤላ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንቶች ከሃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣
አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ፤
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በፌድራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የተቋማት ኦዲት ሪፖርት የ2014 በጀት ዓመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 24 መስሪያ ቤቶች ውስጥ እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት ውስጥ ተካተዋል።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
2024/06/30 19:28:05
Back to Top
HTML Embed Code: