Telegram Web Link
DBU Daily News
አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ! @dbu11
📌📌Exclusive ሰለ ተመራቂ ተማሪዎች 

ዛሬ የተማሪ ህብረት እና የክፍል ተወካዮች ከተናገሩት ቻናላችን  ያገኛቸው መረጃዎች


👉በዛሬው ዕለት የተማሪዎች ህብረት የክፍል ተጠሪዎችን በጠራው ስብሰባ ላይ ተመራቂ ተማሪዎች የተለያዩ ነጥቦችን አንስተዋል።

👉ተጠሪዎቹ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲንም ሆነ የተማሪዎች ህብረትን በሚሰጠው መረጃ ዙሪያ ዕምነት ማሳደር እንዳቃታቸው  ተናግረዋል።

👉በተደጋጋሚ ከተጠየቁ ጥያቄዎች መሃከል የመመረቂያ ቀን ጉዳይ ሲሆን ተማሪዎቹ  የመመረቂያ ቀን መቼ እንደሚሆን በእርግጠኝነት እንዲነገራቸው ጠይቀዋል።

👉በቀጣይም ቀሪ የመጨረሻ ሴሚስተር ና   ለExit exam tutor ያለው የጊዜ ሰንጠረዥ አከራካሪ እንደነበር ተሰሞቷል

👉አንዳንድ ተማሪዎች የExit exam tutor አላስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም እንደ ምክንያት ያነሱት፦ ፈተናው ላይ ለሚመጡት ኮርሶች ጠቅላላ በቂ አስተማሪ አለመኖር ፣ የሀገራችን ሰላም አስተማማኝ አለመሆን፣ ከዩኒቨርስቲ ስንወጣ ያለንን የስራ ዕድል ላለማባከን እንዲሁም  ለድጋሜ ትምህርት እርስ በእርስ መደጋገፍ እንችላለን በሚል ሃሳባቸውን ገልጸዋል ።

👉በአንፃሩ ሌሎች ተማሪዎች የtutorኡን  አስፈላጊነት  Exit exam ማለፍን እንደዋና ነጥብ አንስተውታል።

👉 ሌላኛው በውይይቱ የተነሳው ነጥብ የ2013  ባች ተማሪዎች cost sharing አከፋፈል የተጠቀሙትን ጊዜ ከግምት ያስገባ እንደሆነ ጠይቀዋል።

👉ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸው ግልፅ የሆነ ነገር በፍጥነት መስማት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

👉የተማሪዎች ህብረት ጥያቄዎቻቸውን ለሚመለከተው አካል አቅርበው ፈጣን የሆነ መልስ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።



@DBU11
@DBU11
በትላንትናው እለት ጥቅምት 22 ረፋድ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ከትምህርት ሚኒስቴር በተላኩ ባለሙያዎች አማካኝነት student satisfaction survey (የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች እርካታ ጥናት) መረጃ ሲሞላ የነበረ መሆኑን DBU daily news መመልከት ችሏል።
ባለሙያዎቹ የሚሞላው መረጃ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ምን ያህል ተጠቃሚ መሆናቸውን እና በቆይታቸው ያላቸውን እርካታ ለመረዳት እና አስፈላጊ ከሆነ የትምህርት ፓሊሲ እና እቅዶችን መንደፍን ጨምሮ አስፈላጊ ሪፎርም ለማድረግ ያገለግላል ብለዋል። ይህ survey በሁሉም የሀገሪቱ ዩንቨርስቲዎች ይካሔዳልም ነው ያሉት።የ survey data መሰብሰቢያ ጥያቄዎቹ ከዚህ በታች የተያያዙ ሲሆን አውርዳችሁ መመልከት ትችላላችሁ ወይም ከዚህ በታች በተቀመጠላችሁ ሊንክ በመግባት በስልክ ከከፈታችሁ desktop site ላይ አድርጋችሁ መመልከት ትችላላችሁ። አስተያየቶቻችሁንም የመልዕክት መስጫ ሳጥን ላይ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።
👉Questionnaire to be filled by students
https://forms.office.com/r/V27dbncPBT?origin=lprLink

@DBU11
@DBU11
Telegram account hack እየተደረገ ነው

"There are your photos in it" ከሚል massage ጋር link በመላክ እና የተለያዩ text በሚያውቁት ሰው በኩል በመላክ telegram account hack ማድረግ ስለተጀመረ ተጠንቀቁ

ያልተረጋገጠ link ከመክፈት ተቆጠቡ

@DBU11
@DBU111
OLD GROUP

የትኛውም የማትጠቀሙበት ወይም ማትፈልጉት ከተከፈተ 2 አመት እና ከዛ በላይ የሆነው ማለትም በፈረንጆቹ 2022,2021,2020,2019,2018,2017 የተከፈተ የቴሌግራም Group የ class ሊሆን ይችላል or የአሳይመንት ወይም ሌላ  ያላችሁ አምጡት ልግዛቹ🤝

እኛ ጋር ሲመጡ ልዩ የሚያደርገን ከሶስት በላይ ምታመጡ ከሆነ የቦነስ ብር እንሰጣለን::

እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ በ አካልም አግኝታችሁን መጨረስ ትችላላችሁ DBU  ለሆናችሁ አሁን ላይ

  Block 35 dorm 202 እንገኛለን መታችሁ አውሩን ወይም ደግሞ ያለችሁበት መጥተን መጨረስ እንችላለን
ይደውሉልን 0964035485

በተሻሻለው ዋጋ

2018 = 750 birr
2019 = 700 birr
2020 = 650 birr
2021 = 600 birr
2022 = 550 birr
2023 first 5 month=300 birr


በጣም በአሪፍ በሆነ  ዋጋ እገዛለሁ ነው

Member 1 ቢሆንም ችግር የለውም 🤝

💰Payment method {የክፍያ መንገድ}
Telebirr or 🏛Bank


ማሳሰቢያ የትኛውም ተጠቃሚ ጉሩፑን ሲሸጥ ሁሉንም አባሎች ከጉሩፑ ማስወጣት እና የተከፈተበትን ቀን የማይበት መጀመሪያ ላይ የተፓሰቱ ፖስቶች አስቀርተው ማጥፋት ይችላሉ:: ይህም ሽያጩ ከምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የፀዳ መሆኑን ልብ ይለዋል ::
ግን አደራ clear history እንዳትሉት🙏

የቴሌ ግራም ግሩፕ ለምን መግዛት አስፈለጉ  አይነት ጥያቄዎችን በተመለከተ ቻናላችንን join ብለው  ሙሉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
                 Our channal
    https://www.tg-me.com/groupbuyerreall

Contact  @Ebenezer_ofga
                   @Narccccc
                    0964035485
ውድ ሆሄያውያን!

ከብዙ ጊዜያት መጠፋፋት በኋላ እንደተለመደው ሆሄ እንደገና በሩን ከፍቶ ኑ እንሞዝቅ ፣እነደርም፣ እንፃፍ፣እንግጠም ይላችኋል ።

፨ ነገ SE01 በ11 ሰዓት ማንም እንዳይቀር
ይህ ማስታወቂያ ለነባር አባላት ሲሆን
በቅርቡም ለአዲስ አባላት የምዝገባ ማስታወቂያ የምናወጣ መሆኑን ልናሳውቅ እንወዳለን።

                 የሆሄ ተስፋ ኪነጥበብ ቡድን

@dbu11
@dbu_entertainment
Non cafe መመዝገብ ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ ምዝገባ ተጀምሯል

@DBU11
@DBU11
የበጎ አድራጎት ክበብ አባላት ለነበራችሁ ተማሪዎች

የፊታችን እሁድ ከምሽቱ 1:00 የቀድሞ አባላቶች ስብሰባ ያካሂዳል።(መገናኛ ቦታ LH02)

እንዲሁም በክበቡ ውስጥ አዲስ አባል መሆን ለምትሹ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የአባላት ምዝገባ የጀመረ መሆኑን ያሳውቃል።
(መመዝቢያ ቦታ SE01 ቢሮ ቁጥር 05)

ለበለጠ መረጃ 0918099394/0918337898 ይደውሉ።


         የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ በግ አድራጎት ክበብ
@dbu11
@dbu_entertainment
ለግንዛቤ (ዝቅተኛው 4° ደርሷል )

ለደብረብርሃን አዲስ ባይሆንም ሰሞኑን የነበረው ቅዝቃዜ በተለይም ማለዳ እና ምሽት ላይ ከባድ በሚባል መልኩ ልዩ ቅዝቃዜ ተስተውሏል።

በዚህን ሰሞን ዝቅተኛው መጠነሙቀት እስከ 4°C እንዲሁም ከፍተኛው 19°C የተመዘገበ ሲሆም ባለፉት ዓመታት በተለይም ታህሳስ እና ጥር ላይ ዝቅተኛ እስከ 1°C ተስተውሏል።

እና የብርዱ ነገር እንዴት ነው...?

@DBU11
@DBU111
🖇 Join Our : Channel | Group | Tik Tok | LinkedIn
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🚀 4 Days to Go! TechtonicTribe’s Big Event!

This Saturday at DBU, join us for a day of tech, inspiration, and connection. Don’t miss out!

📅 Date: Saturday, 7/02/2017
Time: 2:00 PM - 5:30 PM
📍 Location: PR Hall, DBU

Let’s build the future together! 🌍💡🖇 Join Our : Channel | Group | Tik Tok | LinkedIn
ትልቅ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ዕድል በዩኒቨርስቲአችን!

የእንግሊዝኛ ቋንቋችሁን ማዳበር የምትፈልጉ ተማሪዎች  በግቢያችን ደብረ ብርሃን የEnglish language improvement center (ELIC)  ያዘጋጀው የውይይት፣ንባብ፣ፅሁፍ እንዲሁም የተለያዩ የቋንቋ ችሎታን የሚያዳብሩ ነገሮች ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

የምዝገባ ቦታ= SE02 F1 ELIC OFFICE
የምዝገባ ጊዜ =ከህዳር 2-21-2017/በሁሉም ስራ ቀናት

@dbu11
ለሁሉም የምህንድስና ተማሪዎች 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

@DBU11
@DBU11
ለወንድ ተማሪዎች በሙሉ የተማሪዎች መኝታ አገልግሎት (students dormitory service) ባወጣው ማስታወቂያ ማንኛውንም አገልግሎት( i.e የመውጫ ፈቃድ ወረቀት )የተማሪ ህብረት ህንፃ ኮሪደር (ground) ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት እንደምትችሉ ገልጿል።

@DBU11
@DBU11
🚀 Join TechtonicTribe’s Opening Event at Debre Birhan University!

This Saturday, we’re launching a new chapter for tech enthusiasts and innovators. Join us as we explore fresh opportunities, connect with like-minded peers, and embark on a community-driven journey into the future of tech!

📅 Date: 7/03/2017
Time: 2:00 PM - 5:30 PM 
📍 Location: PR hall, DBU 
🎙️ Speakers: Meet inspiring industry leaders, including
                     Bereketab H/eyesus,
                     Amare Terefe,
                     and Abrham Assefa!

Be part of something bigger. Let’s code the future together! 🌍💻
🖇 Join Our : Channel | Group | Tik Tok | LinkedIn
የተሳሳተ መረጃ


የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ መደበኛ እና ሬሚዲያል ተማሪዎችን በተመለከተ እየተዘዋወረ ያለው የጥሪ ማስታወቂያ ትክክለኛ አለመሆኑን እንድታውቁ እና ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ በዚሁ ገጽ የምናጋራ መሆኑን እንገልፃለን።

@DBU11
@DBU111
#AD
𝑬𝑻𝑺𝑼𝑩 𝑭𝑰𝑵𝑫𝑺 𝑶𝑵𝑳𝑰𝑵𝑬 𝑺𝑯𝑶𝑷𝑷𝑰𝑵𝑮 🛍

ሰላም 👋 እንዴት ናቹህ 🤗

Trendy እንዲሁም BEST 🗣 አልባሳት ጫማ ሁዲ ቲሸርት ሽቶ Human hair ኤሌክትሮኒክስ .....  🥵 ብቻ ምን አለፋቹ የምትፈልጉት ሁሉ በእጃችሁ በደጃቻቹህ

ከእናንተ የሚጠበቀው ኢችን ጠቅ

👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/etsubfindsonlineshop

👆👆👆👆

ሁሉም በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ ቤተሰብ ይሁኑን

ቤተሰብ +

https://www.tg-me.com/etsubfindsonlineshop

መልካም ቀን 🙌
የህግ ተማሪዎች ቅሬታ 

እኛ የ2013 ባች የህግ ተማሪዎች አሁን በያዝነው የትምህርት ዘመን (2017) ዓ.ም  የህግ ትምህርት (LL. B curriculum) ትምህርታችንን እንደምናጠናቅቅ እናውቅ የነበረ እንዲሁም ቃል ተገብቶልን የነበረ ሲሆን ይህንንም ከዳር ለማድረስ በ 2015 የትምህርት ዘመን ሶስት ሴሚስተር፤ በ 2016 ደግሞ ከ የካቲት 23- ሰኔ 27 ባሉት አራት ወራት ሁለት ሴሚስተር  ወስደን ያጠናቀቅን ሲሆን ፤ በተጨማሪም ለዚህ ይረዳን ዘንድ ባለፈዉ የክረምት ወቅት የመመረቂያ ፅሁፍ (Research) ተሰጥቶን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እኛ ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና እራሳችንን በስነልቦና  እያዘጋጀን በምንገኝበት  በዚህ ወቅት የፈተናም ሆነ የመመረቂያ ጊዜያችን ወደ ጥር 2018 የተራዘመ እንደሆነ ተነግሮናል

፤ በመሆኑም ይህ የፕሮግራም መቀየር እና ቃል የተገባልን የጊዜ ሠሌዳ አለመተግበሩ ለከፍተኛ እና ተደራራቢ ችግርች ተጋላጭ ያደርገናል ፤ ከነዚህም መካከል፦

1ኛ.  እኛ የህግ ተማሪዎች  ከህግ ትምህርት ቤት ተመርቀን ስንወጣ  ወደ ስራ ለመግባት የምንወስደው የፌደራልም ይሁን የየክልሎቹ የፍትህ ቢሮዎች የሚያወጡት የዳኝነት ስልጠና (judicial training) መውሰድ የምንችለው እና ማስታወቂያ የሚወጣው በየአመቱ መጀመሪያ በመሆኑ ይህ ውሳኔ ስልጠናውን የምንወስድበትን ጊዜ በአንድ አመት በማራዘም ወደ 2019 ይወስደዋል። ከዚህም አለፍ ሲል በዛው አመት (2018) ለሚመረቁ ተማሪዎች ቅድሚያ የመወዳደር እድል የሚሰጥ በመሆኑ የአመታት ልፋታችን ውጤት ለፍሬ እንዳይበቃ ያደርገዋል ፤ ይህም ምን ያህል ኢኮኖሚያዊና ስነ ልቦናዊ ጫና እንደሚያስከትል እሙን ነው።

2ኛ. ከላይ ከተዘረዘሩት ነጥቦች በተጨማሪ የመውጫ ፈተና (exit exam) ላይ ከሚመጡ ኮርሶች ውስጥ የቀሩን ሁለት ብቻ ሲሆኑ እነሱንም አሁን ባለንበት ሴሚስተር በማካተት ለፈተናው ዝግጁ ማድረግ መቻሉ እና በ2018 ጥር ወር ላይ  ለመመረቅ በየጊዜው ከሚያገረሸው የሠላም እጦት የተነሳ በየትኛው ወር ላይ ጥሪ እንደሚደረግልን አለመታወቁ ውድ ጊዜያችንን  ከማራዘም (ከማቃጠል) ውጭ ከዚህ የተሻለ ጊዜ እንደማይኖረን አመላካች ነው።

3ኛ. ከእኛ ዩንቨርስቲ ጋር ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሌሎች ዩንቨርስቲዎች ማለትም ደብረ ማርቆስ፥ ወሎ፥ ፥ ጎንደር ፥ ደባርቅ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የኛ ባች (2013 entry) ተማሪዎችን ለማስመረቅ የሚያስችል ፕሮግራም አውጥተው ተማሪዎቻቸውን በማስተማር ላይ ይገኛሉ። ይህም ከሌሎች አቻዎቻችን ጋር እኩል ወደ ስራው አለም የምንቀላቀልበት እና ላሉት ውስን ክፍት የስራ ቦታዎች  እኩል ተወዳዳሪ እንዳንሆን በማድረግ ለኛም ፥ ላስተማረን ቤተሰብም ሆነ ማህበረሰብ ውሳኔው እጅግ ተስፋ የሚያስቆርጥ አድርጎታል።
ከላይ ከተዘረዘሩት ነጥቦች እና ከሚያስከትሏቸው ተጓዳኝ ችግሮች በመነሳት ይህንኑ ጥያቄ ለሚመለከተው የዩኒቨርስቲው አካል ማለትም ለ ፕሬዘዳንት ፅ/ቤት እና ለዩኒቨርስቲው ሴኔት በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ህብረት እና በዩኒቨርስቲው የህግ ማህበር በኩል ያቀረብን ቢሆንም አጥጋቢ ምላሽ ሳናገኝ ቀርተናል። በመሆኑም የሚመለከታቸው የዩኒቨርስቲው አካላት ተማሪዎችን በማወያየት እና ሌሎች መሰል ዩኒቨርስቲዎች እየተከተሉ ያሉትን አስቻይ ሁኔታዎች በአፅንኦት በመመልከት እንዲሁም የደረሰብንን እና ሊደርስብን የሚችለውን ከባድ ጉዳት እና ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት ውሳኔውን በድጋሚ እንዲመለከቱት ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

@DBU11
@DBU111
2024/11/16 09:52:29
Back to Top
HTML Embed Code: