Telegram Web Link
ከውስጥ ምንጮቻችን የደረሰን የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ!

የተለያዮ አመራሮቻችንን በስም መጥራት "ድብቅ ድርድር ጀምረዋል" የምትል የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እንዲሰራጭና እንዲሰራበት ለብልፅግናው መንጋ ስምሪት መሰጠቱን ባህርዳር ዊክሊክስ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል። ዓላማው የአመራሮቻችንን ተዓማኒነት ማሳጣትና ክፍፍል መፍጠር ነው።
የመረጃን ሃይል ያየንበት ደንበኛ ድል አስመዝግበናል። አስገራሚ እቅድ፣ አስገራሚ የኦፕሬሽን አፈጻጸም! መጀመሪያ በደፈጣ፣ ቀጥለው በቆረጣ ነድፈው ነድለው ጥለውታል።

እንመለስበታለን!
በቁጥጥር ስር የዋሉት ባንዳዎች
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ስም ዝርዝራቸው ይፋ ሆነ፦ ሰኞ ዕለት በፋኖ ቁጥጥር ስር የዋሉት የአምሐራ ሳይንት ወረዳ ባንዳዎች ቁጥር 12 ደርሷል፤

ከአርሶ አደሩ ግብር እየሰበሰቡ ለጥምር ጦር ቀለብ ሲሰፍሩ እና በግና ፍየል እየገዙ ህዝብን ለሚጨፈጭፍ አረመኔ ስጋ የሚቀልቡት የአምሐራ ሳይንት የንግድ እና ገቢዎች ፅ/ቤቶች ባለሙያዎች በብዛት የተካተቱበት የመንግስት አሽቃቦጮች ቡድን ግብር ሰብስቦ በመኪና ሲመለስ በፋኖ እጅ መግባቱ ይታወሳል። የእነዚህ ኮልኮሌዎች ስም እና ሀላፊነት እንደሚከተለው ቀርቧል፦

1·ወንድምሰው እንየው- የፍርድ ቤት የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢ

2. መስፍን ደረሰ አየለ- የግብርና ትምህርት ኮሙኒኬሽን ባለሙያ

3. እንዳለ አማረ ታደለ- የኮምፒውተር ባለሙያ

4. አለምነው ገሰሰ አበባው- ክትትል ባለሙያ

5. ጀንበሩ ብርሀኑ ጋሻው- የታክስ ሂሳብ ሰራተኛ

6. አሻግሬ አድማሱ አወቀ- የኢንስፔክሽን ባለሙያ

7. ገሰሰ ገበያው ታደሰ- የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ

8. መለሰ ወዳጄ እሸቱ- የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ

9· አንተነህ ታረቀ ታደሰ- የክትትል ባለሙያ

10· ጀንበሩ ተስፋው መንግስቱ- የንግድ ገበያ ልማት ባለሙያ

11· ታከለ ታደሰ ተገኘ- የሰው ሀብት ባለሙያ

12· ቃኘው አፍሬ ሊበን- ሾፌር

አሁን ላይ በፋኖ ቁጥጥር ስር ነው ያሉት፤ ነገር ግን በሸጋው ሎጋው የሚመራ የማፊያ ቡድን 200 ሺህ ብር በእያንዳንዳቸው ከተከፈለኝ እንድለቀቁ አደርጋለሁኝ ብሎ ውዥንብር በመፍጠሩ የተነሳ የመንግስት ሰራተኞች ለስራ ባልደረቦቻችን ማስለቀቂያ የሚሆን ገንዘብ እናዋጣ እያሉ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል።

የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ እስክንድር ነጋ ክፍለ ጦር በበኩሉ የተያዙት አመራሮችን በድርድር ለመልቀቅ የሚሞክር ኃይልን እንደማይታገስ እገምታለሁ። የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ የሆነው ፊታውራሪ ሀብታሙ ደምሴ (አባ ጨፍልቅ) በእንዲህ አይነት ጉዳይ ቀልድ እንደማያውቅ እስካሁን ከነበሩት ውሳኔዎቹ ተነስቼ መናገር እችላለሁ።

የተያዙ ባንዳዎች የፓለቲካ እና ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ፋኖ ሆነው ማየት እንፈልጋለን። በድርድር ከተለቀቁ ትግሉም ትግል አይሆንም፤ ለፋኖ መልካም ስም እና ዝናም ጥሩ አይደለም። ህዝቡም በፋኖ ላይ እምነት ሊኖረው የሚችለው እነዚህ ባንዳዎች ሳይለቀቁ ሲቀሩ ነው። ያዝ ለቀቅ ከተለመደ ህዝብም በፋኖ ላይ እምነት አይኖረውም5
ከአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም የተሰጠ      አስቸኳይ መግለጫ

ሕገ መንገስቱ ሕገ አራዊት ካልሆነ ሕግ ይከበር !
አንድ የሆነን ማሕበረሰብ ወይም አካል አንድ ሁኑ ማለት ይከብዳል፡፡ ምንአልባትም የተሻለ ሊሆን የሚችለው የበለጠ አንድ ሁኑ ማለት ሳይሻል አይቀርም፡፡ በመሰረቱ፣አንድ እንሁን ያልነው አንድ የመሆን ተፈጥሯዊ ማንነታችን ስለሚፈቅድ ነው፡፡

መገለጫችን ስለሆነና ስለምንችል እንዲሁም አንድ መሆን ማለት የግዴታ አንድ አይነት ማለትም አይደለም፡፡  ‹‹ አንድ እንሁን ›› ያልነው አንድ አለመሆናችን ያስከተለውን፤ያስከፈለንን እና የሚስከፍለንን ከባድ ዋጋ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ነው ፡፡ የአማራ ፋኖ ፣ የአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም እንዲሁም መላው የአማራ ሕዝብ ፈጽሞ ከማይደራደርባቸው ቁልፍ አበይት ጉዳዮች አንዱ አምሓራዊ አንድነቱ ነው፡፡

ዛሬም እንደ ትናንቱ እኛ አምሓራዊያን ከኢትዮጵያዊነት ሊያወርዱን አማሓራዊነታችን በታትነው እንደ አናሳ ብሔረሰብ ሊሳንስኑን ለሚመጡ የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ጠላቶች ረመጥ እሳት ነን፡፡  የነጻነት ታጋይን ልታስር ትችላለህ እንጅ ነጻነትን አታስርም ፤ ታጋይን ልትገድል ትችላለህ እንጅ ዓላማን የሰነቀ ትግል ሕያው ሆኖ ስለሚቀጥል ትግል አይሞትም፡፡

ዛሬ ታላቁ የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያን ከፊት በማስቀደሙና ዲሞክራሲያዊ የአምሓራዊ ብሔርተኝነቱን በማስቀደሙ ብቻ ለዘርፈ ብዙ ስቃይና መከራ ተዳርጓል፡፡ ይህ ደግሞ ሊያበቃ ይገባል እያልን አሁናዊ የሀገሪቱን ሁኔታ በጥልቅ በመረዳት የሚከተለውን መግለጫ አውጥተናል፡፡ ሰጠናል፡፡

ከምክክር ኮሚሽን አንጻር የምናነሳቸው ጥያቄዎች፤-

1ኛ. የአምሓራ ሕዝብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ በሆነበት ሰዐት እና የአምሓራ ሕዝብ በጦርነት ላይ በሚገኝበትና አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት በአልተደረገበት ሁኔታ
2ኛ. በሕዝብ ጥያቄ የተያዙ ምሁራንና አጀንዳ ቀረጻ ላይ የሚሣተፉ ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞችና ወጣቶች በታሰሩበት ሑኔታ እንዲሁም  በሲቪልና ወታደራዊ ተቋማት ያሉ ምሁር አምሓራዊያን በማንነታቸው ምክንያት እየተገፉና እየተሳደዱ በሚገኙበት ሁኔታ

3ኛ. በሃገረ መንግሥት ግንባታ የላቀ ሚና በሚጫወቱ የእምነት ተቋማት ላይ ለአብነትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንደ አምሓራ ሕዝብ ስቃይና መከራ ስደት እየተቀበለችበት ባለችበት ሰዐት እና በሃገራዊ አጀንዳ ተሳታፊ እንዳትሆን በተደረጉበት ወቅት

4ኛ. አጀንዳ ቀረጻ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ ሁሉም የመገናኛ ዘዴዎች ዝግ በተደረጉበት ሁኔታ ከዚህ በተጨማሪም  መዋቅራዊ ተሳትፎ የሚደረግበት ምንም አይነት አደረጃጀት እና ተዋረድ በሌለበት ሁኔታ

5ኛ. ነጻ እና ገለልተኛ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶችን በአገለለ ሁኔታ እና አዲስ አበባ ጨምሮ ሁሉም ክልሎች የሚኖሩ የአምሓራ ተወላጆችን አካታች እና አሳታፊ ባላደረገ መልኩ የተካሄደው የምክክር ሒደት

6ኛ. ሁሉም የተቃዋሚ ፖርቲዎች በአልተሳተፉበትና ከምክክሩ በተገለሉበት ሁኔታ

7ኛ. የአማሓራ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዳይመለሱ ክተት አዋጅ በታወጀበት ሰዐት የትኛዋ ኢትዮጵያ ናት ስትመክር የነበረችው እያልን ጥያቄችን እያቀረብን ከሐገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጋር የነበረን ሒደት እና ስለ ኮሚሽኑ አሰራርና ግልጸኝነት በቀጣይ ራሱን በቻለ መግለጫ ለመላው የአማራ ህዝብና ለኢትዮጵያዊያን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

            ስለሆነም 


አስቸካይ ጊዜ አዋጅ ከመጠናቀቁ አንጻር ያለን አቋም ፤-
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረውና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚነት ተጠናቋል፡፡

  በዚህ መሠረትም

1ኛ. በአዋጁ አተገባበር ዐውድ ውስጥ የቆዩ በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች በማንነታቸው ብቻ የታፈኑ እና ለስቃይ የተዳረጉ የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ

2ኛ. በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎችና በመላው አምሓራዊያን ላይ የተጣለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከአሁን በኃላ በሕገ መንግስቱ መሠረት ተቀባይነት ስለሌለው ለሕገ መንግስቱ ስርዓት መከበር ‹‹ ሕግ እያስከበር ›› ነው የሚሉ አካላት የሚፈጽሙት የኮማንድ ፖስት ተግባር ሁሉ ሕገ - አራዊት መሆኑን እንድታውቁት

3ኛ. በክልሉ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ፈርሶ የክልሉ ሕዝብ በነጻነት ከሰዐት እላፊ ገደብ ወጥቶ ሠላማዊ ኑሮውን የሚመራበት ምቹ ሁኔታዎች ለመፍጠር ሁሉም አካል የጋራ ተሳትፎና ርብርብ እንዲያደርግ

4ኛ. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ምክንያት በጦርነቱ የተጎዱ አምሓራዊያን ለማቋቋምና ለማገዝ ሁሉም በየአካባቢው የድርሻውን እንዲወጣ እንዲሁም አርምሞ ላይ የነበራችሁ በአምሓራዊያን ስም የተደራጃችሁ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች የተቋቋማችሁበትን ዓላማ ትልቁ ፍጡር ሰው ከሌለ እናተም የላችሁምና ሰውን ለማዳን በምናደርገው ርብርብ ከጎናችን እንድትቆሙ እየጠይቅን

5ኛ. ‹‹ አንድ ሁኑ ! ›› ወዳዳችሁም ጠላችሁም አምሓራዊያን አንድ ሁነናል ፡፡ ቃሉም በተግባር ተፈጽሟል ፡፡ ወንድም እህቶቻችን ፤ አባት እናቶቻችን የሆናችሁ አምሓራዊ በሁለት ጎራ ተከፍላችሁ የቤተሰብ ጦርነት የከፈታችሁ ወገኖች የጠላት መሳቂና መሳለቂያ ሳንሆን አንድ እንሁን፡፡ ጊዜው የአንድነት ሀይሎች የአሸናፊነት ዘመን እያልን

ለተከበርከው የትግራይ ህዝብ፤-  በተሳሳተ የ50 ዓመት የፖለቲካ ታሪክና ትርክ በመርዝ በተለወሰ ሴራ ከወንድም የትግራይ ሕዝብ ጋር ተዋጋን፡፡ የትግራይ ሕዝብና አምሓራዊያን ምን አተረፍን ? 1 ሚሊየን በላይ አምራች ክብር የሆነውን ሰው አጣን ፤ በመቶሽዎች አካላቸው ጉደለ ፤ በትሪሊየን የሚቆጠር ሀብት ወደመ ሕዝብ ተጎዳ የፖለቲካ ቁማርተኞች ግን እስከ ከራባታቸው በሐሴትና በደስታ አሉ፡፡

ስለዚህ የእኛን ደስታ የነጠቁ ቁማርተኞች ወደ ጎን በመተው ሕዝብ ለሕዝብ ወዳጅነታችን እናጠናክር ዘንድ በጋራ እንድንሰራ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የተከበርከው የኦሮሚያ ሕዝብ ፤- በኦሮማራ ሴራ ሳይገባን በቅንነት የኦሮሞ ደም የእኔም ደም ነው ብለን ጎንደር ላይ መስዋዕትነት ከፍለናል ፡፡ እናተም ጣና ኬኛ ብላችሁ በአምሓራዊያን መዲና ባህርዳር የጣና እንቦጭን አረም አርማችዋል ፡፡

የሚያምርብን ይህ ነው፡፡ እኛ አልተጣላንም ፡፡ አንጣላም ፡፡ የጋራ እንቦጭ አረም ለማረም ግን ዛሬም የኦሮሞና አምሓራዊነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናችን በተግባር እንድናሳይ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ለተከበራችሁ ወንድም የሌሎች ክልል ህዝቦች፤- አምሓራ ከማስተዋል፣ ጥበብን ከእውቀት፣ፈሪያ እግዚአብሔርን ፣ከሀገር ፍቅር ጋር አስተባብሮ የረቀቀ ሕዝባዊነት መገለጫ ነው፡፡ አምሓራነት ከመለያየት አንድነትን፤ከባርነት ነጻነትን ፤ ከውርደት ሞትን ፤ከመግፋት መገፋትን የሚል የአስተዋይ ሕዝብ ስነልቦናዊ ውቅር አናጭ ማንነት በመሆኑ በልዩነት ውበትን በመፍጠር ለዘመናት ከብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተጋብቶ፣ተዋልዶና ተዋዶ ኑራል ፡፡

ዛሬም ለወደፊቱም ይኖራል፡፡ በመሆኑም አብሮነታችን የጋራ መገለጫችን ነውና አብሮነታችን በጽኑ መሰረት ላይ እንድናስቀጥል በአምሓራዊያን ስም እንጠይቃለን፡፡

ሕዝብን ማሸነፍ አይቻልም ! ሰኔ 1 /2016 ዓ.ም                            ባህርዳር
ቅጠረኛው እና ተላላኪው ብአዴን በፋኖ ስም ያለ ቤት እና ንብረት መወረስ አለበት የሚል ትዕዛዝ ማውረዱ ተሰምቷል። ከዚህ በፊት በተለያዩ ቦታዎች የፋኖዎችን ቤት ማቃጠል፣ ንብረታቸውን ጭኖ መውሰድ እና ቤተሰቦቻቸውን የማሰር እና የማንገላታት ሥራ ሲፈጽም እንደነበር ይታወቃል።

ከሰሞኑ፤ አደረኩ ባለው ግምገማ 'ለፋኖ መሪ ለሆኑት፣ በስማቸው ደብዳቤ ተጽፎ እንዲደርሳቸው በማድረግ በይቅርታ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው እንዲገቡ ጥረት እናድርግ' ይህን ካልተቀበሉ ግን፣ በሥማቸው ያለውን ቤት እና ንብረት መውረስ አለብን የሚል ውሳኔ ላይ ደርሷል። እነሱን የሚረዳ የቅርብ ዘመድ ካለም፣ የዘመድ አዝማዳቸው ሃብትና ንብረትም መወረስ አለበት ማለቱ ታውቋል።

በዚህ መነሻ፣ ደብረ ማርቆስን ጨምሮ በተያዩ ከተሞች ነጋዴዎችን 'የፋኖ መረጃ፣ ሎጅስቲክ እና ደጋፊ ናችሁ' በሚል ነዴዎችን በጅምላ ማስር፣ ማዋክብ፣ ማስፈራራት እና ቤትቻውን ማሸግ እየሰራ ይገኛል።

ስለሆነም፤ ሕዝባችን ይህን የአገዛዙን ዘራፊነት ተገንዝቦ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ እናሳስባለን
እምሽክ !

በደቡብ ጎንደር ዞን #ላይ_ጋይንት ከ107 በላይ የጁላ ሰራዊት እና 9 ባንዳ ሚሊሻዎች እምሽክ ተደርገዋል። በዚህ ውጊያ ከ60 በላይ የጁላ ሰራዊት ደግሞ ቁስለኛ ተደርጓል።

ይህን ሁሉ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው አገዛዙ ኮለኔል ታደሰን ገድያለው ብሎ ቢያስወራም ኮለኔሉ ግን አሁንም ስራ ላይ ናቸው። ከወገን መጠነኛ ቁስለት ከማጋጠም ውጭ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ያገኘንው መረጃ ያመላክታል
መረጃ -ጎንደር
፨፨፨፨፨፨፨፨

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቋራ ኦሜዳድ እና በጌምድር ክፍለጦሮች በቋራ እልህ አስጨራሽ ውጊያ እያደረጉ ነው።

ክፈፍለጦሩቹ በጠላት ሐይል ላይ የበላይነትን ሲቀዳጁ ጠላት በበኩሉ ከቀጠናው ለማፈግፈግ ተገዷል። በአሁኑ ሰዓት ከገጠር አካባቢወች በተጨማሪ ሽንፋ ከተማም በፋኖዎቹ ቁጥጥር ስር ይገኛል።

የአድማ ብተናና የፖሊስ ሐይል እጅ እንስጥ እያለ እየተማፀነ ሲሆን መከላከያ ሐይል ተራራ ላይ ተከቧል ሲል የዕዙ ቃል አቀባይ ተናግሯል።

በተያያዘ መረጃ መንግስት ተብየው ቡድን የህዝብ ማመላለሻ አውሮፕላን ተጠቅሞ አየር ወለድ ለማውረድ ያደረገውን ሙከራ እንዳከሸፉበት  ቃል አቀባዩ ተናግሯል። በዛሬው ዕለት ሚካኤል ደብር አፄ መስክ የተባለ ሰፊ ሜዳ ላይ አየር ወለድ ለማውረድ የሞከረ ሲሆን በሙከራ ላይ እንዳሉ በተከፈተበት ተኩስ ሳይሳካለት ቀርቷል ብሏል።

የሲብል  መንገደኞች አውሮፕላን በተደጋጋሚ እየፈፀመው ባለው የጦር ወንጀል የሚጠየቅበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ብሏል ቃል አቀባዩ ኮማንዶ ያለው አዱኛ።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ 
ዋና አዛዥ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ 

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለአማራ ፋኖ
የጠላትን ቅስም ከሁለት "ቋቋቋ" ያደረገው ድል!

ከሰሞኑን ከዘገብናቸው ፊልም የሚመስሉ የነበልባሎቻችን ድል ውስጥ ወደ በረኸት ለመግባት በ17 መኪኖች ተግተልትሎ የመጣውን አራዊት ሰራዊት አብዛኛው ኃይሉን መንገድ ላይ ያስቀረንበት ነው።

ይህንን ተከትሎም ሁለት አስገራሚ ነገሮች መፈጠራቸውን ሰምተናል፦

1. የበረኸት ፋኖ እንደማይቀመስ ያወቀው አራዊት ሰራዊት እንደምንም የተረፈውን ኃይሉን ከበረኸት እስከ ምንጃር ሸንኮራ ድረስ 72 ኪሎሜትሮችን ደፈጣ ፍራቻ በእግር እየተጓዘ ተመልሷል። ከሞጆ በመኪና ተግተልትሎ መጣ… በደፈጣ ተራገፈ… ቀሪው በእግሩ እየተንፏቀቀ ወደ ሞጆ ተመለሰ።

2. ከቀን ግንቦት 23 እስከ ግንቦት 28 ድረስ ደግሞ የተጎዱ ወታደራዊ አመራሮች እና ወታደሮች በሄሊኮፕተር ሲያወጣ እንደነበር ባህርዳር ዊክሊክስ ለማወቅ ችለናል። 

ይህ ለጠላት ቅስም ሰባሪ የሆነን ታሪካዊ ድል የተመዘገበበትን አውደውጊያና ኦፕሬሽን የመራው በትግል ስሙ ሻለቃ አዝንበው የሚባል ወጣት፣ ቆፍጣና ነበልባል የከሰም ክፍለጦር ዋና አዛዥ ነው።
#ማስጠንቀቂያ

በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ የግዮን ሸመቾች ህ/ስ/ማ/ኋ/የተወሠነ የግል ማህበር ተቋም ውስጥ ንፁሐንን የሚያሳፍኑና በስርቆት ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከአፀያፊ እኩይ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተጠቆመ

1,መስፍን ፈጠነ=ሊቀመንበር
2,አምሳለ አረፍዓይኔ= ፀሀፊ
3,አለሙ ገላየ=ስራ አስኪያጅ
በጋራ በመተባበር ተቋሙን የመዘበሩ ሲሆን ንፁሃንን ለፋሽስቱ ስርዓት ሰለባ እንዲሆኑ ማድረጋቸው ተረጋግጧል
ሰሞነኛ የብልፅግና ጀነራሎችና ካድሬዎች ስብከት " እናንተ ፋኖን እንደምንም አምጡልን፣ እናንተ ያመጣችኃቸውን አይደለም መግደል ቀርቶ በጥፊ አንነካቸውም፣ እናንተ አምጧቸው እንጅ እኛ ወልቃይት ጠገዴን ጠለምትን ራያን እንጠብቃለን" ሁኗል። በጥፊ እንደተመታህ ሲገባህ ጥፊ ትዝ ይልሃል😁

ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ራያ አላማጣ የብልፅግና ስልጣን ማስጠበቂያ የህዝባችን ደግሞ የሰቀቀን አጀንዳ መሆን አይችልም። እድሜ ልክ ጦርነት የሚፈልግ ካለ ይሞክረው። ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ራያ አላማጣ ብልፅግና እንዳቀደው የሚድንበት ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ መቀበሪያው የፖለቲካ ፣ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ማዕከል ነው። አማራ ወይ ፍንክች።

በነገራችን ላይ ብልፅግና ከተወገደ ህውሃት አንድ ቀን አያድርም። እርስ በርስ ነው የሚጠባበቁት። ብልፅግና ካለ የህውሃት ሰርቫይቫል ይቀጥላል።

ድል ለፋኖ
ሰራዊቱ ፎጣ ሊለብስ ነው - ማረጋገጫ አግኝተናል!

ምንጮቻችንን ጠቅሰን በትናንትናው ዕለት ላወጣነው የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ ማረጋገጫ አግኝተናል። ከታች በቁጥር ሁለት ላይ እንደሚታየው፣ "አርሶአደር መስሎ ስምሪት የሚወስድ አራዊት ሰራዊት ተመልምሎ መሰማራቱን" ገልፀን ነበር።

ዛሬ ያገኘነው መረጃ የትናንትናውን የሚያጠናክር ሆኖ አግኝተነዋል -- "በሺዎች የሚቆጠር ፎጣ ተገዝቶ ወደ ጎጃም ቀጠና ለስርጭት መዘጋጀቱ" ታውቋል።

ይህ ለሁሉም ቀጠና ፋኖዎቻችን እንዲደርስ በማዛመት አግዙን።
ሰበር ዜና ጎንደር -አምባጊወርጊስ ‼️

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አምባጊወርጊስ ከተማ ላይ የነበረን ገዳይ ቡድን ማፅዳቱን አስታወቀ ።

እራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራ ገዳይ ቡድን ሙሉ በሙሉ ተወግዶ ከተማው በእነሱ እጅ እንደሆነ የዕዙ አደረጃጀት ሀላፊ ተናግሯል ።

ከተማዋን የያዛት የጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር አካል የሆነው ምስጋናው አጠኔ ብርጌድ እንደሆነም ተናግሯል ከተማው ውስጥ የነበረ የጠላት ሀይል በተኩስ ልውውጡ የተመታው ተመቶ የቀረው ተማርኳል ሲል ሻለቃው ተናግሯል ።
በአዲስ ቅዳምናና አካባቢዋ የአገዛዙ መንግስት በህዝቡ ላይ እያስፈፀመው ያለው ግፍና መከራ እንደቀጠለ ነው!!
ከዚህ በፊት የአማራ ፋኖ በአዲስ ቅዳምና አካባቢው ከስምንት ወራቶች በላይ ተቆጣጥሮትና ሲያስተዳድር በቆየበት ወቅት፣አካባቢው ከስርቆት፣ከውንብድና፣ከሌሎችም ወንጀሎች ነፃ ሆኖ ህዝቡ በሰላም ገብቶና ወጦ ሲተዳደር መቆየቱ ህዝብ ምስክር ነው፣ይሁን እንጅ ፋኖ ስልታዊ ማፈግፈግ አድርጎ የአዲስ ቅዳም ከተማን ከለቀቀበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ የአገዛዙ መንግስት አስፈፃሚ አመራሮች የግለሰብ ወንበር ጠባቂ በሆነው መከላከያ፣በሆዳሙ የአድማ ብተና፣ፖሊስና ሚሊሻ አማካኝነት የወንድ ሚስት የደፈራ ወንጀል፣የእጅ ስልክና የገንዝብ ዘረፋ ወንጀል፣ወጣቶችን የድብደባና የአካል ማጉደል ወንጀል፣ወንጀል ሳይሰሩ በግል ቂም ግለሰቦች ማሰርና የማሰቃየት ወንጀል፣አስሮ ገንዘብ የመቀበል ወንጀል ወዘተ እየተፈፀመባቸው መሆኑን በደል ከደረሰባቸው እና የህዝብ እንግልት ከሚያሳስባቸው ከአንዳንድ ሰዎች መረጃዎች ደርሰውናል፣ጥምር የፀጥታ ኃይሉ በህዝቡ ላይ ወንጀል እንዲፈፀምበት የታሰበው ፋኖን ተንከባክባችሁ ስትይዙት እኛ ስንገባ በክፋ አይን አይታችሁናል በሚልና ሲሆን፤
ጉዳዮን  በበላይነት የሚመሩት ቦክሰኛውና ተደባዳቢው የፋግታ ለኮማ ም/አስተዳዳሪ አቶ ታገል እጅጉ፣ተለጣፊውና ተላላኪው የአዲስ ቅዳም ከተማ ገ/ኢ/ል/ት/ፅ/ቤትና ምክትል ከንቲባ አቶ ምንተስኖት ሁነኛው፣ ሳጅን ግዛቸው ባዮ የአዲስ ቅዳም ከተማ ሰላምና ደህንነት ፅ/ ቤት ኃላፊ፣ኮማንደር መንግስቱ የኔው የአዲስ ቅዳም ከተማ አስተዳድር ፖሊስ አዛዥ፣ኢንስፔክተር አየነው የፋግታ ለኮማ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ፣የሆኑ የስረዓቱ ታማኝ አገልጋይ እና አስፈፃሚ፣ህዝቡን በማሰር ገንዘብ የሚቀበሉ፣የሚያሰርቁ፣የሚያስደፍሩ ወዘተ ጉዳዮን በበላይነት የሚመሩና የሚያስተባብሩ መሆኑን የአማራ እንዲሁም የኢትዮጵያ  ህዝብ እንዲያውቅልን የህዝብ እንግልትና ስቃይ ለሚቆረቆሩ ሚዲያዎች ይድረስልን።
ድል ለክንደ-ነበልባሉ ፋኖ!!
ውድቀትና ውርደት ለብልፅግና መንግስት!!
ፋኖ ወደ ፊት!!!!
የአማራ ጪፍጨፋና የመሬት ንጥቂያ በምእራብ ሸዋ!!!

በምእራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ በሚገኙ በርካታ አማራወች ላይ በርካታ በደሎች ሲፈጸሙ ቆይተዋል እየተፈጸሙም ይገኛሉ ።የህም በ2008 ዓ.ም በርካታ አማራወች ከአበሽጌ ወረዳ አሻጋሪ የምትገኝ ሰኞ ገበያ የምትባል ቦታ የሚገኙ አማራ ማህበረሰቦችን ቤታቸውን በማቃጠል ሚሊሾቹን በመጨፍጨፍ የኦሮሚያ ፖሊስ ሚናቸውን ተወጥተዋል ።በዚህ የዘረፋ፣ የማፈናቀል ፣የመግደልና የማሳደድ ተግባር የተሳተፉ ወንጀለኞች ባለጊዜዎች በመሆናቸው የማእረግ እድገት እንጂ በህግ የጠየቃቸው የለም ።
ወደ ቅርብ ጊዜዉ ስመለስ በወረዳው ዉስጥ ከሚገኙ 35 ቀበሌዎች ዉስጥ በሁሉም ቀበሌዎች አማራ የሚኖር ሲሆን በአሁኑ ሰአት ደግሞ ስምንት (8) ቀበሌ ብቻ ላይ ነዉ የሚኖረው ።27(ሃያ ሰባት )ቀበሌ ዉሰጥ የሚገኙ አማራወች ህይወታቸው ፣ገንዘባቸው ፣መሬታቸው ተቀምተዉ በህይወት የተረፉትን በማባረር ጨርሰዋል ።
የተቀረው ስምንት ቀበሌዎችን ደግሞ ዱሮ ጫካ መንጥሮ ያለማ አማራ ሁለት ሄክታር ተሰጥቶት ቀሪውን የኦሮሞ ቄሮ እንድቀማቸዉ፣መሬት በሚሸጥበት ሰአት ገዝተው ይኖሩ የነበሩ አማሮችን ደግሞ የባቴ፣የአያቴ ርስት ነበር በማለት በመቀማት አብዛኞቹ አማራች ከመሬት ባለይዞታነት ታግደዉ ተባረሩ ።ያንን የተቀማ መሬት ደግሞ የወረዳው ካቢኔወች ጪምር በመቀራመት በትራክተር እያረሱ ኢንቨስትመንት እያሉ ይገኛሉ ።አሁን ደግሞ ራሱ መንግስት ቦንብ በማፈንዳት በርካታ ኦሮሞወችን ካስጨፈጨፈ በኋላ በአካባቢው የሚገኙ ከ100 በላይ አማራዎችን በኦሮሚያ ልዩ ሃይል በአሰቃቂ ሁኔታ አስጨፍጪፏል።
ይህ ሁሉ አሻጥር ከ35 ቀበሌ አማራ ወደ 8 ቀበሌ ያለዉን አማራ ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ካላቸዉ እቅድ የተነሳ ነዉ።በዚህም የኦሮሚያ ልዩ ሃይል አማራዉን ይገድላል ፣ያባርራል፣ያሯሩጣል፣
የ።ሃረር ሰፋሪዎች(በዛዉ የሚገኙት )ደግሞ የአማራውን ቤት ዘርፈው ያቃጥላሉ ።
ይህ የዘር ፍጅት እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልሄደም ።
#አገዛዙ በጅጋ የፈጸመው ጭፍጨፋ/የዘር ማጥፋት ወንጀል

የአማራ አክቲቪስት መቼ ነው ትርጉም ያለው ስራ የሚሰራው?
የአማራ ህዝብስ ይህን ዘር አጥፊ አረመኔ በጉያው ታቅፎ የሚኖረው እስከመቼ ነው?

ለምን ፋኖ ክተት አውጆ ላንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ጠራርጎ ከክልሉ ለማሶጣት አይሰራም?

አማራ ሆ ብሎ የሚነሳው መቼ ነው? ፋኖ በዚህ ያክል ወኔ ጠላትን እየቀበረው ባለበት የአማራ ህዝብ ስለምን ገዳዩን በጉያው አስቀምጦ ይጨፈጨፋል።
ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ የተረጋገጠ መረጃ!

15 ሴት ተማሪዎች በአገዛዙ ዙፋን ጠበቂ ሠራዊት በጭካኔ ተደፍረዋል። የአንድ ሴት ተማሪ ሕይወት አልፏል። ብዙ ተማሪዎች ስልካቸውን ጨምሮ ያላቸውን ንብረት ተዘርፈዋል። ዛሬ ብዙ ተማሪዎች ከግቢ እየወጡ ይገኛሉ።
ሰበር የድል ዜና!!

ከፍተኛው የብልፅግና መከላከያ ደህንነት በጀግኖቹ መሸኘቱ ተበሰረ።

በአማራ ፋኖ በጎንደር የአፄዎቹ ክፍለጦር ተሰርቷል በተባለው ኦፕሬሽን ኮሮኔል ዮሴፍ መገደሉ ተነግሯል።

(አሁን በውጊያ ላይ የሚገኙት ፋኖዎቹ ዝርዝሩን ከደቂቃዎች በኋላ ይዘን የምንመለስ ይሆናል)

ሞገሴ ሽፈራው
2024/06/26 12:37:12
Back to Top
HTML Embed Code: